TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

"መታወቂያ አምጡ" በማለት በመሳሪያ በማስፈራራት ዘርፈዋል የተባሉ ሁለት የፖሊስ አባላት ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ረዳት ሳጅን ሬድዋን ሁሴን እና ኮንስታብል ሳሙኤል ድጉማ ይባላሉ።

ሰዎቹ የፖሊስ አባላት / ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 የሐርቡ ፖሊስ ጣቢያ አባል ናቸው።

"ስልጣንን ያለ አግባብ በመገልገል" ወንጀል  ተከሰው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል።

ሌሊት ላይ ለወንጀል መከላከል ሥራ በተሰማሩበት ቦታ ላይ ግለሰብን አግተው #በሽጉጥ_አስፈራርተው ንብረት ወስደዋል ነው የተባለው።

የክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወንጀል መርማሪ እንዳለው ፥ ተጠርጣሪዎቹ ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ሌሊት በወንጀል መከላከል ሥራ ላይ ተመድበው ሲሠሩ መንገድ ላይ ያገኙዋቸውን አንድ የግል ተበዳይ " መታወቂያ አምጡ " በማለት ፖሊስ ጣቢያ እንደወሚወስዷቸው ገልጸው ግለሰቡ በኪሳቸው የያዙትን ሁለት ዘመናዊ ሞባይሎች በሽጉጥ አስፈራርተው በመደብደብ እንደወሰዱባቸው ገልጿል፡፡

በተጨማሪም ከግለሰቡ የተወሰዱትን ስልኮች 2ኛ ተጠርጣሪ በመኖሪያ ቤቱ በሚተኛበት ፍራሽ ውስጥ ደብቆ መገኘቱን ጠቅሷል።

በዚህም መርማሪ " ስልጣንን ያለ አግባብ መገልገል " ወንጀል ለተጨማሪ ምርመራ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።

ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው ድርጊቱን አለመፈጸማቸውን ገልጸው ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ምርመራው ሳይጠናቀቅ በዋስ ቢወጡ የግል ተበዳዩን ሊያስፈራሩ ይችላሉ በማለት የዋስትና ጥያቄውን ተቃውሟል።

ግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤት የ7 ቀን የምርመራ ማጠናቀቂያ ጊዜ ለመርማሪ ፖሊስ ፈቅዷል።

#AddisAbaba #FBC #JournalistTarikAdugna

@tikvahethiopia