TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጅግጅጋ🔝

የስምንተኛው #የኢትዮጵያ_ከተሞች_ፎረም የማጠቃለያ ፕሮግራም ጅግጅጋ በሚገኘው የሱማሌ ክልል ቤተመንግስት አዳራሽ ተጀምሯል። በማጠቃለያው ልዩ ልዩ #ሽልማቶች በተለያዩ ዘርፎች የሚሰጡ ሲሆን #የዘጠነኛው_ፎረም አዘጋጅ ከተማም የሚታወቅ ይሆናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
5ሺ ዶላር የሚየሸልም ውድድር ይፋ ተደረገ!

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 5ሺ የአሜሪካን ዶላር የሚያሸልም ውድድር ይፋ አደረገ። ሚኒስቴሩ ከአይቢኤ ኢትዮጲያ ከተሰኘ የግል ኩባንያ ጋር በመተባበር አህጉራዊ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ንቅናቄ ‹‹አፍሪካ ኢኖቬሽን ሳምንት›› በሚል ከጥቅምት 17 እስከ ጥቅምት 22ቀን 2012 ድረስ በአዲስ አበባ አካሂዳለሁ ብሏል፡፡

ስለሆነም ችግር ፈቺ፤ ሀብት ፈጣሪና ወደ ምርትና አገልግሎት ሊቀየር የሚችል የፈጠራ ስራ ያላችሁ በዚህ አህጉራዊ መድረክ ላይ ሀገራችሁን ወክላችሁ እንድትወዳደሩና የፈጠራ ውጤቶቻችሁን ለውጭና ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች፤ ለቬንቸር ካፒታል ተቋማት እና ለሌሎች የፋይናስ ምንጮች በማስተዋወቅ ወደ ምርትና አገልግሎት እንድትቀላቀሉ ይጋብዛል፡፡ በዚህ ውድድር አሸናፊ የሆኑ አምስት ከፍተኛ የፈጠራ ወይም የምርምር ስራዎች እያንዳንዳቸው 5ሺ የአሜሪካን ዶላር ተሸላሚ ይሆናሉ ተብሏል፡፡

ሌሎችም ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ #ሽልማቶች እንደሚበረከትላቸው በተገለጸው በዚህ ውድድር ላይ ለመካፈል ዘመናዊ ከተሞች እና አዳዲስ የመኖሪያ ቴክኖሎጂዎች፤ ዲጂታላይዜሽን፤ የኢንተርኔት ንግድ ስርዓት፤ የግብርና፤ የጤናና የህክምና ቴክኖሎጂ፤ መስተንግዶና ቱሪዝም፤ የማምረቻና እና የማዕድን ኢንደስትሪ አመልካቾች የፈጠራ ስራ ፕሮፖዛላችሁን ስከ መስከረም 16ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብላችኋል።

በዚህ ውድድር ላይ የመወዳደሪያ ሀሳባችሁን [email protected] ላይ በመላክ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል።

Via #ETHIO_FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia