#AddisAbaba
" ከቅጣት በኋላ ካላስተካከሉ የማሸግ እንዲሁም ከዚህ አለፍ ሲል ከዘርፉ እስከማሰናበት እርምጃ ይወሰዳል " - በአ/አ ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ
በአዲስ አበባ የሚገኙ ሆቴሎች እና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተጋጆቻቸውን " የተራቆተ " ልብስ የሚያስለብሱ ከሆነ ከ50 ሺህ ብር እስከ #እገዳ የሚደርስ ቅጣት የሚጥል ረቂቅ መዘጋጀቱ ታውቋል።
የረቂቁ ስያሜ ፦ " በሆቴል እና መሰል አገልግሎቶች ሰጪ ተቋማት የሚሠሩ ባለሙያዎች የደንብ ልብስ አለባበስ፣ የጌጣ ጌጥ እና የመዋቢያ አጠቃቀም ደንብ " ይሰኛል።
የተዘጋጀው ፦ በአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ነው።
በተለይም እንደ #ሥጋ_ቤቶች ባሉ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ በታየው የአስተናጋጆች " የተራቆተ አለባበስ " ምክንያት ረቂቁ ተዘጋጅቷል።
ረቂቁ ምን ያላል ?
- ከመስተንግዶ ስነምግባር እና ከሀገሪቱ ባህል የወጣ አለባበስ ይከለክላል።
- አስተናጋጆች ከባህል፣ ከጨዋነት ያፈነገጠ እና የተራቆተ አለባበስ እንዳይኖራቸው ይከለክላል።
- አስተናጋጆች #በሚታይ የሰውነት አካል ላይ ንቅሳት እንዳይኖራቸው ይከለክላል።
- #ወንዶች በምንም ተአምር ጆሮ ጌጥ አድርገው እንዳያስተናግዱ አይፈቀድም።
- የተቋማቱ ሠራተኞች ከሸሚዝ በላይ የሚሆን የአንገት ጌጥ እንዲሁም የእጅ ጌጥ እንዳይጠቀሙ ይከለክላል።
- ከጌጣ ጌጥ ጋር ተያይዞ ለሴቶች ጆሮ ጌጥ ይፈቀዳል። ነገር ግን ወደታች ያልወረደ እዚያው ላይ ልጥፍ የሚል መሆን አለበት። በተለይ በጆሮ ዙሪያ ላይ የሚደረግ ጆሮ ጌጥ አይፈቀድም።
- በሚታዩ የሰውነት አካላት ላይ . . . ምንም ዓይነት ንቅሳትም ሆነ ሌላም በሥዕል ተጠቅሞ ማስተናገድ አይቻልም። ይሁንና ከንቅሳት ጋር በተያየዘ የሚነሱ የባህል ጉዳዮች የደንቡን መጽደቅ ተከትሎ በሚወጣ መመሪያ ይታያል።
- ከአለባበስ፣ በሚታዩ የሰውነት አካላት ላይ ከሚደረጉ የጌጣ ጌጦች አጠቃቀም በተጨማሪ የፀጉር አያያዝን እንዲሁም የሚጠቀሟቸው ሽቶዎች መጠንን ላይ ገደብ ተቀምጧል።
ክልከላው እነማንን ይመለከታል ?
ሁሉንም ሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪዎችን ይመለከታል።
* ሆቴሎች፣
* ካፍቴሪያዎች፣
* ምሽት ቤቶች፣
* ማሳጅ ቤቶች፣
* ጂሞች
* የስቲም እና ሳውና አገልግሎት ሰጪዎች ክልከላው ከሚመለከታቸው ውስጥ ናቸው።
ቅጣትን በተመለከተ ረቂቅ ደንቡ ምን ይላል ?
ደንቡ ላይ የተቀመጠውን ድንጋጌ የሚተላለፉ ፦
☑ በ15 ቀናት ውስጥ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል።
☑ በ15 ቀን ጊዜ ውስጥ ማስተካከያ ያማያደርጉ ከሆነ የ50 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።
☑ ከቅጣት በኋላም ካላስተካከለ የማሸግ እርምጃ ይወሰዳል። ከዚህ አለፍ ሲልም ከዘርፉ እስከማሰናበት እርምጃ ይወሰዳል።
መቼ ተግባራዊ ይደረጋል ?
ደንቡ ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው ለአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ቀርቦ ከጸደቀ በኋላ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ማግኘቱን ይገልጻል።
@tikvahethiopia