TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቤቲንግ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ጨምሮ ሌሎችም ተቋማት ነገ ከጥዋቱ 2:30 ላይ የስፖርት ውርርድ ፈቃድ ከተሰጣቸው ድርጅቶች ጋር ሊመክሩ ቀጠሮ መያዛቸው ተሰምቷል። ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር በመተባበር አዘጋጀሁት ባለው የምክክር መድረክ ላይ ፤ የስፖርት ውርርድ ፈቃድ የተሰጣቸው ድርጅቶች ጥዋት 2:30 ላይ ቀበና አካባቢ በሚገኘው ራስ አምባ ሆቴል የስብሰባ…
#ቤቲንግ

➡️ " ቤቲንግ ቤቶች ዳግም #እንዳይከፈቱ ሕብረተሰቡ አሳስቦናል " - የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ

➡️ " ሁሉንም ቤቶች በጅምላ መፈረጅ ትክክል አይደለም። ህጉን ተከትለው የሚሰሩና ብዙ ሰራተኛ ያላቸው ቤቲንግ ቤቶች አሉ " - የቤቲንግ ቤት ባለቤቶች

በአዲስ አበባ ከተማ በቤቲንግ ቤቶች እንቅስቃሴ ዙሪያ ሲካሄድ በነበረ የዳሰሳ ጥናት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መደረጉ ተሰምቷል።

ውይይቱ የተደረገው፦ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ገቢዎች፣ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኃላፊዎች ወይም ተወካዮች በተገኙበት ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በተቋቋመው ግብረሃይል አማካይነት ባለፈው ጊዜ በዘርፈ ብዙ ችግሮች ውስጥ የተገኙ የቤቲንግ ቤቶች በጥናት ተመስርቶ እንዲታሸጉ መደረጋቸውን ገልጿል።

በዚህም፦

1ኛ. አብዛኛው ቤቲንግ ቤቶች በትምህርት ቤቶች አቅራቢያ ላይ በመሆናቸው፣

2ኛ. የብሔራዊ ሎቶሪ ባወጣውን ደንብ መሠረት ዕድሜያቸው ከ21ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች ገብተው ሲጫወቱ በመገኘታቸው፣

3ኛ. በቤቶቹ ውስጥ አዋኪ ድርጊቶች ማለትም፦ ጫት መቃም፣ አልኮል መጠጦች መጠጣት...ወዘተ ሲፈፀምባቸው በመገኘታቸው፣

4ኛ. ያለንግድ ፈቃድ ሲሰሩ በመገኘታቸው፣

5ኛ. የቡድን ፀብ የተከሰተባቸው መገኘታቸው ለመዘጋታቸው ምክንያት መሆኑን አስረድቷል።

ቢሮው፤ " ሕብረተሰቡም በቤቲንግ ቤቶች ደስተኛ እንዳልሆነ ተረድተናል " ብሏል።

ቢሮው ፤ ከዘርፉ ከሚገኘው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ አመዝኖ እንደሚታይ ፤ ቤቲንግ ቤቶች ዳግም እንዳይከፈቱ ሕብረተሰቡም አሳስቦናል ሲል አሳውቋል።

በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱ ምክንያቶች የታሸጉ የቤቲንግ ቤቶች ፦

1ኛ. ለቤቲንግ ቤት ያከራዩ የቤት ባለቤቶች የንግድ ዘርፉን ቀይረው ከመጡ፣

2ኛ. " አገልግሎቱን አንፈልግም ካሁን ቀደም ሳናውቅ ስለገባንበት ከዚህ በኋላ አንሠራም " ብለው ማረጋገጫ ለሚሠጡና ቤቶቹ ተከፍተው ለሌላ አገልግሎት እንዲውሉ ለማድረግ ዝግጅቱ ተጠናቋል ሲል የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አሳውቋል።

በሌላ በኩል፤ በአዲስ አበባ ስፖርት ውርርድ /ቤቲንግ/ በመንግስት ከታሸገ 3 ወር ሆኖታል የሚሉ በዘርፉ ላይ ያሉ አካላት ፤ ትክክለኛ መረጃ እያገኙ እንዳልሆነና በየ ወረዳው የሚነገራቸው የተለያየ ሃሳብ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

" ዘርፍ ቀይሩ ወይንም ዕቃ አውጡ እየተባልን ነው ፤ ብሄራዊ ሎተሪ እንደሚከፍትልን እና ዝግጅት እንድናደርግ ብሎም እድሳት አድርጎ ፍቃዳችንን ከሰጠ በኋላ ነው እንዲ የተጉላላነው " ብለዋል።

" በስራችን ብዙ ሰራተኞችን የያዝን እና ከፍተኛ ግብር ለሀገራችን የምናስገባን ድርጅቶች ማንገላታት አግባብ አይደለም " የሚሉት የዘርፉ ባለቤቶች " ስራ በሌለበት ወቅት ብዙ ስራ አጦች በከተማችን ባሉበት ሁኔታ ተጨማሪ ስራ አጦች እንድንሆን እየተደረግን ነው " በማለት ቅሬታ አቅርበዋል።

" ቤቲንግ መስራት ሲገባቸው አለአግባብ ከህግ ውጪ የሚንቀሳቀሱ ካሉ በህግ መጠየቅ እንጂ ሁሉንም በአንድ መፈረጅ አይገባም " ብለዋል።

የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ቤቲንግ ቤቶች እስከ ወዲያኛው እንዲዘጉ ጫና እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

የዘርፉ ባለቤቶች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፤ " በአጠቃላይ ጥብቅ ቁጥጥር ተደርጎ ከእምነት ተቋማት ፣ ከትምህርት ቤት መራቅ ያለበትን ርቀት ተከትሎ እድሜ ከ21 አመት በላይ ብቻ እንዲጠቀም ተደርጎ ቢቀጥል ለሀገርም ለህዝብም ጥቅም ይኖረዋል " ብለዋል።

@tikvahethiopia