TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Oromia

ኦሮሚያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የሀገር ውስጥ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በችግር ላይ ላሉ ወገኖች አስቸኳይ የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲደረግላቸው የጋራ ጥሪ አቅርበዋል።

በአጠቃላይ 12 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በኦሮሚያ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ አውጥተዋል።

በመግለጫቸው፤ በኦሮሚያ እየተከሰተ ያለውን የሰብዓዊ ቀውስ ለመፍታት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትኩረት እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

" በድርቅ እና ግጭቶች ከ14 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል " ያሉት ድርጅቶቹ " ከነዚህ መካከል በግጭቶች እና በድርቅ ሳቢያ #የተፈናቀሉ 3.4 ሚሊዮን ያህል ሰዎች ይገኙበታል " ሲሉ ገልጸዋል።

የሰብዓዊ ድጋፍ አጋር ድርጅቶች በክልሉ ያለውን ሰብዓዊ ሁኔታ በዝርዝር እንዲገመግሙ እና ለድንገተኛ ሰብዓዊ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ የሰብዓዊ ድጋፍ ፈንድ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

" የውስጥ ተፈናቃዮች የመጠለያ፣ የንፅህና አገልግሎት፣ የምግብ፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎት ያስፈልጋቸዋል " ያሉት ድርጅቶቹ ፤ በኦሮሚያ በአጠቃላይ ከ3.7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አስቸኳይ የውሃ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አመላክተዋል።

እነዚሁ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ #በቦረና በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ሳቢያ በአንዳንድ አካባቢዎች ለ5 ተከታታይ የዝናብ ወቅቶች ዝናብ ባለመዝናቡ 46 በመቶ የሚሆኑት የቀንድ ከብቶች እንዲጠፉ ምክንያት እንደሆነና በርካታ አባወራዎች ሁሉንም ያላቸውን ከብቶች እንዳጡ ጠቁመዋል።

ድርጅቶቹ፤ በተለይ በቦረና ዞን ከዚህ ቀደም በታሪክ ታይቶ አይታወቅም ባሉት ድርቅ ምክንያት የህዝቡ ሁኔታ አሁን ላይ ወደ ለህይወት ወደሚያሰጋ ደረጃ ተቀይሯል ሲሉ አሳውቀዋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

Pic. Jawar Mohammed

@tikvahethiopia