TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#መቐለ #ኣሉላ_ኣባነጋ_ኤርፖርት
በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች " ወደ መቐለ ሊያመራ የነበረ አውሮፕላን አደጋ አጋጠመው " በሚል የሚሰራጩት መረጃዎች #ትክክለኛ_አይደሉም።
ዛሬ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው የመንገደኞች አውሮፕላን መንገደኞችን እንደያዘ በመቐለ " አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ " አደጋ አጋጥሞታል።
ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ግለሰብም ፤ አውሮፕላኑ መንሸራተት አጋጥሞት ከዋናው መንገድ መውጣቱን ገልጸዋል።
በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።
የአውሮፕለን አደጋው ዝርዝር መነሻ ላይም ማጣራት እየተደረገ ነው ተብሏል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣን ፕ/ር ክንደያ ገ/ህይወትም ዛሬ 8 ሰዓት ላይ አውሮፕላኑ ተንሸራቶ ከዋናው መንገድ በመውጣት አደጋ የገጠመው በመቐለ አለላ አባነጋ ኤርፖርት መሆኑን ገልጸው ፤ በመንገደኞች ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ አሳውቀዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድም በመቐለ አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ስለተፈጠረው ነገር መረጃ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ይህ ሆኖ ሳለ አደጋው " ወደ መቐለ ሊበር ሲል በአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት " እንደደረሰ ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያ እየወጡ ያሉት መረጃዎች ትክክል አይደሉም።
መረጃው በቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።
@tikvahethiopia