#WorldMentalHealthDay
"ሥራ የመስራት እድሜ ላይ ከደረሱ ስድስት አዋቂዎች አንዱ የአዕምሮ ጤና ችግር ያጋጥማቸዋል" - ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
የ2024 #የዓለም_የአእምሮ_ጤና_ቀን በዛሬው እለት እየተከበረ ይገኛል። የዘንድሮው ቀን "የአእምሮ ጤና በስራ ቦታ ላይ" በሚል መሪ ሀሳብ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተገልጿል።
ከአለም ህዝብ 60 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች በስራ አለም ላይ እንደሆኑ የአለም ጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል።
በስራ ላይ ካሉት ሰራተኞች ውስጥም ግማሽ የሚሆኑት የአእምሮ ጤና ችግር እንደሚያጋጥማቸው የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በዛሬው እለት የዓለም የአእምሮ ጤና ቀንን አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት ተናግረዋል።
የስራ አለም ላይ ያሉ ሰራተኞች በሚገጥማቸው የአእምሮ ጤና ችግርም በየአመቱ 1 ትሪሊዮን ዶላር እንደሚጠፋ ዶ/ር ቴድሮስ ጠቅሰዋል።
ሰራተኞችን ለአእምሮ ጤና ችግር የሚዳርገው ምንድነው?
- ዝቅተኛ የስራ ክህሎት፣ ችሎታ እና አፈፃፀም
- ከመጠን በላይ የሆነ የሥራ ጫና፤ የሰራተኞች እጥረት፤ አድልዎ፣ መገለል፣ ጥቃትና ትንኮሳ
- ረጅም፣ ያልተገደቡ እና ተለዋዋጭ የስራ ሰዓቶች
- አሉታዊ ድርጊቶችን የሚደግፍ ድርጅታዊ ባህል
- ከሥራ ባልደረቦች በቂ ድጋፍ አለማግኘት
- በቂ ያልሆነ ክፍያ፣ የሚጋጩ የሥራ ፍላጎቶች የአእምሮ ጤና እንደሚያስከትሉ የአለም ጤና ድርጅት ገልጿል።
ዶ/ር ቴድሮስ ስራ የመስራት እድሜ ላይ ከደረሱ ስድስት አዋቂዎች አንዱ የአእምሮ ጤና ችግር እንደሚያጋጥመው የገለፁ ሲሆን የአእምሮ ጤናን ለመጠበቅ የሚደረገው ኢንቨስትመንት አነስተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።
ችግሩን ለመከላከል ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ምን መደረግ አለበት አሉ ?
° አሰሪዎች የአእምሮ ጤና ችግር የሚያስከትሉ ችግሮችን በመለየት ምቹ የስራ ከባቢን መፍጠር እንደሚገባቸው፤
° የድርጅት ኃላፊዎች ጭንቀት ያጋጠማቸውን ሰራተኞች እንዲለዩ፣ የስራ ቦታ ላይ የሚያጋጥም የአእምሮ ጤና ችግርን እንዲቀርፉ መስራት እንደሚገባቸው፤
° የስራ ከባቢን ለሰራተኞች ምቹ እንዲሆን ማድረግ፤ አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ሁሉም ሰራተኞች በንቃት እንዲሰሩ የሚያስችል የስራ ከባቢ መፍጠር እንደሚገባ ዶ/ር ቴድሮስ ባስተላለፉት መልእክት ተናግረዋል።
ሰራተኞች የአእምሮ ጤና ችግር በሚገጥማቸው ጊዜም ሰዎችን ማውራት፣ ባለሙያ ማማከር ወይም እራሳቸውን ማረጋጋት እንደሚኖርባቸው ዶ/ር ቴድሮስ ገልፀዋል።
Via @tikvahethmagazine