አ.ሳ.ቴ.ዩ‼️
#የአዳማ_ሳይንስና_ቴክኖሎጂ_ዩኒቨርሲቲ ከጥር 12 እስከ 14 ቀን 2011ዓ.ም. ሁሉም የመደበኛ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ለቀው እንዲወጡ መወሰኑን ተከትሎ፣ ተማሪዎቹና የዪኒቨርሲቲው አስተዳደር እየተወዛገቡ ነው። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት #ለሚ_ጉታ (ዶ/ር)የተላለፈው ውሳኔ ትክክል ነው ሲሉ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ተማሪዎቹ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ የተወሰነው ውሳኔ ሕጉን መሠረት ያደረገ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ያስረዱ ቢሆንም፣ ተማሪዎቹ የተወሰደው ዕርምጃ መሬት ላይ ያለውን #እውነታ ከግምት ያላስገባ ነው በማለት #ተቃውመውታል።
ዩኒቨርሲቲው ከጥር 15 ቀን ጀምሮ ለቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የሚሰጠውን ማንኛውንም አገልግሎት እንደሚያቋርጥ ጥር 12:በዩኒቨርሲቲው ሰሌዳ ባወጣው ማስታወቂያ ይፋ አድርጓል፡፡
በዩኒቨርሲቲው ሴኔት መመሪያ መሠረት አንድ ተማሪ በሴሚስተር መከታተል ያለበት ቢያንስ ሰማንያ በመቶ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ሲሆን፣ ተማሪዎቹ በሴሚስተሩ ከተቀመጠው የትምህርት ክፍለ ጊዜ 34.4 በመቶ እንዳልተከታተሉ፣ በመመሪያው አንቀጽ 101.2 እና 231.3መሠረት በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ውሳኔ ዕርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ በማግኘቱ ዕርምጃው መወሰዱን በዩኒቨርሲቲው የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ይፋ የሆነው ማስታወቂያ ይገልጻል፡፡
ይህን ያህል የትምህርት ክፍለ ጊዜ ሊከታተሉ ያልቻሉት በተደጋጋሚ ለተቃውሞ ሠልፎች በመውጣታቸው እንደነበር ተማሪዎቹ ገልጸው፣ ከወር በፊት በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ሦስት ተማሪዎች ሕይወት ማለፉ ለተቃውሞዎቹ መራዘም ምክንያት መሆኑንም አክለዋል፡፡ በዚህ ክስተት ማግሥት ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የአጋማሽ ፈተና እንዲወስዱ ማስታወቂያ ወጥቶ እንደነበር፣ ፈተናውን መውሰድ እንደማይችሉ ቢገልጹም ሰሚ አለማግኘታቸውን ተማሪዎቹ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ለተከታታይ ዘጠኝ ቀናት የመማር ማስተማር ሒደቱ ተቋርጧል በማለት የተላለፈውን ውሳኔ ተቃውመዋል፡፡
‹‹ይኼንን ፈተና መውሰድ ያልቻልነው በሦስቱ #ወንድሞቻችን ላይ የደረሰው ድንገተኛ ሞት ምክንያት በደረሰብን መሪር #ሐዘንና #ድንጋጤ እንዲሁም ሥርዓተ ቀብር ለመፈፀም ወደ የትውልድ ቦታቸው (አሰላ፣ አለታ ወንዶና ባህር ዳር) በመጓዛችን ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ተገቢውን ዝግጅት አላደረግንም፤›› ሲሉ ፈተናው እንዲራዝም የጠየቁበትን ምክንያት ለሪፖርተር ያስረዱ ሲሆን ‹‹ዋናው ጥያቄያችንም የደኅንነት ጥያቄ ነው›› ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የሞቱትን ተማሪዎች በሚመለከት ከአዳማ ፖሊስ መምሪያና ከቅዱስ ጳውሎስ ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የአስክሬን ምርመራ ውጤት እንደደረሳቸው ወዲያውኑ ለተማሪዎች ይፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱም ይህ ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊት ተማሪዎቹ የሁለተኛና የሦስተኛ ዲግሪ ዕድል ይመቻችልን እንዲሁም የሥራ ዕድል ትስስር ከኢንዱስትሪዎች ጋር እንደሚፈጠርልን ቃል ተገብቶልን ነበር በሚል ከሦስት ሳምንት በላይ ትምህርት አቋርጠው እንደነበር ተናግረዋል፡፡ እነዚህ ቀናት ሁሉ ባክነው የመጀመሪያውን መንፈቀ ዓመት ዕቅድ ማሳካት ስለማይቻል እንደ አዲስ የመማር ማስተማሩ ሒደት የካቲት 25 እና 26 ቀን 2011 ዓ.ም. እንዲጀመር በሴኔቱ ተወስኗል ብለዋል፡፡ የባከነውን የትምህርት ክፍለ ጊዜ ለማካካስም አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መልሰን ለመጥራት ርብርብ እያደረግን እንገኛለን ሲሉም አክለዋል፡፡
ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia

"የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ
.
.
ከትናንት በስቲያ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ET 302 ዋና አብራሪ የነበረው ያሬድ ጌታቸውን ለአስራ አንድ ዓመታት የሚያውቀው ኡጋንዳዊ ጓደኛው ሃሰን ካቴንዴ ያሬድ ራግቢ በጣም ይወድ እንደነበር ይናገራል።
ያሬድና ሃሰን የሚተዋወቁት ከዓመታት በፊት ቦሌ አካባቢ በሚገኝ አንድ ህንፃ ፀጉር ቤት ያሬድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ የበራሪ ፅሁፍ ወረቀት ይዞ ሃሰን [ፓይለት ነህ] ብሎ ያሬድን በጠየቀበት አጋጣሚ ነበር።
ያሬድ ኬንያ እንደተወለደ ነግሮት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ ያወሩት በስዋሂሊ እንደነበር ሃሰን ያስታውሳል።
ሃሰን እንደሚለው ያሬድ ስፖርት የሚወድ አይነት ሰው የነበረ ሲሆን ለራግቢ ግን ልዩ ፍቅር ነበረው።
ያሬድና ሃሰን አዘውትረው ይገኛኙ የነበረው ግእዝ የሚባል የፈረንሳይ ሬስቶራንት ተገናኝተው ነበር ራግቢ የሚመለከቱት።
መጀመሪያ አካባቢ ሀሰንም መኪና ስላልነበረው አብዛኛውን ጊዜ ያሬድ ያሽከረክር የነበረውን የአባቱን አሮጌ መኪና እየሾፈረ ብዙ ቦታዎች መሄዳቸውንም ሃሰን ያስታውሳል።
ያሬድና ሃሰን ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት ከሁለት ሳምንት ገደማ በፊት የነበረ ሲሆን በሎሜ ስካይ አየር መንገድ ስራ ስላገኘ ጓደኛቸው ነበር ያወሩት።
ያሬድ የተወለደው ኬንያ ውስጥ ሲሆን እናቱ ኬንያዊ ሲሆኑ አባቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ናቸው። የልጅነት ጊዜውን በኬንያ ያሳለፈ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ኢትዮጵያ ውስጥ ተከታትሎ የኢትዯጵያ አየር መንገድ አቬሽን ትምህርት ቤትን ተቀላቅሏል።
ሃሰን እንደሚለው ያሬድ ኢትዮጵያዊም ኬንያዊም ማንነቱን ይወድ ነበር። ያሬድ አማርኛ ፣ ስዋሂሊና እንግሊዝኛ ቋንቋዎችን ጥርት አድርጎ ይናገር እንደነበር ሀሰን ገልፆልናል።
"ብዙ ጊዜ ማንነቱን የሚያውቁ ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያዊ ነህ ሲሉት [ኢትዮጵያዊና ኬንያዊ]ብሎ ይመልስ ነበር] በማለት ነገሩ አንዳንድ ጊዜም ያሬድን ያስቆጣው እንደነበር ሃሰን ይናገራል።
ሃሰን የአደጋውን ዜና የሰማው ከማህበራዊ ሚዲያ ሲሆን መጀመሪያ ላይ ጓደኛው በአደጋው ስለመሞቱ ያወቀው ነገር አልነበረም።
"የአደጋውን ዜናና የአውሮፕኑን ሰራተኞች ስም ዝርዝር ስመለከት ያሬድ የሚል ስም ባይም የተለመደ ስም ስለሆነ ሌላ ያሬድ ነው ብዬ አሰብኩ። የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም። ቆይቶ ማታ ሁለት ሰዓት ላይ ሌላ ጓደኛችን ስለ ያሬድ ሰማህ ወይ? ምንድነው ምንትለው? ያሬድ ምን ሆነ ነው ያልኩት። በጣም አሰቃቂ ነው" ብሏል ሃሰን።
ከዚያም ጓደኛው የተከሰከሰው አውሮፕላን አብራሪ የእነሱ ጓደኛ ያሬድ እንደሆነ ሲነግረው ለማመን በጣም እንደከበደውና ሊሆን አይችልምም የሚል ስሜት እንደተሰማው ይናገራል።
"ለማመን የሚከብድ ነገር ነው። መተኛት አልቻልኩም እስካሁን #ድንጋጤ ውስጥ ነኝ"
እሱ ብቻ ሳትሆን የሀሰን እናትም በድንጋጤ ውስጥ እንዳሉ ይናገራል።
ያሬድ የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ይመለከት እንደነበር የሚናገረው ሃሰን "በሚገባ #የሰለጠነ አብራሪ ነው። እርግጠኛ ነኝ #እስከመጨረሻዋ ሰዓት ብቃቱን እንደተጠቀመ" በማለት ጓደኛው ያሬድ እንደ ጀግና እንዲታወስ እንደሚፈልግ ይናገራል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ አማርኛ