TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
“ኢዴፓ #ፈርሷል የተባለው #በውሸት ነው”- አቶ ልደቱ አያሌው
.
.
ኢዴፓ ፈርሷል የተባለው ውሸት መሆኑንና ለኢዴፓ ህጋዊ ዕውቅና የሚሰጠው ምርጫ ቦርድም ኢዴፓ አለመፍረሱን እንደገለጸ አቶ ልደቱ አያሌው ተናገሩ፡፡

አቶ ልደቱ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት በኢዴፓ መፍረስ አለመፍረስ ላይ ምንም ክርክር እንደሌለና ለኢዴፓ ህጋዊ ዕውቅና የሚሰጠው ምርጫ ቦርድም ኢዴፓ አለመፍረሱን እንደገለፀ ተናግረዋል፡፡

ከምርጫ ቦርዱ ምላሽ በኋላ የኛ መልስ አያስፈልግም ያሉት አቶ ልደቱ ፈርሷል የተባለው በውሸት ነው፤ ሊያፈርሰው የሚችለው አካል ጭራሽ አልተሰበሰበም ብለዋል፡፡

#ሊያፈርሰው የሚችለውን አካል ምርጫ ቦርድ ዕገዳ ጥሎበታል፤ ያ ዕገዳ ባልተነሳበት ሁኔታ ከሌላ ጋር መዋሃድም ውሳኔ መስጠት አይቻ ልም፤ ዝም ብሎ ወሬ ነበር፤ ወሬ መሆኑም በሂደት ታይቷልም ነው ያሉት፡፡ እንደ አቶ ልደቱ ገለፃ በዚህ ጉዳይ ላይ የተካሄደ ክርክርም ይሁን ክስም አልነበረም፡፡

መጋቢት 1 ጉባኤ መካሄዱ እና መፍረሱም ሲጠቀስ እንደነበርና ይህ ምን ያህል እውነት እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ልደቱ በመተዳደሪያ ደንባችን መሰረት ጠቅላላ ጉባኤውን የሚጠራው በአንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ13 ነጥብ 4 መሰረት ብሔራዊ ምክር ቤቱ ነው ያሉ ሲሆን ብሔራዊ ምክር ቤቱ ብዙሃኑ ያለው ደግሞ እኛ ጋር ነው፤ እኛ ያልጠራነው ጠቅላላ ጉባኤ ማንም ሊጠራው አይችልም ነው ያሉት፡፡

ብሔራዊ ምክር ቤቱ ላይ ምርጫ ቦርድ ዕገዳ እንደጣለ የጠቀሱት አቶ ልደቱ ያ ዕገዳ ሳይነሳ ማፍረስም ሆነ ማዋሃድ አይቻልም ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"...ጠ/ሚኒስትሩ በተለያየ ግዜ የተናገሩትን በመቁረጥና በመቀጠል የተፈጠረ ሀሰተኛ መረጃ ነው" - የጠ/ሚ ፅ/ቤት

ዛሬ ምሽት መቀመጫነታቸውን ከኢትዮጵያ ውጭ ያደረጉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ጠ/ሚ ዐቢይ በብልፅግና ፓርቲ ስብሰባ ላይ የተነናገሩት ንግግር ሾልኮ ወጣ በሚል አንድ የድምፅ ቅጂ አሰራጭተዋል።

እነዚህ ውጭ ሀገር ያሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ያሰራጩት ምስጥራዊ ነው የተባለው የጠ/ሚ ዐቢይ የድምፅ ቅጂ ፥ "ለ10 ዓመት ማንም ሰው መንግስት መሆን አይችልም ፣ እሞታለሁ እንጂ ስልጣን አልሰጥም ፣ ብዙ እርምጃዎች ይወሰዳሉ ለዚህ የተዘጋጀው ግብረኃይል ስራውን ጀምሯል ፣ ስለዚህም ከፍተኛ የሆነ ፍጅት ደም መፋሰስ ይፈጠራል ፣ ከወዲሁ እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ ምርጫውን አሸንፈናል" የሚሉ እና ሌሎችም ንግግሮች ያሉበት ነው።

ከዚሁ የድምፅ ፋይል ጋር በተያያዘ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ አስተያየት ሰጥቶበታል።

ፅ/ቤቱ ባለፈው ሳምንት በ "ብልጽግና ፓርቲ" ስብሰባ ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተባለ በማስመሰል የተለቀቀው የድምፅ ፋይል #በውሸት የተቀነባበረና ጠ/ሚኒስትሩ በተለያያየ ግዜ የተናገሩትን በመቁረጥ እና በመቀጠል የተፈጠረ ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን አረጋግጣለሁ ብሏል።

ፅ/ቤቱ አክሎም ፥ በዚህ የሀሰት መረጃ ዘመን እና ምርጫው እየተቃረበ ባለበት ወቅት ዜጎች አለመግባባትን ለመፍጠር ያተኮሩ እንደነዚህ ዓይነቶቹ የማሳሳት የመረጃ ዘመቻ ዓይነቶች እንዳይታለል አሳስቧል።

ብልጽግና ፓርቲ ባወጣው መግለጫ፥ ሀሰተኛ መረጃዎች በማሰራጨት የሚታወቁ ሚዲያዎች ሾልኮ የወጣ ብለው የሚያስተላልፉት ድምጽ ሀሰት የሆነ ፣ ከስብሰባው የተወሰደ አንድም ቃል የሌለው፣ የፓርቲው ፕሬዚዳንት በተለያዩ ጊዜያት ካደረጓቸው ንግግሮች የተወሰዱ ቃላትን በመገጣጠም የተቀነባበረ ድምፅ ነው ብሏል።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ🚨

" ማህበረሰቡ ያለበትን #የቤት_እጦት እና ፍላጎት በመገንዘብ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከኢትዮ - ቴሌኮም ጋር በመተባበር 100 ሚሊዮን ብር መድቦ እየሰራ ነው " እየተባለ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጨው መረጃ ፍጹም #ሀሰተኛ ነው።

በማህበራዊ ሚዲያው የሚዘዋወረው መልዕክት አጭበርባሪዎች ህብረተሰቡን #ለማጭበርበር የፈጠሩት ነው።

" ሼር ብቻ እያደረጋችሁ የቤት ባለዕድለኛ ሆኑ ፣ ተሸለሙ " የሚሉት መልዕክቶች በሁለቱም ተቋማት እውቅና የሌላቸው የአጭበርባሪዎች ስራ ናቸው።

" ቤት ታገኛላችሁ ሼር አድርጉ " እንዲህ የሚባል ነገር የለም።

ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦቻችን ፤ መሰል #በውሸት የተሞሉ የማጭበርበሪያ ስልቶችን እንድትጠነቀቁ ከዚህ ቀደም በዛ ያሉ መልዕክቶች ተለዋውጠናል ፤ በቂ እውቀትም አላችሁ።

ምናልባት እንዲህ ያለን ሀሰተኛ መልዕክት አምኖ የሚጭበረበር ወዳጅ ዘመንድ እንዳይኖራችሁ አስገንዝቧቸው።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia