#update ፌደራል ፖሊስ⬇️
ለኦነግ አባላትና አመራር በአዲስ አበባ የተዘጋጀው የአቀባበል ስነስርዓት #ያለአንዳች ችግር መጠናቀቁን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል አስታወቁ።
ኮሚሸነሩ ከfbc ጋር ባደረጉት ቆይታ በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የሀገር መከላከያ፣ የኦሮሚያ ፖሊስ፣ የፌደራል ፖሊስ እና ደህንነት የተጠናከረ ጥበቃ ሲያደርጉ መቆየታቸውንም አንስተዋል።
በአቀባበል ስነስርቱ ላይ ከአራት ሚሊየን (4,000,000) #በላይ ህዝብ የተገኘ ሲሆን፥ የህዝቡን ሰላም በጠበቀ መልኩ #በሰላም መጠናቀቁን ገልጸዋል።
በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ የተገኙ #ወጣቶችም ከፖሊስ ጋር #ትብብር ሲያደርጉ መቆየታቸውን ያነሱት ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ #ጸጥታውን ለማስከበርም በጋር ሲፈትሹ እንደነበረም ጠቅሰዋል።
በዚህም #ቄሮዎችን ያመሰገኑ ሲሆን፥ ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ተግባር መፈጸማቸውን ጠቅሰዋል።
የአዲስ አበባ ወጣትም የአቀባበል ስነስርዓቱ መጠናቀቅን ተከትሎ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚመለሱ ወጣቶችን #ምግብና ውሃ በማዘጋጀት ግብዣ ሲያካሂድ እንደነበረ ገልጸዋል።
ኮሚሽነሩ ይህ #አንድነትን ይበልጥ የሚያጠናክርና ለሀገሪቱም ትልቅ #ተስፋ መሆኑን አንስተዋል።
አንዳንድ ቦታዎች ላይ "ወጣት ነን" የሚሉ ግለሰቦች #ድንጋይ የመወርወር አዝማሚያ ማሳየታቸውን የጠቀሱ ሲሆን፥ ፖሊስም #በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ተናግረዋል።
በተመሳሳይ በአዲስ አበባ #ዙሪያ በቄሮ ስም #የሚነግዱ ቄሮ ያልሆኑ ከአቀባበል ስነ ስርዓቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ግለሰቦች ዝርፊያና #ግድያ መፈጸማቸውን አንስተዋል።
በዚህም ፌደራል ፖሊስ፣ የኦሮሚያ ፖሊስ እና የሀገር መከላከያ ወደ አካባቢው በመሄድ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር እያዋለ ይገኛል ብለዋል።
በጥቅሉ አቀባበሉ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የታየበት ጥሩ መንፈስ የነፈሰበት ህዝቡ እንግዶቹን ተቀብሎ በሰላም እንዲጠናቀቅ ያደረገበት ነው ብለዋል።
የአቀባበል ስነስርዓቱ በሰላም መጠናቀቅ ህዝቡ ላደረገው ትብብር፣ ለቄሮ እና ለአዲስ አበባ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል።
በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ የነበሩ ቄሮዎች ባሳዩት ትብብር ፖሊስ መኩራቱን ገልጸው በቀጣይም ፖሊስ ጋር በመሆን እጅና ጓንት ሆነው እንደሚሰሩ እምነታቸውን ገልፀዋል።
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️
በአዲስ አበባ ከተማ የተከበረው #123ኛው የአድዋ ድል በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር #በሰላም መጠናቀቁን የከተማ ፓሊስ ኮሚሽን እስታወቀ። የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ በሚኒልክ አደባባይ እና በመስቀል አደባባይ በደማቅ ስነ ስርዓት የተከበረው የድል በዓል ሰላማዊ ሆነ መጠናቀቁን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
በዛሬው ዕለት በከፍተኛ ሁኔታ የተከበረው 123ኛው የአድዋ ድል በዓል ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ ሰላማዊ እንደነበረ አንስተዋል፡፡ ይህ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ሚና ለነበራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች እና ለሁሉም የፀጥታ አካላት በኮሚሽኑ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር #ታከለ_ኡማ በዓሉ በደማቅ ሁኔታ እንዲከበርና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ላስቻሉ ሁሉም አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ምንጭ፦ fbc

አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን!
#1440ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል #በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሰታወቀ። በአል በሰላም እንዲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት፣ ከእምነቱ አባቶችና ከበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ጋር ውይይት እንደተካሄደና ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ወደ ስራው የተገባ መሆኑ ፓሊስ አስታውቋል፡፡
በዚህ መሰረትም ምዕመኑ ለኢድ-ሶላት በሰላም ወጥቶ በሠላም እንዲገባ በዋና ዋና መንገዶች በተለይም በአዲስ አበባ ስታድየም እና በዙሪያው ከበዓሉ አስተባባሪ ወጣቶች ጋር በመቀናጀት ጠንካራ የፀጥታ ሰራ ተከናውኗል፡፡ ለስራው ስኬታማነት የእምነቱ ተከታዮች ላሳዩት ቀና ትብብር የአዲስ አበባ ፖሊሰ ኮሚሽን ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
Via #FBC

TIKVAH-ETHIOPIA
#HappeningNow በአሁን ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ህወሓትን እና ሸኔን የሚያወግዝ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ነው። በሰልፉ ላይ የውጭ ሀገር ጣልቃ ገብነትንና የውጭ ሀገር መገነኛ ብዙሃንን አጥብቀው የሚተቹ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ የተፃፉ የተለያዩ መፈክሮች በሰልፈኞች ተይዘዋል። ሰልፈኞች ካያዟቸው መፈክሮች መካከል ፦ - የአሜሪካ…
#Update
" ሰልፉ በሰላም ተጠናቋል " - የአዲስ አበባ ፖሊስ
በመስቀል አደባባይና በዙሪያው የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ #በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ፕሮግራሙ በሰላም እንዲጠናቀቅ የከተማው ነዋሪ በተለይ ደግሞ የሰላማዊ ሰልፉ ታዳሚዎች ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ተገቢውን ትብብር በማድረጋቸው ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል።
በተጨማሪ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ ላሉ የፀጥታ አካላት እንዲሁም ሰልፉን ላስተባበሩ እና ለመሩ አካላት በሙሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል።
@tikvahethiopia

#AU ኮሞሮስ የ2023 የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበርነትን #ከሴኔጋል በይፋ ተረክባለች። 36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተጀምሯል። በጉባዔው መክፈቻ መርሐግብር የወቅቱ የሕብረቱ ሊቀ መንበር ሴኔጋል ለኮሞሮስ ሊቀ መንበርነቷን በይፋ አስረክባለች። የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ ከፕሬዜዳንት ማኪ ሳል የሊቀመንበርነቱን ቦታ የተረከቡ ሲሆን 2023ን የህብረቱ…
#AU #ETHIOPIA
የ36ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ትላንት ቅዳሜ እንዲሁም ዛሬ እሁድ ተደርጎ ተጠናቋል።
ይህን ተከትሎ የጉባኤው ተሳታፊ ሀገራት መሪዎች ወደ አገራቸው መመለስ ጀምረዋል።
እስካሁን የበርካታ ሀገራት መሪዎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
እስካሁን ድረስ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱት መካከል ፦
- የጋና፣
- የሞዛምቢክ፣
- የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣
- የኬኒያ፣
- የሩዋንዳ፣
- የሞሮኮ፣
- የማዳጋስካር ፣
- የኡጋንዳ፣
- የዚምባብዌ ፣
- አንጎላ ፣
- ደቡብ አፍሪካ ፣
- ኮንጎ ብራዛቢል፣
- ቻድ እንዲሁም የሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ መሪዎች ይጠቀሳሉ።
የተመድ ዋና ፀሀፊት አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ ሌሎችም የጉባኤው ተካፋዮች ተሸኝተዋል።
መሪዎቹ ትላንትናና ዛሬ በአዲስ አበባ በተካሄደው ጉባኤ ላይ ከመሳተፍ ባለፈ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን አድርገዋል።
በሌላ በኩል የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ #በሰላም መጠናቀቁን ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉባኤው በሰላም እንዲጠናቀቅ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

#አሁን " ኢፍጣራችን ለወገናችን " በሚል መሪ ቃል የዘንድሮው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ስነስርዓት በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በዚሁ ዝግጅት ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን ተገኝቶ ስነስርዓቱን እየታደመ ነው። @tikvahethiopia
#AddisAbaba
የዘንድሮው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ስነስርዓት በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ።
የዘንድሮው ኢፍጧር ስነስርዓት " ኢፍጧራችን ለወገናችን " በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን እጅግ ከፍተኛ የሆነ ምዕመን ስነስርዓቱን ታድሟል።
በሌላ በኩል ፥ የአዲስ አበባ ፖሊስ የኢፍጧር ፕሮግራሙ #በሰላም_መጠናቀቁን አሳውቋል።
ለፕሮግራሙ በሰላም መጠናቀቅ የከተማው ነዋሪ በተለይም የሙስሊሙ ማህበረሰብ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ተገቢውን ትብብር ማድረጉን ፖሊስ ገልጿል።
ለኘሮግራሙ ሠላማዊነት የድርሻቸውን ላበረከቱ እና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታ አካላት ምስጋና አቅርቧል።
Photo : Mayor Office & Addis TV