TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" አሻራ የሚቀመጠው ታሪክን በመደምሰስና በሕዝብ ሰቆቃ ላይ አይደለም ! " - አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች

አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ልከዋል።

ፓርቲዎቹ ፦

➡️ እናት
➡️ መኢአድ፣
➡️ ኢሕአፓ፣
➡️ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ ናቸው።

ፓርቲዎቹ ምን አሉ ?

" ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ በመጀመሪያ የወንዝ ዳር ልማትና የጫካ ፕሮጀክት በሚል ተጀምሮ አኹን ላይ የኮሪደር ልማት በሚል መጠኑንና አድማሱን አስፍቶ ሙሉ ከተማ ወደማፍረስ የተሸጋገረው ሥራ አሻራ በማሳረፍ ሰበብ የመቶ ሺህዎችን ሕይወት እያመሰቃቀለ እንደሚገኝ ባደረግነው ዳሰሳ ተረድተናል " ብለዋል።

" በድንገት ቤታቸው የፈረሰባቸውና የይፈርሳል መርዶው ሲነገር ለጠና ሕመም የተዳረጉ፣ ከለመዱት ማኅበራዊ መሠረት የተናጠቡ፣ ሥራቸው ሙሉ ለሙሉ የተቋረጠና ለከፋ ችግር የተዳረጉ፣ ቍጥሩ በውል ያልታወቀ በድንጋጤም የሞቱ እንዳሉ ለመረዳት ችለናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከዋና ባለቤቶች/ባልይዞታዎች ባልትናነሰ ተከራዮች ከፍ ላለ ስቃይ እንደተዳረጉ፣ አካል ጉዳተኞችና አቅመ ደካሞች የከፋ ችግር ላይ መውደቃቸውን ታዝበናል " ሲሉም ጠቁመዋል።

ፓርቲዎቹ " ይዋል ይደር እንጂ ይህ የሕይወት መመሰቃቀል የማይነካው የከተማዋ ነዋሪ እንደማይኖር ለመገመት ነቢይ መሆን አይጠይቅም " ብለዋል።

" አዲስ አበባ በዓለም ሦስተኛዋ ድፕሎማቲክ ከተማ በመኾኗ ንፁሕ መሆን፣ የበለጠ ማማርና መዘመን እንዳለባት ኹሉም የሚቀበለው ሀቅ ነው " ያሉት ፓርቲዎቹ  " ይህ ማለት ግን ከተማው ' ያረጀ ነው፤ የቤቶቹ ግድግዳ ጭቃና እንጨት ነው፤ ሸራ ነው፤ አብዛኛው የመንግሥት ቤቶች ናቸው፤ ...' በሚል ሰበብ በአንድ በኩል አዛኝ በመምሰል በግልባጩ ግን ከተማው ' የእኛ ' አሻራ የለበትም በሚል ከስሁት ትርክት በተወለደ ጥላቻ የማፍረሻ ምክንያት እየፈለጉ የከተማዋን ነዋሪ በማፈናቀልና በአንድ ጀምበር ኑሮውን ወደ ሲዖልነት መለወጥ ፍጹም ተቀባይነት የሌለውም " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈው " ሀገር የምትተዳደርበትን ሕገ መንግሥት (አንቀጽ 40፣ 41፣ 89፣ 90፣ 91፣ 92) እና አዋጅ ቍ. 1161/2011 ዓ.ም በመሠረታዊነት የጣሰና ይጠብቀው ዘንድ ሓላፊነቱን በተቀበለ መንግሥት እየተፈጸመ የሚገኝ ከፍተኛ ወንጀል ነው ብለን እናምናለን " ሲሉ ገልጸዋል።

" ቤት ንብረታቸው በአንድ ጀምበር እንዲፈርስ የሚደረጉ ዜጎች በአብዛኛው ካሳም ሆነ ምትክ ቦታ እንዲሁም በቂ የመዘጋጃ ጊዜ ሳይሰጣቸው በማኅበረሰብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ጭምር ለመኖር እየተገደዱና ሌሎች ደግሞ ጊዜያዊ መጠለያ በቆርቆሮ ሠርተው እንዲገቡ መመሪያ የተሰጣቸው መሆኑን ከተረኛ የጉዳቱ ሰለባዎች ለመረዳት ችለናል " ብለዋል።

" ከእነዚህ ዜጎች ‘እድለኛ’ የሆኑ ጥቂቶቹ በማካካሻ መልክ የሚሰጣቸው ኮንዶሚኒዬም ቤት ብዙ 100 ሺዎች ለአሥርት ዓመታት ቆጥበው የተሠራና እጣው ባለመውጣቱ እንጂ ባለቤት ያለው ነበር " ሲሉ ገልጸዋል።

አራቱ ፓርቲዎች ፥ 

° " በአያገባህም " ስሜት የከተማ ልማት መሪ እቅድ ወደ ጎን ተወርውሮ በጥናትና ስሌት ሳይሆን በስሜት ብቻ ከላይ ወደታች በሚወርድ ውሳኔ፣

° ጥቅምና ጉዳታቸው በዘርፉ ባለሙያዎች ያልተመዘነ፣

° በፕሮግራም/strategy/ ያልተያዙና የአጭር ጊዜ ትርፍ ብቻ ያላቸው (project based) አካሄድ እንዲህ የኑሮ ውድነት፣ የቤት/የቦታ እጥረትና ዋጋ መናር፣ የመጓጓዣ፣ የውሐና መሰል መሠረተ ልማት ችግር ጠፍሮ ለያዛቸው ከተሞች የእግረኛ መንገድ፣ የሕንጻ ላይ መብራትና ቀለም፣ ሣርና ዘንባባ ተከላ እና መሰል የተብለጨለጩ ማሸብረቂያዎች የወረት ያህል ለጊዜው ከላይ ሲታይ ያማረ ቢመስልም የከተማውን ነዋሪ ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ችግር ቢያወሳስበው እንጂ እሴት ጨምሮ ችግራቸውን አይፈታውም፤ የሥርዓቱንም ስም አይገነባም ብለዋል።

" ከተማን የማሳመርና ማዘመን ሀሳብ ከየትኛውም ወገን ሊነሳ ቢችልም ከመሪዎች ፍላጎት /inspiration/ በላይ በዘርፉ ልምድና እውቀት ጠገብ በሆኑ ባለሙያዎች ኹለንተናዊ ምልከታና ሙግት ተደርጎበት ትርፍና ኪሳራው ተሰልቶ ሊሆን እንደሚገባ በጽኑ እናምናለን " ሲሉ ገልጸዋል።

" አሻራ ማኖር በራሱ የሚጠላ ባይሆንም ፖለቲካዊ ፍላጎት የተጫነው፣ ሕዝብን ያገለለ፣ ታሪክን የሚያፈርስ፣ የማኅበረሰብን በዘመናት የተገነባ ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር የሚያናጋ፣ ነዋሪዎችን በአንድ ጀምበር ጥሪት አልባ የሚያደርግ፣ ብዙ መቶ ሺዎች የሚተዳደሩበትን የንግድ ሥራ ሙሉ በሙሉ የሚገድል፣ ግብታዊና ነዋሪው ‘በአብሬ አድጋለሁ’ ተስፋ ሳይሆን ‘በያፈናቅሉኛል’ ሥጋትና ኹል ጊዜ መጻተኛ ስሜት እንዲሰማው የሚያደርግ መሆን እንደሌለበት የሚታመን ቢሆንም በአዲስ አበባ ከተማ እየተተገበረ ያለው ይህ መራራ እውነት ነው " ብለዋል።

ፓርቲዎቹ ፤ " አኹን ላይ በአዲስ አበባ በ4ኪሎ፣ 5ኪሎ፣ ፒያሳ፣ ቤላ፣ አምባሳደር፣ ፈረንሳይ፣ ቦሌ፣ ካዛንችስ፣ ገርጂ እና በኹሉም ወንዝ አለባቸው በሚባሉ የከተማዋ አካባቢዎችና በሌሎችም አካባቢዎች በዋና ዋና መንገዶች ዳርቻ  ከፍተኛ ፈረሳዎች እየተካሄዱ/እንደሚካሄዱ በይፋም ይፋዊ ባልሆነ መንገድም እያየንና እየሰማን ነው " ሲሉ ጠቁመዋል።

" በኑሮ ውድነትና ሰላም እጦት ወገቡ የጎበጠን ማኅበረሰብ አለፍ ሲልም ገሃድ የወጣ የከተማ ውስጥ ረሃብ ባለበት በተጣደፈ አኳኋን ዜጎችን ከድጡ ወደ ማጡ መውሰድ ለምን እንደተፈለገ አፍራሾቹ ብቻ የሚገባቸው እውነት ኾኖ ዋናው ግን ልማት ሳይሆን ፦
• ነባሩን ማኅበረሰብ ከማኅበራዊ መሠረቱ መነጠልና ማሳሳት፣
• የእምነት ቦታዎችን ያለሰው ማስቀረት፣
• ሰውን ከመሐል መግፋት ከዳር ማስጨነቅ፣
• መንግሥት የገጠመውን በጀት እጥረት ከሊዝ ሽያጭ መሰብሰብ፣
• ሥርዓቱን ተጠግተው ፍርፋሪ ለሚጠብቁ " የአየር ባየር ባለሀብቶች " ማበልጸጊያ እንደሆነ እሙን ነው " ብለዋል።

" በሌላ በኩል እንደሥርዓት በሀገር ደረጃ ያጣውን ቅቡልነትና ቁጥጥር በማዕከል አለሁ ለማለትና አዲስ የከተማ ትርክት/narration/ ከመፍጠር የመነጨ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ቢያንስ ቢያንስ ተነሽዎችን ከአልሚዎቹ/ባለሀብቶች ጋር በመስማማት ከሚሠራው ሕንፃ አንደአቅማቸው የድርሻቸውን አግኝተው እንዲኖሩ ማድረግ በተገባ ነበር " ያሉት ፓርቲዎቹ " እየተፈጸመ ያለው ነገር ኢ ሕገ መንግሥታዊ፣ አግላይ፣ የበላይና የበታች አካሄድ በመሆኑ በጽኑ እናወግዛለን " ብለዋል።

አራቱ ፓርቲዎች ፦

1ኛ. " መንግሥት በሕገ መንግሥቱ የተደነገገውን የዜጎች መብት እንዲያከብርና ማኅበረሰቡን መሠረታዊ በሆነ መልኩ ከሚያናጋ በልማት ሽፋን የሚተገበር ደባ እንዲያቆም " ብለዋል።

2ኛ. " የፈረሳው ሰለባ የሆነው የአዲስ አበባ ነዋሪ ባገኘው አጋጣሚ ኹሉ ድርጊቱን በሰላማዊ መንገድ በመቃወም ሕገ መንግሥታዊ መብቱን እንዲያስከብር " የሚል ጥሪ አቅርበዋል።

3ኛ. " ከቦታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የነበሩበትን ቦታ ካርታና መሰል የነዋሪነት/ባለ ይዞታነት/ ማስረጃዎች በጥንቃቄ እንዲያስቀምጡ " አስገንዝበዋል።

4ኛ. " አዲስ በፈረሱ አካባቢዎች ላይ እየገነችሁ ያላችሁ ባለሀብቶች የተፈናቀለ ወገናችሁ አንድ ቀን ተመልሶ እንደሚመጣ አድርጋችሁ ማሰብም መሥራትም አለባችሁ " ሲሉ አሳስበዋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኮሬ “ ባለፉት ዓመታት ከ300 በላይ ንጹሐን በታጣቂዎች ተገድለዋል ” - ኮሬ ዞን ኮሚዩኒኬሽን  “መንግስት ቸልተኛ ሆኗል የሚል ግምገማ አለን። ዛሬ ጠዋትም ሰው ተገድሏል” - የክልሉ ተወካዮች ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ  ንጹሐን ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች፣ ዞኑና የክልሉ ተወካዮች ምክር ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። በዞኑ ጎርካ ወረዳ ዳኖና ኬረዳ…
#ኮሬ

🛑 “ አሁንም ግድያው እንደቀጠለ ነው። ዛሬም 3 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል” - ኮሬ ዞን

🔵 “ ምንም መፍትሄ የሌለው ጉዳይ ነው የሆነው። ግድያና መፈናቀሉ ቀጥሏል” - በፌደራል ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የኮሬ ህዝብ ተወካይ

ዛሬ (ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ/ም) ሦስት ንጹሐን ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ከምዕራብ ጉጂ በተነሱ ታጣቂዎች መገዳላቸውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኮሬ ዞን አስተዳደር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል።

“ ችግሩን ማስቆም የሚችል መንግሥት አካል አልተገኘም ” ያሉት አንድ ስማቸው እንዲነገር ያልፈለጉ በዞኑ ኃላፊነት ላይ የተቀመጡ አካል፣ በሁለተኛው ዙር የመኸር ወቅት ብቻ 11 ሰዎች ሲገደሉ አራት ደግሞ መቁሰላቸውን ገልጸዋል።

“ ጉዳቱ የደረሰባቸው ቀበሌዎች ዳኖ፣ ጎልቤ፣ ጋሙሌ፣ ኬረዳ፣ ሻሮ ናቸው። በአጠቃላይ ከ3.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት በታጣቂዎች ተዘርፏል ” ነው ያሉት።

በአካባቢው ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ የሚፈጸመው ግድያ ለምን ይሆን መቋጫ ያጣው ? ምን እየተሰራ ነው ? የሚል ጥያቄ ያቀረብንላቸው በፌደራል ተወካዮች ምክር ቤት የኮሬ የህዝብ ተወካይ አምዛዬ አወቀ (ዶ/ር) ምላሽ ተሰጥተዋል።
 
“ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ምንም መቋጫ አላገኘም። እኛም በተደጋጋሚ ለመንግስት አመልክተናል። ግን ምንም መፍትሄ የለም። በየቀኑ ግድያ እንሰማለን ” ብለዋል።

“ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እኛም ሁሉም በዬቦታው እየጮኸ ነው ግን መፍትሄ የለም። ግራ የሚያጋባ ሁኔታ ነው ” ሲሉም አክለዋል።

የኮሬን ህዝብ የወከሉት በፌደራል ደረጃ እንደመሆንዎ ለመንግስት ቅርብ ነዎትና ጉዳዩን በግልጽ ለመንግስት አንስታችሁ ነበር? ከሆነስ የመንግስት ምላሽ ምንድን ነው? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄም ፦

“ በየጊዜው ነው የሚነሳው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርላማ በተገኙበት ጊዜ ኦፊሻሊ ጥያቄ ሁሉ አንስቼ ነበር በ2016 ዓ/ም። ‘ሁኔታውን ለማርገብ የተወሰነ የመከላከያ ኃይል ይላካልና ሁኔታው ይረጋጋል’ ብለው ነበር።

ከዚያ በኋላ የተወሰነ ኃይል ሂዶ ነበር። እሱም አሁን በአገሪቱ ባለው ሁኔታ ይመስለኛል ተቀነሰ። ከዚያ በኋላ ግን ሁኔታው እየተባባሰ ነው የሄደው።

ወር በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ 10 ሰዎች ተገድለዋል። ህዝቡ በዬቀኑ ይዘረፋል። መንገድም የለም። የዲላ ህዝብ ጋር ነው የኮሬ ዞን የሚገናኘው ይሄ መንገድም ከተዘጋ ዘጠኝ ዓመት ሆኖታል።

ይሄን ሁሉ በማመልከታቸም አመልክተናል። ሽማግሌዎች ወጥተው ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት፣ ለሰላም ሚኒስቴር አመልክተዋል፤ ለክልሉ መንግስት በዬጊዜው የሚቀርብ ጉዳይ ነው። 

ነገር ግን ምንም መፍትሄ የሌለው ጉዳይ ነው የሆነው። ግድያና መፈናቀሉ ቀጥሏል ”
ሲሉ መልሰዋል።

ስለዚህ የመፍትሄው ጉዳይ ምንም እየተሰራበት አይደለም ማለት ነው ? ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ ምላሻቸው፣ “ ምንም መፍትሄ የለም ” የሚል ነው።

“ አንዳንድ ጊዜ ‘እርቅ ተደርጓል’ ይባላል፤  አምና እርቅም ለማድረግ ተሰብስበው የነበሩት የብልጽና ፓርቲ ኃላፊም ጭምር የተገደሉበት ሁኔታ አለ። መንግስት የራሱ ፓርቲ አባል ሲገደል እንኳ ገዳዮች እነማን ናቸው ብሎ ተከታትሎ ሊያቀርብ አልቻለም ” ሲሉም ተናግረዋል።

በመሆኑም መንግስት፣ ሚዲያዎችም የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ህዝቡን እንዲታደጉ በህዝቡ ስም ጥሪ አስተላልፈዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ዛሬና ነገ በኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም በአፍሪካ እጅግ ትልቁ የቴክኖሎጂ ውድድር ”A2SV - AI for Impact Hackathon Expo” ይከናወናል! ለሁለተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ የሚካሄደው ይህ ውድድር የአፍሪካ ድንቅ ባለ ተሰጥኦ ወጣቶች አርተፊሻል አስተውሎትን በመጠቀም ችግር ፈቺ የሆኑ ፈጠራዎች የሚያሳዩበት ነው።

ሁላችሁም ይሄንን የቴክኖሎጂ ኤክስፓ መታችሁ እንድትጎበኙ እንጋብዛለን ። እንዲሁም ረቡዕ ጥቅምት 6 የሚካሄደውን ከ 7 የአፍሪካ ሀገራት የመጡትን ተወዳደሪዎች የመጨረሻ ለ 30,000 ዶላር ሽልማት የሚያደርጉትን ፍልምያ እንድትታደሙ ጋብዘኖታል ። በእለቱም የአዲስ ኣበባ ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤ የመክፈቻ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ።

የፕሮግራሙ መርሀግብር
- ኤክስፖ: ጥቅምት 5 - 6 2017 ከጠዋቱ 3 ሰአት እስከ ምሽት 12 ሰዓት
- መዝጊያ ፕሮግራም: ጥቅምት 6 2017 ከምሽት 12 ሰአት እስከ ምሽት 1 ሰዓት
- ቦታው: የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚያም

መግቢያ በነፃ !

(አዘጋጆቹ)
#NBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በሚገዙበት እና በሚሸጡበት ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት ከ2 በመቶ መብለጥ እንደሌለበት አሳስቧል።

ብሔራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በሚገዙበት እና በሚሸጡበት መካከል ያለው ልዩነት በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት መሆን እንዳለበት አመልክቷል።

አሁንም ቢሆን ንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን ገበያ መር በሆነ መንገድ መተመናቸውን እና ይህንኑ ዋጋቸውን በተናጠል በየቀኑ ማሳወቃቸውን መቀጠል እንዳለባቸው ጠቁሟል።

ባንኩ እስካሁን በነበረው አሰራር ንግድ ባንኮች ከውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጋር በተያያዘ የሚጠይቁትን ኮሚሽን ከምንዛሪ መሸጫ ጋር ደምረው ያስታውቁ እንደነበር ጠቅሶ፤ ወደፊት ግን ኮሚሽኑን ከምንዛሪ መሸጫ ጋር ሳይሆን በተናጠል ለደንበኞቻቸው እንዲያሳውቁ አስታውቋል።

#NBE

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NBE የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በሚገዙበት እና በሚሸጡበት ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት ከ2 በመቶ መብለጥ እንደሌለበት አሳስቧል። ብሔራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በሚገዙበት እና በሚሸጡበት መካከል ያለው ልዩነት በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት መሆን እንዳለበት አመልክቷል። አሁንም ቢሆን ንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን ገበያ መር በሆነ…
#ዶላር

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዶላር ዋጋ አሽቆለቆለ።

ባለፉት በርካታ ቀናት በንግድ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ112 ብር ከ3957 ሳንቲም እየተገዛ በ123 ብር ከ6353 ሳንቲም ሲሸጥ ነበር።

ዛሬ ባንኩ ይፋ ባደረገው የዕለታዊ የምንዛሬ ተመን አንዱን የአሜሪካ ዶላር የሚገዛበትን ዋጋ ወደ 113 ብር ከ1308 ሳንቲም አሳድጎ መሸጫውን ወደ 115 ብር ከ3934 ሳንቲም አውርዶታል።

እንደ ዛሬው የምንዛሬ ተመን ባንኩ ዶላር መግዣውን በ1 ብር ከፍ ያደረገው ሲሆን መሸጫው ላይ ካለፉት ቀናት የ8 ብር ቅናሽ አድርጎበታል።

@tikvahethiopia
Forwarded from telebirr
🏆 ሁለተኛው 480,000 ብር ለዕድለኛው ደርሷል!!
🎉🎉 ዕድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ!

ሁንም በርካታ ሽልማቶች እርስዎን ይጠብቃሉ፤ ከባህርማዶ በቴሌብር ሬሚት እና በአጋሮቻችን በኩል የተላከልዎን ሐዋላ በቴሌብር ይቀበሉ ከ11% የገንዘብ ስጦታ በተጨማሪ፣ 5 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ሲቀበሉ አጓጊ ለሆነው የዕድል ጨዋታ ብቁ ይሆናሉ!

🏞 ኩሪፍቱ ወተር ፓርክ ቤተሰብ ፓኬጅ - እያንዳንዳቸው 44,000 ብር
🐏 የበግ ስጦታዎች - እያንዳንዳቸው 20,000 ብር...

የሚቀበሉት የገንዘብ መጠን ሲጨምር የጨዋታ ዕድልዎም ይጨምራል!

🗓 እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም

#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
#Arbaminch

በአርባ ምንጭ ከተማ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የሚሰሩ ህጻዎች ከፍታቸው G+6 እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ስታንዳርድ ተቀመጠ።

የከተማ ህንፃ ቀለማት ምርጫም ነጭና ቢጫ ውህድ ፤ አንድ ህንፃ መቀባት ያለበትም ሶስት አይነት ቀለም ብቻ ነው ተብሏል።

" በኮሪደር የሚለሙ ቋሚ አጥር ግንባታ 1.50 ሜትር ፤ በሚካሄዱ ግንባታዎች ጊዜያዊ አጥሮች ከሁለት ሜትር በላይ ከፍታ ያላቸው ሆነው አረንጓዴ ቀለም በኤጋ ቆርቆሮ ማጠር " እንደሚገባ ተገልጿል።

ዝቅተኛ ህንፃዎች ከመንገድ መራቅ ያለባቸው ርቀት (set back) አደባባዮች ዙሪያ 6 ሜትር፣ ለሌች መንገዶችን ተከትሎ 4 ሜትር፣ ከግለሰቦች ወሰን በኩል መሰኮት ከሌለው 2 ሜትር፣ መስኮት ካለው 3 ሜትር ርቀት መኖር አለበት ተብሏክ።

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በቀንና በማታ ዕይታን የማይረብሽ ውብና ሳቢ መንገድ ዳር መብራት ቀለም የመብራት ቀለም ከ3000K Warm LED በከተማው በሁሉም ዋና መስመሮች በከተማ ውስጥ ያሉ ንግድና ግለሰብ ቤቶች፣ ድርጅቶችና መንግስታዊ እና ሌሎች ተቋማት የማውጣት ግዴታ እንዳለባቸው ስታንዳርድ ተቀምጧል።

አዲስ አበባ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ ወደ ክልሎችም የሄደ ሲሆን የኮሪደር ስራ እየተሰራባቸው ካሉ ከተሞች አንዷ አርባ ምንጭ ናት።

@tikvahethiopia