TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተፈተኗቸው የትምህርት አይነቶች መካከል ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት በመመዘኛነት የማያገለግሉ ውጤቶች፦

በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ፦

•ባዮሎጂ፣
•ኬሚስትሪ እና ስነ-ዜጋ (Civics) ፈተናዎች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ለመቀላቀል በመመዘኛነት #አያገለግሉም

በማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ፦

•የታሪክ (History)፤
•ኤኮኖሚክስ እና ስነ-ዜጋ ፈተናዎች ውጤቶች #ውድቅ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዘሪሁን ዱሬሳ (ዶ/ር) እንዳሉት ባለፈው ሰኔ ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመቀጠል በእንግሊዘኛ፣ ሒሳብ እና አፕቲቲዩድ ውጤቶቻቸው ይለካሉ።

ከተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ፊዚክስ፣ ከማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ደግሞ የጂኦግራፊ ፈተናዎች ለመመዘኛነት ተመርጠዋል።

ዶክተር ዘሪሁን ዱሬሳ «ተማሪዎችንም ፍትኃዊ በሆነ መልክ ሊያወዳድር እና ከእነሱ ችሎታ ባሻገር ምንም መበላለጥን ሊያስከትል የማይችል ሆኖ ስላገኘንው እነዚህን ተጠቅመን ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲ መመደብ እና የተለያዩ ሥራዎችን ለመሥራት ወስነናል» ብለዋል።

ከ322 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ከሰኔ 6 እስከ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. የተቀመጡበት ይኸው ፈተና ችግር እንደነበረበት ከተሰማ በኋላ በተለያዩ ወገኖች ዘንድ ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቶ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አርዓያ ገብረእግዚዓብሔር «ሰኔ 6 እና 7 የተፈተኑት ፈተና ትክክለኛ ይዘት አለው። ሰኔ 10 እና 12 [የተፈተኑት ፈተናዎች ውጤት] ከመጀመሪያዎቹ ቀናት ሲታይ የመጨመር ባሕሪ ሲያሳይ የተወሰነ ቦታ ላይ ግን ከሚጠበቀው በላይ ጋሽቦ ሔዷል» ብለዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር #ጥላዬ_ጌቴ «መቁረጫ ነጥቡ የት ይሆናል የሚለውን ኤጀንሲው ለተማሪዎች እና ለወላጆች፤ ለዩኒቨርሲቲዎች ግልፅ የሚያደርግ ይሆናል» ብለዋል።

የመንግሥት ባለስልጣናቱ ውሳኔ ቀድሞም ቀውስ ውስጥ በገባው የትምህርት ዘርፍ ተጨማሪ የውዝግብ መነሾ ሆኗል። ለመመዘኛነት አያገለግሉም ተብለው ውድቅ የተደረጉት የፈተና ውጤቶች ችግሮች ምንድናቸው? በፈተና አሰጣጥ ወቅት ምን አይነት ችግሮች ተፈጠሩ? #ተጠያቂውስ ማነው ለሚሉ ጥያቄዎች ባለሥልጣናቱ በግልፅ የሰጡት ማብራሪያ ባይኖርም ጉዳዩ ጠቅላይ ምኒስትሩ በሚመሩት አጣሪ ኮሚቴ ጉዳዩ ይመረመራል ተብሏል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia