TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ ተደረገ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ አዲስ ታሪፍ ይፋ አድርጓል።

በዚህም በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ በተሰማሩ ሚኒ-ባሶች ፣ ሚዲ-ባስ ታክሲዎችና የከተማ አውቶብሶች ላይ የአገልግሎት ታሪፍ ጭማሪ ተደርጓል።

አዲሱ ታሪፍ ከነገ ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

ጭማሪ በተደረገበት በአዲሱ ታሪፍ ዝቅተኛው 10 ብር ሲሆን ከፍተኛው 65 ብር ገብቷል።

" ቀድሞ አገልግሎት ሲሰጥበት የነበረው የታሪፍ ተመን ከጥቅምት 20 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ አገልግሎት ላይ የዋለ ነበር ፤ ስሌቱም የነዳጅ ጭማሪ ዋጋን ብቻ ታሳቢ ያደረገ ነበር " ሲል ቢሮው ገልጿል።

የአሁን አዲስ ታሪፍ ወቅታዊ የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ እና ሌሎች አስተዳደራዊ ወጪዎችን ያማከለ እንደሆነ አመልክቷል።

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች አዲስ በተሻሻለው ህጋዊ የታሪፍ ተመን ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስቧል።

(የአዲሱ ታሪፍ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
ላይፍቦይ፣ በ AI የታገዘና ቡቹ የተሰኘ የልጆች መምህር ይፋ አደረገ

ዮኒሊቨር ኢትዮጵያ፣ ከታዋቂ ምርቶቹ አንዱ በሆነው ላይፍቦይ ሳሙና አማካኝነት፣ የእጅ መታጠብ ቀንን አስመልክቶ የጤና አጠባበቅ ትምህርቶችን ለልጆች የሚያስተምር ቡቹ የተሰኘ የ AI መምህር ይፋ አድርጓል፡፡  
መምህር ቡቹ፣ በዓይን የማይታዩ ጀርሞችን በላይፍቦይ ሳሙና የመከላከልን ጥቅሞች ጨዋታዎች፣ መዝሙሮች እና መሰል አዝናኝ እንቅስቃሴዎች በመጠቀም ህጻናት እንዲሁም ማኅበረሰቡ አስፈላጊው የንፅህና አጠባበቅ ዕውቀት እንዲኖራቸው ያስችላል።

ተቋሙ፥ "መ” ለ - መታጠብ በሚለው ንቅናቄው ከተለያዩ ሀገራት መንግሥታት እና ከ130 በላይ ተጽእኖ አድራጊዎች በተገኘ ድጋፍ ከ14 ሚሊዮን በላይ ልጆችን ያሳተፈ ሲሆን በኢትዮጵያም ከ10 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ተደራሽ ማድረግ ችሏል፡፡

በባህሪ ለውጥ ላይ የሚያተኩረውና በላይፍቦይ ሳሙና አነሣሽነት እና መሪነት የሚሰጠው የንጽሕና አጠባበቅ ትምህርት፣  እስከ ጥቅምት ወር መጨረሻ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን በመላው ኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ጋር ለመድረስ ያለመ ነው።

ቡቹን ለማግኘት፡ https://lifebouy-handwashing.staging.aircards.io/?mkt=ET

#GHD2024 #Lifebuoy #Lifebuoyet #Buchu
ደሴ አድባሯን አጣች !

ባህታዊ አባ መፍቀሬ ሰብዕ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ፥ " ደሴ አድባሯን አጣች፤ ብዝኅ ሕይዎት ጠባቂያቸውን እና ተንከባካቢያቸውን ተነጠቁ፤ ሊቀ ትጉሀን ባህታዊ አባ መፍቀሬ ሰብዕ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ " ብሏል።

" የሁሉ አባት፣ የሁሉ አለቃ፣ የሁሉ መካሪ፣ የሁሉ ዘካሪ፣ የሀገር ምሰሶ፣ የቤተ ክርስትያን ድምቀት እና የአውደ ምህረት ጌጥ ነበሩ " ሲል ገልጿል።

በ1921 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ተጉለት ወርቅጉር አካባቢ የተወለዱት አባ መፍቀሬ ሰብዕ በ96 ዓመታቸው ነው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት።

አባ በሐይማኖታዊ አስተምኅሮ፣ በብዝኃ ሕይወት ጥበቃ ሥራ እና አንድነነትን በማስተማር ለበርካታ ዓመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ አድባራት አገልግለዋል።

በግሸን ደብረ ከርቤ ለበርካታ ዓመታት ሲያገለግሉ ቆይታዋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba 🛬 #DireDawa

በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET248 ድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፍያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ ሳለ በአውሮፕላኑ ውስጥ #ጢስ መታየቱን አየር መንገዱ አሳውቋል።

አውሮፕላኑ በድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፍያ በሰላም እንዳረፈም ገልጿል።

መንገደኞችን በተለመደው መልኩ ከአውሮፕላኑ ማውረድ መቻሉን ገልጾ አየር ጢሱ የተነሳበትን ምክንያት በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁሟል።

ለተፈጠረው ክስተት መንገደኞቹን ይቅርታ ጠይቋል።

ከዚህ ቀደም (ከወራት በፊት) ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ አውሮፕላን ውስጥ ጭስ መታየቱን ፤ ነገር ግን አውሮፕላኑ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል መቆሙ መንገዶኞቹም ከአውሮፕላን ላይ ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መወርዳቸው መገለጹ የሚዘነጋ አይደለም።

በወቅቱም ጢሱ ከእሳት ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ ሳይሆን አዉሮፕላን ዉስጥ ያለዉ ዘይት ተቃጥሎ የተፈጠረ መሆኑን ይህም አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ችግር እንደሆነ አስረድቶ ነበር።

ዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ በነበረውና ድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፍያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ በነበረው አውሮፕላኑ ውስጥ የታየው #ጢስ ምክንያት ምን እንደሆነ #እያጣራ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#MPESASafaricom

💯 የድምጽ ጥቅሎችን እየገዛን በ100% ጉርሻ ደቂቃዎች እንንበሽበሽ!! ከሳፋሪኮም ጋር በአብሮነት አንድ ወደፊት⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details...
የቴሌግራም ቦታችንን https://t.iss.one/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኢትዮ ቴሌኮም የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ግብይት አገናኝነት (broker) ፈቃድ አግኝቷል " - ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዘው ኢትዮ ቴሌኮም ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ለመሸጥ ያቀደውን 10 በመቶ ድርሻውን፣ የራሱን የቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ራሱ እንዲያገበያይ እንደተፈቀደለት ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ከኢትዮ ቴሌኮም ጠቅላላ ሀብት ውስጥ አሥር በመቶ የሚሆነው በአክሲዮን…
#ኢትዮቴሌኮም : ዛሬ የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ ሆኗል።

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በተካሄደ ሥነ-ስርዓት የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ ተደርጓል።

የአክሲዮን ሽያጭ ጊዜው ከዛሬ ጥቅምት 6 ጀምሮ እስከ ታኅሣስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል፡፡

ዝርዝር መረጃ ፦

- በ2016 በወጣው የሂሳብ ሪፖርት የድርጅቱ ካፒታል ➡️ 100 ቢሊዮን ብር ነው።

- በዓለም አቀፍ የ3ተኛ ወገን የገበያ ተመን መሰረት ድርጅቱ የሚያወጣው ዋጋ ➡️ 300 ቢሊዮን ብር ነው።

- በመጀመሪያው ዙር መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ የቀረበው ➡️ 100 ሚሊዮን ሼር ነው።

- የአንድ ሼር ዋጋ ➡️ 300 ብር ነው።

- 100 ሚሊዮን ሼር በ300 ብር ሲሸጥ ኢትዮ ቴሌኮም ከሼር ሽያጭ ➡️ 30 ቢሊዮን ብር ያገኛል።

- ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን  ➡️ 33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል።

- ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 3,333 ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ ➡️999,900 ብር ይሆናል።

- መግዛት የሚቻለው ከዛሬ ጥቅምት 6 እስከ ታህሳስ 25 ድረስ ይሆናል።

- የሼር አባላቱ የሚታወቁት ➡️ ጥር 23/2017

- ሽያጩ በቴሌብር ብቻ የሚደረግ ይሆናል።

- ክፍያውን በ48 ሰዓት ውስጥ መክፈል ይቻላል።

- አንድ አክሲዮን ግዢ ሲፈጸም ከአክስዮኑ ዋጋ በተጨማሪ 1.5% የአገልግሎት ክፍያ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፍል ይሆናል።

- ከከፍተኛው የአክሲዮን መጠን በላይ መግዛት አይቻልም።

- ግብይቱ የሚካሄደው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮቴሌኮም : ዛሬ የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ ሆኗል። ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በተካሄደ ሥነ-ስርዓት የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ ተደርጓል። የአክሲዮን ሽያጭ ጊዜው ከዛሬ ጥቅምት 6 ጀምሮ እስከ ታኅሣስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል፡፡ ዝርዝር መረጃ ፦ - በ2016 በወጣው የሂሳብ ሪፖርት የድርጅቱ ካፒታል ➡️ 100…
አንድ ሰው ከኢትዮ ቴሌኮም የገዛውን አክሲዮን ድርሻ ማዘዋወር፤ አትርፎ መሸጥ ፤ እንደ ማሲያዣ መጠቀም ቢፈልግ ይችላል ወይ ?

አትዮ ቴሌኮም አሁን የሚጀመረው የአክሲዮን ሺያጭ የመጀመሪያው ምዕራፍ እንደሆነ አስታውቋል።

በዚህ ምዕራፍ ዜጎች የአክሲዮን ድርሻ ብቻ መግዛት የሚችሉ ይሆናል።

ዜጎች ድርሻቸውን ማዘዋወር ፤ አትርፎ መሸጥ ፤ እንደ ማሲያዣ መጠቀም የሚችሉት ኢትዮ ቴሌኮም ሁለተኛ ምዕራፍ ብሎ ባስቀመጠው ሲሆን ይህም ገና በሂደት ላይ እንዳለ ተጠቅሷል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ቴሌኮም በ " listing " ሂደት ላይ እንደሚገኝ እና ይህም በአጭር ጊዜ እንደሚጠናቀቅ የጠቀሱ ሲሆን ይፋዊ ቀን ግን አልተቆረጠለትም።

የሁለተኛው ዙር አክሲዮን ሽያጭ ሲጀመር ደግሞ ዜጎች ድርሻ ማዘዋወር ፣ አትርፎ መሸጥ ፤ እንደ ማሲያዣ መጠቀም ያስችላቸዋል።

እንዴት ነው አክሲዮን የሚገዛው ?

በቴሌብር ላይ ነው መግዛት የሚቻለው። ቴሌብር ላይ ሲገቡ አክሲዎን ለመግዛት የሚል አማራጭ ይገናኛል (ልክ ላውንች ሲደረግ) በዛ አማካኝነት ነው መግዛት የሚቻለው። በዛ ዝርዝር መረጃ ይገኛል፤ የደብንበኝነት ውልን ስለሚኖር አንብቦ መቀጠል ይችላል ከተስማሙ።

(እስካሁን ድረስ ቴሌብር ላይ ይህ የአክሲዎችን ሽያጭ አማራጭ አልመጣም ልክ ሲመጣ እናሳውቃችኃለን)

ፎርሙን በ48 ሰዓት ውስጥ ማስተካከል  ይቻላል ፤ በተመሳሳይ ክፍያም በ48 ሰዓት ውስጥ መከፈል አለበት። ከ48 ሰዓት በኃላ ፎርሙን ማስተካከል አይቻልም።

ፎርሙን መጀመሪያ በመደበኛ መታወቂያ፣ መንጃ ፍቃድ ፣ ፓስፖርት መሙላት የሚቻል ሲሆን መጨረሻ ላይ የሼር ባለቤት ለመሆን የናሽናል አይዲ (ፋይዳ) ያስፈልጋል።

ሼር ገዢ ተመዝጋቢዎች ቁጥር ለሽያጭ ከቀረበው ሼር በላይ ከመጣ ከዛ ውስጥ እነማን የሼሩ ባለቤት ይሆናሉ የሚለውን ለመለየት የሚያስችል አሰራር ተቀምጧል። (በቀጣይ በዚህ ላይ መረጃ እናቀርባለን)

➡️ ሼር መግዛት ማመልከይ የሚችለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ እና እዚሁ ሀገር ውስጥ በአካል ያለ ነው።

2016 ዓ/ም በወጣ የሂሳብ ሪፖርት የድርጅቱ የካፒታል 100 ቢሊዮን ብር ሲሆን በዓለም አቀፍ የ3ተኛ ወገን የገበያ ተመን መሰረት ድርጅቱ የሚያወጣው ዋጋ 300 ቢሊዮን ብር ነው።

በመጀመሪያ ዙር መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ የቀረበው ደግሞ 100 ሚሊዮን ሼር ነው። የአንድ ሼር ዋጋም 300 ብር ነው። ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን  33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል። ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 3,333 ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 999,900 ብር ይሆናል።

#TikvahEthiopiaAddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ለመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት የሆነው ቅልጥ አለት መሬት ውስጥ መምጣቱ ነው " - ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) ዛሬ ጠዋት 1 ሰዓት ከ37 ደቂቃ ከ50 ሴኮንድ ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። ቦታው  ባለፈው በተከሰተበት አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.6 አካባቢ እነደሆነ ተገልጿል። የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ ድረስ በደንብ ተሰምቷል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስና…
#Alert🚨

ከደቂቃዎች በፊት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ንዘረት እንደሰሙ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል።

" በተለይም ፎቅ ላይ በደንብ ይታወቅ ነበር " ብለዋል።

ጎተራ፣ አያት ፣ ባልደራስ ፣ ሰሚት ፣ መካኒሳ ፣ ጀሞ ፣ ኮዬ ፣ ጣፎ ፣ ቱሉ ዲምቱ ፣ ጦር ኃይሎች ፣ ቀጨኔ፣ ጎፋ ... እንዲሁም ከሌሎች በርካታ አካባቢዎች ቲክቫህ ኢትዮጵያ ንዝረቱ መሰማቱን የሚመለከቱ መልዕክቶችን ተቀብሏል።

ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት በቀናት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።

ሰሞኑን በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ መሆኑ ይታወቃል።

ይህም የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች ድረስ እየተሰማ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Alert🚨 ከደቂቃዎች በፊት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ንዘረት እንደሰሙ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል። " በተለይም ፎቅ ላይ በደንብ ይታወቅ ነበር " ብለዋል። ጎተራ፣ አያት ፣ ባልደራስ ፣ ሰሚት ፣ መካኒሳ ፣ ጀሞ ፣ ኮዬ ፣ ጣፎ ፣ ቱሉ ዲምቱ ፣ ጦር ኃይሎች ፣ ቀጨኔ፣ ጎፋ ... እንዲሁም ከሌሎች በርካታ አካባቢዎች ቲክቫህ ኢትዮጵያ ንዝረቱ መሰማቱን የሚመለከቱ…
#Update

እንደ ' አሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ ' ዛሬ ምሽት ልክ 5:11 ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከአዋሽ በሰሜን በኩል 17 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው።

በሬክተር ስኬል 4.6 የተመዘገበ እንደሆነ ጠቁሟል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች እና በተለያዩ የክልል ከተሞች ተሰምቷል።

አዋሽ አካባቢ ባለፉት ሳምንታት ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ ሲሆን አዲስ አበባ ድረስ የዘለቀ ንዝረት ሲሰማ ይህ በቀናት ልዩነት ለ3ኛ ጊዜ ነው።

ከቀናት በፊት አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ በሬክተር ስኬል 4.6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ከዛ በፊት ደግሞ በሬክተር ስኬል 4.9 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ንዝረቱ አዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ላይ መሰማቱ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
Announcement of Professional Training Programs
1. Python Programming + Data Analytics and Visualization
2. Python Programming + Artificial Intelligence 

By: Addis Ababa University,
Addis Ababa Institute of Technology (AAiT),
School of Electrical & Computer Engineering
Registration Deadline: October 19, 2024
Training Starts on: October 28, 2024
Registration:  Addis Ababa Institute of Technology (AAiT),
School of Electrical and Computer Engineering, Main Building 1st Floor, Office Number: 124

Online Registration Link: https://forms.gle/E54L9aVkHQ1pCs8v5
Telephone: +251-940-182870 / +251-913-574525
Email: [email protected]

More information:  https://forms.gle/E54L9aVkHQ1pCs8v5 

Our Telegram Channel: https://t.iss.one/TrainingAAiT
ሴጅ ማሰልጠኛ !

የድረ-ገፅ እና ሞባይል መተግበሪያ ማበልፀግ (Full-Stack Website and Mobile Application Development) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን።  
👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ ኮምፒውተርና ፕሮግራሚንግ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 Front-end እና Back-end በአንድ ላይ እስከ Deployment ያካተተ
👉 በተግባር ድረ ገጾችን እና ሞባይል መተግበሪያዎችን እያበለፀጉ የሚሰለጥኑበት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️  0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram:
Tiktok:
Linkedin:
" የታይ-ታይ ከረሜላ በህጋዊ መንገድ የተመዘገበ እና የተረጋገጠ ጤናማ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው " -ቪታ ፉድ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማ

መሰረቱን በቱርክ ያደረገው እና እ.ኤ.አ ከ 2019 ጀምሮ በኢትዮጵያ ታይ ታይ የተሰኙ ከረሜላዎችን በማምረት ለተጠቃሚዎች እያደረሰ የሚገኘው ቪታ ፉድ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማ ምርቶቼ በህጋዊ መንገድ በኢትዮጵያ በአምራችነት የተመዘገቡ እና ጥራታቸውን የጠበቁ መሆናቸውን ሊሰመርበት ይገባል ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ገልጿል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በገበያ ላይ በመንግስት ያልተመዘገቡና የምስክር ወረቀት የሌላቸው ተመሳስለው የተሰሩ ምርቶች መኖራቸውን አስተውለናል ያለው ድርጅቱ እነዚህ ምርቶች በህገ ወጥ መንገድ ስለሚመረቱ ምንም አይነት የአምራች መረጃም ሆነ አድራሻ የላቸውም ብሏል።

ተቋሙ ጉዳዩን ለአዲስ አበባ ጤና ቢሮ እና ለኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በተደጋጋሚ ማሳወቁን በመግለጫው ገልጿል።

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮም እነዚህን ህገወጥ ምርቶች የመለየት ስራ የሰራ ሲሆን የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣንም ምርቶቹን በመገናኛ ብዙሃን በማሳወቅ ከገበያ አግዷቸዋል።

ሆኖም እኚህ የታገዱ፣ በህገወጥ መንገድ የተመረቱ እና ተመሳስለው የተሰሩ ምርቶች የእኛን ምርቶች አመሳስለው ስለሚገለብጡ ደንበኞቻችን ምርቶቹን ከእኛ(ከህጋዊ ምርቶች)መለየት ባለመቻላቸው ምርቶቻችን ታግደዋል የሚል ብዥታ እንደተፈጠረ ተናግሯል።

ድርጅቱ የታይ-ታይ ከረሜላ በህጋዊ መንገድ የተመዘገበ እና የተረጋገጠ ጤናማ እና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሁም በህጋዊ መንገድ በኢትዮጵያ በአምራችነት የተመዘገበ መሆኑን ሊሰመርበት ይገባል ብሏል።

እነዚህ ምርቶች (ከረሜላዎች) በተለይም ልጆች የሚጠቀሟቸው በመሆኑ ሁሉም ሰው ከመግዛቱ በፊት የምርቶቹን ደህንነት ግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚኖርበት አሳስቧል።

@tikvahethiopia