TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መቐለ

ባለፈው የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ/ም ሌሊት በትግራይ መቐለ ከተማ ዓይደር ከፍለ ከተማ በተለምዶ " ሓሚዳይ የኢንዱስትሪ መንደር " ተብሎ በሚጠራ ቦታ በቡድን የተደራጁ ዘራፊዎች የተጠና ስርቆት ሊፈፅሙ ሲሉ ተደርሶባቸው አምልጠዋል።

በወቅቱ ይህ መረጃ የደረሰው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ቦታው ድረስ በመሄድ ጉዳዩን ተከታትሏል።

ድርጊቱ እንዴት ተፈፀመ ?

የካቲት 14/2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት የተደራጁ ዘራፊዎች በሁለት አቅጣጫ #ጠባቂ_በመመደብ የተቀሩት በከፍታ ቦታ የተሰቀለው ባለ 400 ኪሎ ቮልት ትልቅ ትራንስፎርመር መሳልል በመጠቀም ወደ መሬት ለማውደቅ ይጥራሉ።

በዚህ መሃል በአከባቢው የነበረ ጥብቃ ማንነታቸው ሲጠይቃቸው ዘራፊዎቹ የመንግስት ስራ በመስራት ላይ መሆናቸውንና ከማደናቀፍ ተቆጥቦ ስራውን እንዲሰራ ያስጠነቅቁታል።

ብዛት ያላቸው መሆናቸው የተገነዘበው የጥበቃ ባለሞያ ትእዛዛቸው ተቀብሎ የሄደ በመምሰል ራቅ ወዳለ ቦታ በመሄድ በአካባቢው ከሚያውቃቸው ጥበቃዎች ወደ አንዱ ስልክ ይደውላል።

በዚህ መሃል ዘራፊዎቹ ትራንስፎርመሩ ከነበረበት ከፍታ ቦታ ወደ መሬት በመጣል የሚፈልጉት የውስጥ አካል ለመዝረፍ በጥድፍያ ይሰራሉ።

በዚህ ሰዓት በፀጥታ የተዋጠው አከባቢ በጥይት #ቶክስ እና በጥሩምባ ድምፅ ይረበሻል።

ዘራፊዎቹ እጅግ ከመደንገጣቸው የተነሳ የጀመሩት ሳይጨርሱ በሩጫ በትንትናቸው ይወጣል።

በአከባቢው በነበሩ የጥበቃ ሰራተኞች ጥረት ስርቆቱ ከመፈፀም ቢድንም ትራንስፎርመሩ ከከፍታ ወደ መሬት ተከስክሶ ከጥቅም ውጪ ሆኗል።

የስርቆት ሙከራው ወደ ፓሊስና የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎተ ሪፓርት ተደርገዋል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እያፈላለገ ነው።

የኤሌክትሪክ ሃይል የቴክኒክ ቡድን ከስርቆት አምልጦ መሬት ላይ ወድቆ የተከሰከሰው ትራንስፎርመር ተጥግኖ መልሶ አገልግሎት መስጠት ይችል እንደሆነ እየሰራበት ነው። 


የስርቆት ሙከራው የተካሄደበት ቦታ ሓሚዳይ የተባለ የኢንዱስትሪ መንደር ፡ ቀን ሰውና ተሽከርካሪ የሚበዛበት ፤ ጨለማ ሲሆን ደግሞ በሰው እጦት ፀጥታ የሚሰፍንበት ነው።

የስርቆት ሙከራው ሲፈፀም በመቐለ በንፋስ ምክንያት በበርካታ አከባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቋረጥ ስለነበረ ለስርቆቱ አመቺ ሁኔታ ሳይፈጥርላቸው አልቀረም ተብሏል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ገለሰብ ፤ የስርቆት ሙከራው ተራ ስርቆት ሳይሆን በኤሌክትሪክ ሃይል ሰራተኞች የታገዘ የባለሙያ ስርቆት ነው የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልጸዋል።

የትራንስፎርመር ስርቆት ሙከራው ምን ያለመ ነበር ?

የመቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ስርቆቱ ለምን አላማ እንደተፈፀመ ለአንድ የኤሌክትሪክ ሃይል የቴክኒክ ባለሞያ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

ባለሞያው ፦

- ይህ መሰል ሰርቆት በተለይ በጦርነቱ ጊዜ እጅግ የተባባሰ እንደነበረ ፤ ሰርቆቱ በትራንስፎርመሩ ውስጥ የሚገኘው ፈሳሽ ዘይትና ኬብል ለመውሰድ ያለመ መሆኑን፤

- ከትራንስፎርመሩ የሚቀዳ ዘይት ከነዳጅ ጋር ተቀላቅሎ ጥቅም ላይ እንደሚውል ፣ ኬብሉ ደግሞ ቀልጦ ከወርቅ ተደባልቆ እንደሚሰራና በተጨማሪ ለብየዳ ስራ እንደሚውል ፤

- አሁን ስርቆቱ በተፈፀመበት ቦታ በጦርነቱ ጊዜ 800 ኪሎ ቮልት ያለው በአከባቢው የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችና ፋብሪካዎች የሚጠቀሙበት ትልቅ ትራስፎርመር በመፍታት በወስጡ ያለው ዘይት በመዘረፉ ምክንያት ተቃጥሎ ከጥቅም ውጭ በመሆኑ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ መደረሱን ገልጸዋል።

#TikvahFamilyMekelle

@tikvahethiopia