TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች እና አባላት ከጥቂት ቀናት በኋላ ወደ ሀገር ቤት ይገባሉ። ለንቅናቄው አመራሮች የመጀመሪያው አቀባበል እና ዝግጅት የሚደረገው በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲሆን ሌላኛው ዝግጅት የሚከናወነው ደግሞ በሚሊኒየም አዳራሽ መኾኑ ታውቋል።

በተጨማሪ⬇️

#በባሕር_ዳር#በአርባምንጭ#በጎንደር#በሃዋሳ እና በሌሎች በርካታ ከተሞች ከንቅናቄው አባላትና ደጋፊዎች ጋር ሰፊ ሕዝባዊ መድረኮች ይዘጋጃሉ ተብሏል።

©ናትናኤል መኮንን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ #ብናልፍ_አንዱዓለም እንደገለጹት ብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት #በባሕር_ዳር ከተማ ያካሂዳል፡፡

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መስከረም 30 ከኬንያ አቻው ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ #በባሕር_ዳር ዝግጅት ያደረገ ነው፡፡ የብሄራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ ኬንያ ጋናን አሸነፋ ለውድድር የቀረበች ቡድን በመሆኗ ብርቱ ፉክክር ይጠብቀናል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ የመንግስት ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ስድስተኛው ዓለም አቀፍ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዕድገት ላይ የሚያጠነጥን ጉባኤ #በባሕር_ዳር ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹በማረፊያ ቤት ቆይታችን #ሰብዓ_መብታችንን እና #ክብራችንን የሚነካ ድርጊት #ተፈጽሞብናል›› አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ



አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ ‹‹በማረፊያ ቤት ቆይታችን ሰብዓዊ መብታችንን እና ክብራችንን የሚነካ ድርጊት ተፈጽሞብናል›› ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ቅሬታ አቀረቡ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ካለባቸው የጤና ችግር አንጻር በጥንቃቄ የተዘጋጀ ምግብ እንደሚመገቡ ገልጸው፤ ይሁንና በማረፊያ ቤቱ ምግብ በአግባቡ እና በሰዓቱ እንደማይቀርብላቸው ተናግረዋል፡፡ ለአብነትም ትናንት ምሳ በ10፡00 እንደቀረበላቸው ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የሰብአዊ መብት አያያዛቸው እንዲከበርም ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

የኢኮኖሚ ችግር እንዳለባቸው እና ጡረታ በአግባቡ እንደማይወስዱም ነው ተጠርጣሪዎቹ የገለጹት፡፡ በባሕር ዳር ቤት እና ዘመድ ስለሌለን ቤተሰቦቻችን ከአዲስ አበባ ተመላልሰው ምግብ ለማብሰልም ሆነ ለማገዘ አይመቻቸውም ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪ በማረፊያ ጣቢያው ዙሪያ #የተሰበሰቡ ወጣቶች ‹‹ወንጀለኛ፣ ሌባ እና ነብሰ ገዳይ በማለት #ክብራችንን እና ህገ መንግስታዊ መብታችንን የሚነካ ድርጊት ፈጽመውብናል:: በከተማዋ ያለው ድባብ ለደህንነታችን እና ጉዳያችንን በደንብ ተከታትሎ ለመከራከር እክል ይፈጥራል፤ ስለሆነም የክርክሩ ጉዳይ አዲስ አበባ ይታይልን›› ሲሉ ለችሎቱ አቅርበዋል፡፡ ችሎቱም የተጠረጠሩበት ወንጀል የተፈጸመው በአማራ ክልል በመሆኑ የተጠርጣሪዎቹን ጥያቄ ውድቅ አድርጎ ጉዳያቸውን በባሕር ዳር ሆነው እንዲከራከሩ ወስኗል፡፡

‹‹የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እና አመራሮች ወንጀለኛነታችን ሳይረጋገጥ ጉዳዩን በማራገብ የደቦ ፍርድ እንዲደርስብን አድርገዋል›› ብለዋል፡፡ ለአብነትም አቶ በረከት በደብረ ማርቆስ ከተማ በወጣቱ የደረሰውን ሁከት እና ግርግር አንስተዋል፡፡

ጉዳዩን ያየው የባሕር ዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስፈላጊው ጥበቃ እና ክትትል ለተጠርጣሪዎቹ እየተደረገላቸው #በባሕር_ዳር_ማረፊ_ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ በመወሰን የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር ማረሚያ ቤት‼️

#በባሕር_ዳር ማረሚያ ቤት በተከሰተ የፀጥታ ችግር የሰው ሕይወት ማለፉንና ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ማረሚያ ቤት ኃላፊ ኮማንደር ውብሸት መኮንን ለአብመድ እንደተናገሩት የፀጥታ ችግሩ የተከሰተው ትናንት ከቀኑ 7፡00 አካባቢ ነው፤ የችግሩ ምክንያት ደግሞ ‹‹አደንዛዥ ዕፅ እና ሞባይል ወደ ማረሚያ ቤቱ ገብቷል›› የሚል ጥቆማ ለማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች ደርሷቸው ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ታራሚዎች ውስጥ ለፍተሻ በገቡበት ወቅት የማፈን ሙከራ በመደረጉ ነው፡፡

ወደ ታራሚዎች የገቡትን 6 የፖሊስ አባላትን ለማፈን ጥረት መደረጉና አምስቱ ከመታፈን ማምለጣቸውን የገለጹት ኃላፊ ‹‹አንደኛው የፖሊስ አባል ግን በታራሚዎች በመታፈኑ እንዲለቁት ድርድር ቢደረግም ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ይህንን ተከትሎ ታራሚዎች ወደ ፖሊሶች ድንጋይ መወርወር እና ጉዳት ማድረስ በመጀመራቸው የአድማ ብተና ፖሊሶችን እገዛ በመጠየቅ በአስለቃሽ ጋዝ ለማስለቀቅ እና ለማረጋጋት ጥረት ተደርጎ ነበር›› ብለዋል ኮማንደር ውብሸት፡፡

በአመፁ ‹‹አንሳተፍም›› ያሉትን ታራሚዎች አመፅ ቀስቃሾቹ ጉዳት እንዳደረሱባቸውም ኮማንደሩ ተናግረዋል፡፡ እስከዛሬ ጥዋት ባለው መረጃም የአራት ታራሚዎች ሕይወት ማለፉን ኮማንደሩ አረጋግጠዋል፡፡ በመጨረሻም ታፍኖ የነበረው አንድ አባል ትናንት ተለቅቋል፡፡

ቀላል እና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ታራሚዎች ቁጥር በውል ባይታወቅም ከ20 እንደሚበልጡም የማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ለአብመድ አስታውቀዋል፡፡ ተጎጅዎቹ በፈለገ ሕይወት እና በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሎች ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ነግረውናል፡፡

ምንጭ:- አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአዴፓ ሊቀ መንበር አቶ #ደመቀ_መኮንንን የሚመሩት ሕዝባዊ ውይይት #በባሕር_ዳር እየተካሄደ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia