TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጨፌ ኦሮሚያ በዛሬ ውሎው የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (ኦቢኤን) ዋና ዳርዬክተር እና የቦርድ አባላት #ሹመትን አፅድቋል።

በዚህም መሰረት፦

1. ጋዜጠኛ #መሃመድ_አደሞ፦ የኦቢኤን ዋና ዳይሬክተር

2. አቶ ሽመልስ አብዲሳ፦ የኦቢኤን ቦርድ ሰብሳቢ

3. ወይዘሮ ሌሊሴ ነሜ፦ የኦቢኤን የኦርድ አባል

4. ዶክተር ደረጄ ገረፋ፦ የኦቢኤን የኦርድ አባል

5. አቶ አድማሱ ዳምጠው፦ የኦቢኤን የኦርድ አባል

6. ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ

7. ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና፦ የኦቢኤን የኦርድ አባል

8. ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ፦ የኦቢኤን የኦርድ አባል በመሆን ተሹመዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የወላይታ ዞን ምክር ቤት‼️

የወላይታ ዞን ምክር ቤት ትላንት በጀመረው 4ኛ ዙር 6ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የዋናና ምክትል አፈ ጉባኤ #ሹመትን አጸደቀ፡፡

ምክር ቤቱ ወይዘሮ አበበች ኢራሾን የዞኑ ዋና አፈ ጉባኤና ወይዘሮ ዝናሽ በየነን  ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሾሟል።

ምክር ቤቱ ነባር አመራሮት ወደ ከፍተኛ ትምህርተ ቤት መግባታቸውን ተከተሎ ሹመቱን መስጠቱንና አዲስ አመራሮቹ የለውጡን ሂደት አጠናክሮ ለማስቀጠል ብቃት ያላቸው ስለመሆናቸው በወቅቱ ተገልጿል።

ጉባኤው ዛሬም ቀጥሎ የምክር ቤቱ 4ኛ ዙር 6ኛ የሥራ ዘመን አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤን እንዲሁም የ2010 አፈጻጸም ሪፖርት ለውይይት ቀርቦ እንደሚጸድቅ ተመልክቷል።

በተመሳሳይ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎችና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2010 ዕቅድ አፈጻጻም ሪፖርት ቀርቦ የሚጸድቅ ሲሆን የተጓደሉ የቋሚ ኮሚቴዎች አባላት የሟማያ ምርጫም እንደሚካሄድ ታውቋል ።

የወላይታ ብሔር የክልል እንሁን ጥያቄ ለምክር ቤቱ እንደሚቀርብና የዞኑ ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ የተለያዩ ሹመቶች እንደሚሰጡም ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ🔝

ከወርሃ ጥር ጀምሮ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራርና አስተዳደደር ሃላፊዎች #ሹመትን አስመልክቶ የወጣውን መመሪያ ተከትሎ የፕሬዝዳንት አፈላላጊ ኮሚቴ በመሰየም ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዝዳንት አፈላላጊ ኮሚቴም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራርና አስተዳደደር ሃላፊዎችን ምርጫና ሹመት/ምደባ አስመልክቶ የወጣውን መመሪያ ቁጥር 002/2011 ተግባራዊ በማደረግ ሃላፊነቱን በብቃት ሲወጣ ቆይቷል፡፡

በምልመላ እና መረጣ ሂደት ውስጥ በመስፈርትነት የተቀመጡ የትምህርት ዝግጅት፣ የአመራር ልምድ፣ በማስተማር እና በምርምር የተገኘ ልምድን መሰረት በማድረግ ከቀረቡ አሰር ዕጩዎች ተገቢውን መስፈርት የሚያሟሉ ስምንት ተወዳዳሪዎችን ለስትራቴጂክ ዕቅድ ገለጻ ኮሚቴው በመምረጥ ለውድድር አቅርቧል፡፡

ዕጩ ተወዳዳሪዎቹም የቦርድ አመራሮች፣ የሴኔት መማክርት አባላት፣የማኔጅመንት ሃላፊዎች፣በተቋሙ ከሚገኙ ከሁሉም የአካዳሚክ ዘርፎች እና የአስተዳዳር ክፍሎች የተወጣጡ የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ስትራቴጂክ እቅዳቸውን ማቅረብ ችለዋል፡፡

በተሰጣቸው አስራ አምስት ደቂቃ ስትራቴጅክ ዕቅዳቸውን በማቅረብ፣ ከተሳታፊ ለሚነሳላቸው ጥያቄ ለአስራ አመስት ተጨማሪ ደቂቃ ማብራሪያ እንዲሰጡ ተደርጎ በሚስጥራዊ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ዕጩ #ተወዳዳሪዎች ድምጽ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

በምርጫው ሂደት ከተሳተፉ ስምንት ዕጩዎች አምስቱ ተለይተው ለቀጣዩ ሂደት ለዩኒቨርሲቲው ቦርድ የቀረቡ ሲሆን፤መስፈርቱን በማሟላት ከአንድ እስከ አምስት የወጡ ጩዎች ይፋ ተደርገዋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1. ዶ/ር ታከለ ታደሰ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) 88.33 በማምጣት 1ኛ
2. ዶ/ር አብርሃም አላኖ(ተባባሪ ፕሮፌሰር) 77.7 በማምጣት 2ኛ
3. ዶ/ር ሰለሞን ለማ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) 72.94 በማምጣት 3ኛ
4. ዶ/ር ወንድሙ ወልዴ( ረዳት ፕሮፌሰር) 70.37 በማምጣት 4ኛ
5. ዶ/ር መስፍን ቢቢሶ(ተባባሪ ፕሮፌሰር) 66.78 በማምጣት 5ኛ ደረጃን የያዙ ሲሆን በአሰራሩ መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራርና አስተዳደደር #ሃላፊዎች ሹመትን አስመልክቶ የወጣውን መመሪያ በሚደነግገው መሰረት #የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ከሚቀርቡለት አምስት ዕጩዎች ሶስቱን ለይቶ ለትምህርት ሚኒስቴር እንሚልክ ተጠቁሟል፡፡

የውድድር ሂደቱ ፍጹም #ሠላማዊ እንደነበር እና መመሪያና ደንቡ በሚፈቅደው ልክ ግልጽ አሰራርን ተከትሎ ተግባራዊ መደረጉን የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር #ቶላ_በሪሶ ገልጸዋል ሲል የዘገበው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚኒዩኬሽንና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia