TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሜቴክ⬇️

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን የከተማውን የትራንስፖርት እጥረት ለማቃለል ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ትዕዛዝ ከሰጣቸው 850 አውቶብሶች 700ዎቹን እስካሁን እንዳልተረከበ ተሰምቷል። ለአውቶብሶቹ 3.4 ቢሊዮን ብር #ተከፍሏል ነው የተባለው፡፡

የባለስልጣን መ/ቤቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ ወ/ሮ እፀገነት አበበ ዛሬ ለሸገር FM 102.1 ሲናገሩ፣ ከሜቴክ ጋር የአውቶብሶቹን ስራ ውል የገባነው በሰኔ ወር 2009 ዓ/ም ሲሆን አውቶብሶቹን መረከብ የነበረብን ሰኔ 2010 ነበር ብለዋል፡፡

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አውቶብሶቹን በቃሌ መሰረት ያላስረከብኩት በውጪ ምንዛሬ ችግር ነው ብሎናል ያሉት ወ/ሮ እፀገነት ከዚህ ወር ጀምሮ ግን ቀስ በቀስ ቀሪ 700 አውቶብሶቹን ሊያስረክበን ቃል ገብቶልናል ብለዋል፡፡

#ሜቴክ ለአውቶብሶቹ መስሪያ የሚያስፈልገውን እቃዎች አስቀድሞ ገዝቷል፣ በተባለው ጊዜም ያደርስልናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ሲሉ ወ/
ሮ እፀገነት ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሜቴክ ስሙን ሊቀይር ነው⬇️

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ወታደራዊ ምርት የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎችን ለመከላከያ ሚኒስቴር በማስረከብ በአዲስ ስያሜ ሊደራጅ ነው።

ከተቋቋመ ጀምሮ በጥቂት ጊዜ በርካታ የመንግስት ፕሮጀክቶችን እንዲይዝ ተደርጎ የነበረው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ከብቃት፣ እጦትና ከብክነት ጋር ተያያዘ ስሙ ሲነሳ ቆይቷል።

እጁ ላይ የነበሩ በርካታ የስኳር ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ አቅቶት ፕሮጀክቶቹን ሲቀማ፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሃይድሮ መካኒካል ስራዎችን ወስዶ መስራት ባለመቻሉም ቢሊየን ብሮች እንደባከኑ ተሰምቷል።

ከዚህ ሁሉ በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስተዳደር የኮርፖሬሽኑን አመራሮች ከመቀየር አንስቶ የተለያዩ እርምጃዎች እንዲወሰድበት እያደረገ ነው።

የኮርፖሬሽኑ የኮመርሻልና ሲቪል ምርቶች ኦፕሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ #አብዱልዓዚዝ_መሀመድ ለfbc፥ አሁን በመንግስት የተወሰደው እርምጃ የኮርፖሬሽኑን አደረጃጀት ማስተካከል ነው።

ይህም በሜቴክ ስር ወታደራዊ ምርቶችን ሲያመርቱ የነበሩ ኢንዱስትሪዎችን ለመከላከያ ሚኒስቴር በመስጠት ቀሪዎችን በስሩ የሚያስቀጥል መሆኑንም ይናገራሉ።

በዚህ መሰረት ሜቴክ አዲሱን ስያሜ ይዞ የሲቪልና የንግድ ምርቶችን ብቻ የሚያመርት ሲሆን፥ የብሄራዊ ብረታ ብረት ምህንድስና ኮርፖሬሽን የሚል አዲስ ስያሜ ሊሰጠው እንደታሰበም ተናግረዋል።

ለዚህ አዲስ አደረጃጀት ረቂቅ ደንብ የተዘጋጀ ሲሆን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ከጸቀደ በኋላ ወደ ትግበራ እንደሚገባም ነው የተናገሩት።

#ሜቴክ እስካሁን 14 ኢንዱስትሪዎችን ሲያስተዳድር የቆየ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ወታደራዊ ምርቶችን የሚያመርቱ አራት ኢንዱስትሪዎችን ለመከላከያ ሚኒስቴር እንዲያስረክብ በመንግስት ተወስኗል።

ሆሚቾ ኢንዱስትሪ፣ ደጀን አቪየሽን፣ ጋፋት አርማመንት እና ልዩ ትጥቆች አምራች ኢንዱስትሪ የተባሉትን ነው ለመከላከያ ሚኒስቴር እንዲያስረክብ የተወሰነው።

ቀሪ ዘጠኝ ኢንዱስትሪዎች በሜቴክ ወይም ወደፊት የብሄራዊ ብረታ ብረት ምህንድስና ኮርፖሬሽን የሚል ስያሜ በሚሰጠው ተቋም ውስጥ የሚተዳደሩ ይሆናል።

ከዚህ ውስጥ ደግሞ ቢሸፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ወታደራዊም የሲቪል ምርቶችንም ስለሚያመርት በማን እጅ መሆን ይኖርበታል የሚለውን ጉዳይ ለማጥናት ኮሚቴ መቋቋሙን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

አዲሱ ኮርፖሬሽንም ሀገሪቱን ወደ ኢንዱስትሪ የሚያንደረድሩ ምርቶች ላይ የሚሰማራ ይሆናል ብለውናል ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ።

የብሄራዊ ብረታ ብረት ምህንድስና ኮርፖሬሽን የሚል ስያሜ አግኝቶ እንዲቋቋም የታሰበው ኮርፖሬሽን የማቋቋሚያ ካፒታሉ እንደሚሻሻልለትም አቶ አብዱልዓዚዝ አንስተዋል።

ሜቴክ ከአመታት በፊት ሲቋቋም በ10 ቢሊየን ብር የተጠየ ካፒታል ነበር፤ ከዚህ ውስጥ የተከፈለው 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ሲሆን፥ አሁን ወታደራዊ ምርት አምራቾቹ ሲቀነሱ የተከፈለ ካፒታሉ ዝቅ ይላል፤ ከዚህ ጋር ተያይዞም ካፒታሉ ይከፈልለታልም ነው ያሉት አቶ አብዱላዚዝ።

አዲሱ ኮርፖሬሽን ከብቃት ማነስና ከብክነት ጸድቶ ለመሄድም እንደበፊቱ ኮርፖሬሽኑ አቅም ሳይኖር ብዙ ስራን ከመውሰድ ይልቅ፥ የተወሰኑ ዘርፎች ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ የሰው ሀይሉን በአግባቡ ለመጠቀም ታስቧል ብለዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ለከተማ ቀላል ባቡር ባቀረባቸው ጥራት የሌላቸው የኤሌክትሪክ ገመዶች ሳቢያ ባቡር ትራንስፖርት እክል ገጥሞታል፡፡ ኢዜአ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ትራንዚት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር #ሙሉቀን_አሠፋን ጠቅሶ እንደዘገበው በገመዶቹ ሳቢያ የባቡር መቆም እና የሃይል መቆራረጥ ተፈጥሯል፡፡ #ሜቴክ የዘረጋቸው መስመሮች 15 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ ሲሆን ከሀያት እስከ ለም ሆቴል እና ከቃሊቲ እስከ መሹዋለኪያ ያለውን ርቀት ይሸፍናሉ፡፡ ቀሪዎቹን የዘረጋው የቱርክ ኩባንያ ነው፡፡

©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሜቴክ

የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በመንግሥት ውሳኔና ኮርፖሬሽኑ በፈጸመው የተሳሳተ አካሄድ 70 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ሲገልፅ፤ 57 ቢሊዮን ብሩን መንግሥት እንዲሰርዝለትና ወደ ካፒታል እንዲቀይርለት ጥያቄ ማቅረቡን አመለከተ። በያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ከዲዛይንና ማስተባበረ ውጭ እንዳልተሳተፈም ገልጿል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሜቴክ ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (#ሜቴክ) የተሰየመው አዲሱ የሥራ አመራር ቦርድ፣ በኮርፖሬሽኑ ያለ ገበያ #ጥናት ተመርተው ገዥ ማግኘት ባለመቻላቸው በአዳማ የእርሻ መሣሪያዎች ኢንዱስትሪ ከስድስት ዓመታት በላይ ተከማችተው የሚገኙ ከአሥር ሺሕ በላይ የሚሆኑ ትራክተሮችና መለዋወጫዎች፤ከተቻለ በርካሽ ዋጋ እንዲሸጡ ካልሆነም ለክልሎች በስጦታ እንዲበረከቱ ውሳኔ ማሳለፉ ተሰምቷል፡፡

Via Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሜቴክ

የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ሜቴክ ቅድመ ክፍያቸው በባከኑ የምርት ትዕዛዞች ምክንያት የ1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ኪሳራ እንደገጠመው ተገለፀ፡፡
ኮርፖሬሽኑ ካሉት 14 ኢንዱስትሪዎች በተሻለና በሙሉ አቅም በምርት ላይ የሚገኙት አራቱ መሆናቸውን የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል አህመድ አምዛ ከFBC ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት ተናግረዋል፡፡ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ በበርካታ ቀውስ ውስጥ የሚገኝ ቢሆንም ተቋሙ በ2011 በጀት ዓመት ከ9 ቢሊየን ብር በላይ ሽያጭ በመፈጸም 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ትርፍ ለማግኘት አቅዶ ነበር፡፡ ነገር ግን ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ከማማትረፍ ይልቅ ኪሳራ ውስጥ እንደገባ ነው የተገለፀው፡፡ ለመክሰሩ ምክንያት ሁሉም ኢንዱስትሪዎች ወደ ምርት አለመግባታቸው አንዱ ቢሆንም በዋነኝነት ግን ቅድመ ክፍያ የተፈጸመባቸው ምርቶች ናቸው ተብሏል።

©FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው ከእስር ተለቀቁ። የቀድሞው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው፤ ከ5 ዓመት ከ4 ወራት እስር በኋላ ዛሬ ከሰዓት ከእስር መፈታታቸውን ጠበቃቸው ለ" ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ በሰጡት ቃል ተናግረዋል። ጠበቃቸው አቶ ሓፍቶም ከሰተ የቀድሞው የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ የተለቀቁት ፤ አብዛኛውን…
ፎቶ ፦ ላለፉት ዓመታት በእስር ላይ የነበሩት እና በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የቀድሞው የ #ሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው ዛሬ መቐለ ገብተዋል።

መቐለ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የፍትህ ሚኒስቴር የሜጄር ጄነራል ክንፈ ዳኘውና የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አብዲ ኢሌ ክስ ተቋርጦ ከእስር የተፈቱት " ለዘላቂ የህዝብ ጥቅም ሲባል ነው " ማለቱ ይታወሳል።

Photo Credit - Demtsi Woyane

@tikvahethiopia