TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC ብፁዕ አቡነ አብርሃም ምን አሉ ? - በዓለ ጥምቀቱን ለማክብረ በመንግሥት ዘንድ ቤተክርስቲያን ይሄን ትበል ፣ አለበለዚያ እንዲህ አይደለም የሚሉ መልዕክቶች ደርሰውናል። - ቤተክርስቲያን ሰላሟን ታውጃለች። - አሉ አሉ እየተባሉ ስለተነገሩ ንግግሮች እና ግለሰቦች፣ ጳጳሳት እና ሊቃነጳጳሳት ከሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ታያለች፣ ትመክራለች ታስተምራለች። ህግ አላት በህጓ መሰረት ትገስፃላች። ከዚህ…
#EOTC

" ሀገራችን ሰላም ትሁን፤ የሃይማኖት ሰዎች እንደ ሃይማኖት እናስብ፣ እንደ ሃይማኖት እንናገር፣ አላስፈላጊ ጀግንነትን እንርሳው " - ብፁዕነታቸው

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ምን አሉ ?

- የማይደፈር ሲደፈር አይተናል፤ ቤተክርስቲያን ስትደፈር ዝም አንልም።

- " ፖለቲካው የፖለቲካው መስመር ሲደፈር ዝም እንደማይል ሁሉ እኔም ደግሞ የመጀመሪያዋም የመጨረሻዋም ህይወቴም ማንነቴም ክብሬም ቤተክርስቲያኔ ስለሆናች እሷ ስትደፈር ዝም አልልም። እናገራለሁ፤ የመጣውን በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ "

- ከዚህ በፊት ለመንግሥት ችግር ካለ እዚህ ጠቅላይ ቤተክህነት ውስጥ ንገሩን ብለናቸዋል። እኛ እናርማለን፣ እኛው እናስተካክላለን፣ አላስፈላጊ እርምጃ አትውሰዱ ብለናቸዋል። ትላንት ግን ከቤተክህነት የሚወጣው በሙሉ ይፈተሻል ዛሬም፣ የሚወጣ መኪና በሙሉ ይፋተሻል፤ የሚገባው ግን አይፈተሽም። የሚገባውን የኛ ዘበኞች ይፈትሹ ይሆናል፤ የመንግሥት ወታደሮች ግን አይፈትሹም። አንዱ ሌላ ነገር ይዞ ገብቶ ሲወጣ ፈታሹ ሌላ ነገር ይዞ ተብሎ የቤተክርስቲያን ስም እና ክብር ቢዋረድ ማነው ኃላፊው?

- ምንድነው የተፈለገው? ከቤተክርስቲያን ምንድነው የሚወጣው? መድፍ ነው? መሳሪያ ነው? አከፋፋይ ናት ቤተክርስቲያኒቱ? አትታመንም? መንግሥትን ያስጮኸ ነገር አለ እኛም የጮህንበት ከመንግስት በፊት፤ ግለሰቦችን ስለተናገሩት ንግግር የማይባል ተብሏል እያልን እኛ ነን የጮህን ይሄ የቤተክርስቲያን ቋንቋ አይደለም ብለን ነበር፤ መግለጫ ለመስጠት ተዘጋጅተን ነበር መንገዱን ስናየው መጠላለፊያ እንጂ ከፅድቅ ስላልሆነ ነው ዝም ያለነው። የፅድቅ ሲሆን ገፍተን ነው የምንወጣው።

- ከቤተክህነት ምንድነው የሚወጣው ? ከተፈለገ መባል ያለበት ጥርጣሬ አለን ቤተክህነት ውስጥ ይባላል፤ እንዲህ አይነት ነገር ቢወጣ ኃላፊነቱ የናተ ነው ጠብቁ ነው ልንባል የሚገባው ወይም ሰው እንሥጣችሁ የሚያንሳችሁ ከሆነ ቤተክርስቲያኒቱን እንዳያስወቅስ ነው መባል ያለበት እንጂ ቤተክርስቲያን የማትታመን ሆነ ከትላንት ጀምሮ እስካሁን እኛ መሪዎቹ በማናውቀው ፈታሽ በር ላይ ቆሞ መፈተሽ ድፍረት ነው። ቤተክርስቲያኒቱን ህልውናዋን መፈታተን ነው። አቅሟንም መፈትን ነው ተገቢ አይደለም።

- መደፋፈሩ በዝቷል፤ መንግስትም ቤተክርስቲያኒቱን ይደፍራል አልፎ ይሄዳል።

- እንደ ግለሰብ በስሜት የሚናገሩ ሰዎች ይኖራሉ። ቤተክርስቲያኒቱን መድፈር አዳጋ ነው። ለሃይማኖቱ የማይሞት የለም፣ ከዚህ በፊት ብዙዎች ሞተዋል፤ ተከባብረን እንኑር ለሰላም እንኑር።

- ካህን ነው ሲሉት ሌላ ነጭ ለባሽ ይሆናል፣ ነጭ ለባሽ ነው ሲሉት ካህን ሆኖ ይገኛል፤ የቤተክርስቲያን መሪ ነው ሲሉት የፖለቲካ መሪ ሆኖ ይገኛል፤ የፖለቲካ መሪ ሲሉት ቀዳሽ ሆኖ ይገኛል ምን አመጣው ይሄን ቀጥ ብለን እንቁም። ደሃ ሲበደል ተበደለ እንበል ሲታሰር ፍቱ እንበል፤ እያልን ነው እኮ፤ መንግሥትን ፍቱ እያልን እንመካከራለን ይፈታል ለዚህ ደግሞ እናመሰግናለን።

- በሃይማኖት ጉዳይ አንደራደርም።

- ካህን ካህን ይሁን፣ ወታደርም ወታደር ይሁን ሌላውም እራሱን ይሁን በሚያስተሳስረን ነገር ተሳስረን ጥላቻና ሁከትን፣ ሽብርና አላስፈላጊ ነገርን እናርቅ።

- ካላስፈላጊ #ጎጠኝነት#ዘረኝነት እንራቅ።

- ሀገራችን ሰላም ትሁን የሃይማኖት ሰዎች እንደ ሃይማኖት እናስብ፣ እንደ ሃይማኖት እንናገር፣ አላስፈላጊ ጀግንነትን እንርሳው። አላስፈላጊ ሙገሳንም እንርሳው። ካላስፈላጊ ሙገሳ አስፈላጊ በሆነ ወቀሳና ለመጨረሻው መከራ እራሳችንን እናዘጋጅ።

ያንብቡ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-12-2

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
#EOTC

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ከዚህ ቀደም አውግዛ የለየቻቸው ግለሰቦች አሁንም በሕገወጥ እንቅስቃሴያቸው እንደገፉበት አመልክታ ግለሰቦቹን በፍርድ እንደምትጠይቅ አስታወቀች።

ግለሰቦቹን አሁንም አውግዛ ፤ ድርጊታቸውን ተቃውማለች።

የለበሱት ልብስም የቤተክርስቲያን በመሆኑ #እንዲያወልቁት እንደምታደርግ ገልጻለች።

ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት ቤተክርስቲያን " ሕገወጥ " ባለችው መንገድ በጵጵስና ተሹመናል ካሉት እና በኃላም በእርቅ ወደቤተክርስቲያን ሳይመለሱ ከቀሩት መካከል አባ ገብረማርያም ነጋሳን ጨምሮ 4 አባቶች ትላንት በሰጡት መግለጫ " የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተክህነት መንበረ ጴጥሮስ " አቋቁመናል ብለዋል።

ይህ በ2015 ዓ/ም ተቋቁሟል ላሉት የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መንበር መሰየም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቋሚና ጊዜያዊ ፕሮጀክት መምሪያ ኃላፊ መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ወ/ኢየሱስ ሰይፉ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህ መግለጫ ፤ " ግለሰቦቹ በሌላቸው ክህነት ነው መግለጫ እየሰጡ ያሉት " ብለዋል።

እነዚህን አካላት ያደረጉት ከቀኖና ውጭ ስለሆነ ዛሬም ቤተክርስቲያን አጥብቃ ታወግዛለች ሲሉ ተናግረዋል።

" ቤተክርስቲያን በሕግ በፍርድ ቤት ትጠይቃችለች ፤ በፍትህ መንፈሳዊ ከዚህ ቀደም እንዳወገዘችው አሁንም ህጌ፣ ስርዓቴ፣ ልብሴ ፣ ዶግማዬ ይከበር ትላለች " ሲሉ አክለዋል።

" ከዚህ ቀደም በፍ/ቤት ከቤተክርስቲያን እውቅና ውጭ የትም እንዳይንቀሳቀሱ ፣ አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደው ነበር ያንን ተላልፈዋል ከዚህ በኃላ በፍርድ እንጠይቃቸዋለን፤ የለበሱት ልብስም የቤተክርስቲያን ስለሆነ እናስወልቃቸዋለን፤ ህገወጥ ናቸው " ብለዋል።

" ከዚህ ባለፈ ይህ የሕገወጥ የሹመት እንቅስቃሴ ጉዳይ ከኦሮሚያ ወገን የተነሱትን ብቻ ሳይሆን ከትግራይ ወገን የተነሱትንም የሚመለከት ነው " ያሉ ሲሆን ሲመቱ ትክክለኛ አይደለም ቅዱስ ሲኖዶስም አይቀበለውም ብለዋል።

የቤተክርስቲያንን ውሳኔ ማስፈፀም የሚችል አካል ሌላ በመሆኑ እንዲያስፈፅም በትዕግስት እየጠበቅን ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ኃላፊው ፤ ከዚህ ቀደም በኦሮሚያ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት አባቶች በቤተክርስቲያን ጥሪ ተመልሰው መጥተው ፣ ከመንግሥት ጋር በተደረግው ውይይት ፣ ወደቀድሞ ስራቸው እንዲመለሱ ተደርጎ በስራ ላይ ናቸው ብለዋል።

አራቱ እንዳልተመለሱና በሕገወጥ እንቅስቃሴ መቀጠላቸውን ገልጸው " የቤተክርስቲያንን ስም ማንሳት አይችሉም ፣ ስሟን ማጠልሸት አይችሉም " ሲሉ አሳስበዋል።

" እራሱ ህገወጥ ቡድን የ ' 5 ኪሎ ህገወጥ ' እያለ መጥራቱ ትልቅ ድፍረት ነው " ያሉት ኃላፊው ፤ " ይህን ድፍረት የሰጣቸውም ወቅትና ጊዜውን እየዋጁ መነሳታቸው ነው ብለዋል።

" #ሃይማኖት እና #ፖለቲካም ተቀላቅሎባቸዋል " ሲሉ አክለዋል።

" የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ምዕመናኖቿ ይህንን ህገወጥ ተግባር አይቀበሉትም ፤ ስለተወገዛችሁም ምዕመኑንም ከእናተ መስቀል አይባረክም " ሲሉ አሳውቀዋል።

ከዚህ ባለፈ ቤተክርስቲያኗ አውግዤ የለየኋቸውን አካላት መግለጫ ልክ እንደ ህጋዊ እያደረጉ ያቀርባሉ ያለቻቸውን #ሚዲያዎች ' ከቤተክርስቲያን ላይ እጃችሁን ፣ ሚዲያችሁን አንሱ ' ስትል አስጠንቅቃለች።

@tikvahethiopia
#EOTC

ቅዱስ ፓትርያርኩ " የሃይማኖት አባቶች ከፓለቲካ ገለልተኛ በመሆን ሁሉን በፍቅርና በእኩልነት ማቀራረብ ይገባቸዋል " ሲሉ በ11ኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸው ተናገሩ።

ፓለቲከኞቾም ባልዋሉበት እና ባልተፈቀደላቸው ቦታ በቤተክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

ቅዱስነታቸው " የዘመናችን ትውልድ ከተግባር ይልቅ አስመሳይ ሆኖ መታየትን ከቅድስና ይልቅ ነውረ ኃጢአትን፤ ከትሕትና ይልቅ ትዕቢትን የተለማመደ ለሃይማኖትም ሆነ ለማኅበረ ሰብ ጤና ያልተመቸ ትውልድ እንደሆነ በግልጽ ይታያል ሲሉ ተግሳጽ አሰምተዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቀነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት 11ኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን አስመልክቶ ምን አሉ ?

- ያለንበት ዘመን ለእግዚአብሔር ክብርን የነሣ፤ ከፍቅርና ከአንድነት የራቀ ራስ ወዳድነትና በቃኝ አለማለትን የወረረው፤ በዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂ የተዋጠ ትውልድ የታየበት ዘመን ነው።

- የዘመናችን ትውልድ ከተግባር ይልቅ አስመሳይ ሆኖ መታየትን ከቅድስና ይልቅ ነውረ ኃጢአትን፤ ከትሕትና ይልቅ ትዕቢትን የተለማመደ ለሃይማኖትም ሆነ ለማኅበረሰብ ጤና ያልተመቸ ትውልድ እንደሆነ በግልጽ የሚታይ ነው፤ ይህን አደገኛ አዝማሚያ በማስተዋል ካልታረመ ሂዶ ሂዶ የእግዚአብሔርን ቁጣ ማስከተሉ አይቀርምና እንደ እግዚአብሔር ጥሪ ወደ እሱ ብንመለስ ይሻላል።

- እኛ የሃይማኖት አባቶችም አልጫ የሆነውን የዘመናችንን ትውልድ በትጋት አስተምረን በቈራጥነት ገሥጸንና መክረን ወደ እግዚአብሔር ካልመለስነው ከቁጣው አንድንም። ቅዱስ መጽሐፍ እንዳስተማረን አስተምረነው የማይመለስ ከሆነ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል! እኛ ባለማስተማራችን የሚጎዳ ትውልድ ካለ ግን እኛ የደሙ ተጠያቂዎች መሆናችንን በማያሻማ ሁኔታ ተገልጾአልና ነው፤ የእኛ ኃላፊነት እስከዚህ ድረስ ከባድ መሆኑን ባንዘነጋውም እንደ ዓለሙ በልዩ ልዩ ደካማ አስተሳሰቦችና ተግባራት እየተሰናከልን መሆናችን የአደባባይ ምሥጢር ከሆነ ውሎ አድሮአል።

- እኛ የሃይማኖት አባቶች ዓለም ሲሳሳት ከመገሠጽ ይልቅ አብሮ ማጨብጨብ ተለማምደናል፤ ባናጨበጭብም ዝምታን መርጠናል ነገር ግን ኃላፊነቱን የተረከብነው ጥፋት ሲፈጸም ዝም ብሎ ለማየት አልነበረም፤ ከዓለሙ ጋር አብሮ ለማጨብጨብ ወይም አድማቂ ለመሆንም አልነበረም፤ ከቅዱስ ወንጌሉ መሠረተ ሐሳብ ፍንክች ሳንል ፦
* የእውነት፥
* የፍትሕ የሰላም፥
* የፍቅር፥
* የዕርቅ የይቅርታ የአንድነት፥
* የስምምነት ጠበቃ መሆናችንን ማሳየት ነበረብን፣ ሰውን ሁሉ በእኩልነት በመቀበልና የሁሉም እኩል አባቶች መሆናችንን በተግባር ማስመስከር ይገባን ነበር፤ የተዛባውን በማረም ትውልዱን ለማዳን ያደረግነው ጥረት የሚያረካ እንዳልሆነ ታዛቢው ሁሉ አይቶብናል፡፡

- ለፈተና የተጋለጡ ልጆቻችን ሁሉ የዜግነት የሃይማኖትና የሰብአዊ መብታቸው እንዲከበር ሰላም ፍቅር፥ ፍትሕ አንድነት በሀገር እንዲነግሥ ሁሉም ድንበሩን ጠብቆ ሕዝቡን የሚያገለግልበት ዓመት እንዲሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ በርትተን መሥራት አለብን። ይህንን ብናደርግ በእውነትም ወደ እግዚአብሔር ተመልሰናል ማለት ነው፤ እኛ ከተመለስን እሱም ወደ እኛ መመለሱ አይጠረጠርም፤ ስለዚህ አሁንም ወደእሱ እንመለስ፡፡

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የግንቦት 2016 ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ #ረቡዕ ይከፈታል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዓመት ሁለት ጊዜያት ከሚካሔዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤያት አንዱ የግንቦት 2016 ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ነው፡፡ ይህ ጉባኤ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ…
#Update #EOTC

" የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻ አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ ፤ የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው " - ቅዱስነታቸው

ግንቦት ወር ላይ የሚካሄደው ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀመረ።
 
የጉባኤውን መጀመር አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው ምን አሉ ?

ቅዱስነታቸው ፥ " ቤተ ክርስቲያን ከፈተና ተለይታ አታውቅም  " ሲሉ ገልጸዋል።

ፈተናው ከተወሰነ አቅጣጫ ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ከብዙ አቅጣጫ እንደሚከባትም አመልክተዋል።

" የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻ አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ " ያሉ ሲሆን " የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው " ብለዋል።

በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች ሲሉ ገልጸዋል።

የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት እንደሆኑ አሳውቀዋል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ፥ " ከጥንት ጀምሮ የነበረ ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ፣ የጸሊአ ሢመትና የጸሊአ ንዋይ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩ ፦
° ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤
° መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል፣
° ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጐደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን #ተሰሚነትና #ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው " ብለዋል።

" እነዚህና እነዚህ የመሳሰሉ ክሥተቶች በውስጥ ሥር በሰደዱ ቁጥር ጉዳትን እያስከተሉ ነው " ያሉት ቅዱስነታቸው " ሰዎች ከኦርቶዶክሳዊ ቀኖና እና ሥርዓት ባፈነገጠ መልኩ ራስን በራስ የመሾም አባዜ እየተለማመዱ ነው፤ እሽቅድምድሙም በዚህ ዙሪያ አይሎአል " ሲሉ ገልጸዋል።

" የፈተናው መንሥኤ ውጫዊ ሳንካ ባይጠፋበትም የውስጣችን ሰዎች ለሱ ምቹ ሆነው መገኘታቸው አልቀረም፤ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ፈተና የማይናቅ ጉዳት እየደረሰባት ነው፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ሰላምዋና አንድነቷ ጥያቄ ላይ ወድቆአል " ሲሉም አሳውቀዋል።

ቅዱስነታቸው፤ " በመልካም አስተዳደርና በቂም በቀል እያሳበቡ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ብሎም ለማፍረስ መሮጥ በማናቸውም መመዘኛ ሚዛን አይደፋም፤ ውሃም አያነሣም " ያሉ ሲሆን " ችግር ሲኖር በመወያየት በጥበብና በሕግ ማረም እንጂ የጋራ ችግርን ለተወሰነ አካል በመለጠፍና እሱን ብቻ ተጠያቂ በማድረግ ንጹህ መሆን አይቻልም " ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት አስከፊ የሆነ በደል መፈጸሙን የገለጹት ቅዱስነታቸው " አሁንም አልቆመም፤ ይሁን እንጂ በደል ዛሬ ብቻ የተጀመረ አድርገን አናስብ፤ ይብዛም ይነስ በደል ፊትም ነበረ፤ ዛሬም አለ፤ ነገም የተለየ ነገር ይኖራል ተብሎ አይታሰብም " ሲሉ ገልጸዋል።

" በደልን በካሣና በዕርቅ በይቅርታና በምሕረት መዝጋት፣ ተመሳሳይ በደል እንዳይፈጸም አስተማማኝ የሆነ ተቅዋማዊ ሥርዓትን ማበጀት መልካም ፈሊጥ ይሆናል፤ በደልንና ጥፋትን ምክንያት አድርገን እስከ ዘለቄታው መለያየትን መምረጥ ግን ራስን በራስ መጉዳት ይሆናል " ሲሉም አስገንዝበዋል።

ጉባኤውም በዚህ ዙሪያ በስፋትና በጥልቀት በመወያየት ሁሉንም ሊያስማማ በሚችል መልኩ ወደ ሰላምና ዕርቅ ሊያደርስ የሚችል ስራ መስራት ይኖርበታል ብለዋል።

(የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #EOTC " የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻ አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ ፤ የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው " - ቅዱስነታቸው ግንቦት ወር ላይ የሚካሄደው ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀመረ።   የጉባኤውን መጀመር አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ…
#EOTC #ETHIOPIA

ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፦

" የማኅበረሰባችን ችግር በቤተ ክርስቲያን ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ በሀገር ደረጃ እየቀጠለ ያለው አለመግባባትም ለጠቅላላ ማኅበረ ሰባችን ፈተና ከሆነ ውሎ አድሮአል፤ የቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ምንጭ ከሆኑትም አንዱና ዕድል ሰጩ ይህ ሀገራዊ አለመግባባት ነው።

በዚህ አለመግባባት ምክንያት ገዳማውያን መነኮሳት፤ መምህራን ካህናት ምእመናን አብያተ ክርስቲያናት ከባድ የሆነ ጉዳት ደርሶባቸዋል ፤ #በሰላም_ወጥቶ_መግባትም_አጠራጣሪ_ሆኖአል ፤ ይህንን ችግር ለመፍታት የሚደረግ ጥረትም ጎልቶ አይታይም፡፡

በመሆኑም ይህ ክሥተት እውን ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ችግር በራሳችን መፍታት የማንችል ሰዎች ነን ወይ ? ለኛስ ከኛ የበለጠ ማን ይመጣልናል ? የሚለውን ጥያቄ ልናነሣ ግድ ነው። ስለዚህ ለሀገር ህልውናና ድኅነት የሚበጅ ነገር እንዲመጣ ቤተ ክርስቲያን ባላት ሃይማኖታዊና ሰብአዊ ኃላፊነት ጠንክራ መስራት ይጠበቅባታል። "

#ኦርቶዶክስተዋሕዶ #ኢትዮጵያ
#የግንቦት_ርክበ_ካህናት_ቅዱስ_ሲኖዶስ_ምልአተ_ጉባኤ

@tikvahethiopia
#Ethiopia🕊

ቅዱስነታቸው ሁሉም ለሰላም በአንድነት እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ።

" የሃይማኖት ተቋሞቻችን ለዘላቂ ሰላማችን " በሚል ርእስ በአዲስ አበባ አንድ መድረክ ተካሂዷል።

በዚህም መድረክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወክጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው ፤ " ጥላቻ፣ ጦርነት፣ ጠብ፣ ክርክር፣ ሞኝ መሆኑን እያወቅን እዚያ ላይ እንንከባለላለን። የሰው ልጅ ህልውናውን ለመጠበቅ ሰላምን መምረጥ እና መከተል ይኖርበታል " ብለዋል።

" የሰላምን እጦት ያመጣነው ራሳችን ነን። ማንም አምጥቶ አልጫነብንም " ያሉ ሲሆን " ሰላም ከሌላ መንፈሳዊም ሆነ ዓለማዊ ተቋማት ምንም መሰራት እንደማይችሉ አውቀን ለሰላም በአንድነት መቆምና ሰላምን መከተል ይኖርብናል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ለዚህም ሁላችንም ከቀደመው እየተማርን መጪውን ሰላማዊ ለማድረግ መጣር ይኖርብናል " ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ፥ " የሔድንበት መንገድ ጎድቶናል ስለሆነም ወደ ሰላም እንመለስ ብለን መወሰን አለብን። ለዚህም ሁላችንም ወደ አእምሮችን ተመልሰን ሰላምን እንከተላት " ሲሉ አባታዊ ጥሪ አቅርበዋል።

#EOTC
#Ethiopia

@tikvahethiopia
" ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷል ! " - ቋሚ ሲኖዶስ

ቋሚ ሲኖዶስ ፥ ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የምሕላ ጸሎት እንዲፈጸም አወጀ።

በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ በጾም በጸሎት በመወሰን ፣ ምሕላ ይታወጃል።

ምሕላ የሚታወጀው ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ሁሉን ማድረግ ወደሚችለው እግዚአብሔር ምልጃን ለማቅረብ ነው።

"ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷል " ያለው ቋሚ ሲኖዶስ " በእውነት የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ እግዚአብሔር ፦
- መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣
- ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣
- ለቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት፣
- ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መነሻነት ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል " ብሏል።

በዚህም በመላ የሀገራችን ክፍልና ሌሎች አህጉራተ ዓለም የሚገኙ መነኰሳትና መነኰሳይያት ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት የገዳማት ኅብረቱን ጥሪ ተቀብለው የምሕላ ጸሎት እንዲያደርሱ ጥሪ አቅርቧል።

በጤና ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀርም እስከ ዕርበተ ፀሐይ በመጾም ሱባኤ እንዲይዙ ፣ ቋሚ ሲኖዶስ ከአደራ ጋር አሳስቧል።

ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና ምእመናን ሀገራዊ ሰላምን፣  መረጋጋትን እና ፍቅር አንድነትን ለማስፈን ጾምና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የሚያደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርገውት መደበኛው ሥራቸውን በያሉበት ቦታ እየሰሩ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆነው በጾም በጸሎት እንድተጉ ጥሪ ተላልፏል።

https://telegra.ph/EOTC-07-12

#ETHIOPIA #EOTC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ደመራ ዛሬ ከሰዓታት በኃላ ለሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ዝግጅቶች ወደመጠናቀቃቸው ነው። ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ትላንት በዓሉን በማስመልከት መልዕክት አስተላልፈው ነበር። በዚህም በዓሉ በድምቀት ፣ባማረና በሰመረ መልኩ ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ ሕዝበ ክርስቲያኑ በንቃትና በሕብረት…
#EOTC

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፦

" ... አንዳንድ ጊዜ በዓልን ምክንያት በማድረግ መጠጦች ይኖራሉ።

በዓል ለመጠጥ ምክንያት ሊሆን አይችልም።

በዓል ስንል መንፈሳዊ በዓላት ሁል ጊዜ ምክንያቶቻችን ፦
- ለፅድቅ ነው
- ለሰላም ነው
- የተጣላ የምናስታርቅበት ፣
- የራቀውን የምናቀርብበት፣
- የተቸገረውን የምንረዳበት
- ያላመነውን እምነት እንዲኖረው የምናስተምርበት ፣
- ከእግዚአብሔር የራቀውን ከእግዚአብሔር ጋር የሚታረቅበትን ንስሃ የሚገባበትን ስራ ለመስራት የሚያስፈልጉን ነገሮች የተዘረዘሩ እንጂ መጠጥ አይደለም።

መጠጥ ክፉ ምኞትን ያመጣል፣ የጉልበት ስሜትን ያመጣል፣ መጠጥ ስካርን ያስከትላል፤ ከዚያ በኃላ የሚሰሩትንም የሚናገሩትንም አለማወቅ ይመጣል።

አንዳንድ ጊዜ በምንሰማው በመንፈሳዊ በዓላቶቻችን መንፈሳዊ ተብለው ሲከበሩ በመጠጥ ኃይል አላስፈላጊ ግጭቶች ተፈጥረው የብዙ ንጹሃን ህይወት ደም የሚፈስበት ጊዜ ይኖራል ፤ ይህ በየትኛውም ቦታ ነው ፤ ስለዚህ ይሄ ጥቅም ስለሌለው ጥቅማችን እኛ በዓሉን በማክበር ካላስፈላጊ ክፉ ምኞት ሳይሆን በጎ ምኞት ፦
° ያልቆረበ ለመቁረብ ፣
° ያልሰገደ ለመስገድ፣
° ከእግዚአብሔር የራቀ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ፣
° ሰላምን ያጣ ሰላምን ለማግኘት ፣
° የተጣላ ለመታረቅ ፣
° ያጣ ሰርቶ ጥሮ ግሮ እግዚአብሔር ስራውን ባርኮለት እራሱን ችሎ ከድህነት ተላቆ የሚኖርበትን እግዚአብሔርን የሚማፀንበት ስራ መስራት እስከተቻለ ድረስ ሁሉ ነገር ውጤታማ ያደርገናል። "

#EOTC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አረጋዊ ካህኑ ከነባለቤታቸው 4 ቤተሰቦቻቸው ጋር በአንድ ቀን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል " - የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት መ/መ/ቀ/ወልደ ኢየሱስ አያሌው የተባሉ አረጋዊ ካህን ከነባለቤታቸው 4 ቤተሰቦቻቸው ጋር በአንድ ቀን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተገልጿል። መ/መ/ቀ/ወ/ኢየሱስ…
#EOTC

በአረጋዊው መልአከ/መ/ ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌውና አራት ቤተሰባቸው ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግድያን በልዩ  ሁኔታ እንደሚከታተለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት አሳውቋል። 

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሉሜ (ሞጆ )  ወረዳ ቤተ ክህነት  በቢቃ ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ  ለ41 ዓመታት ያህል ከድቁና እስከ ደብር አስተዳዳሪነት ድረስ በትኅትና ሲያገለግሉ የቆዩት መልአከ /መ/ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌ ከባለቤታቸውና ከሦስት ልጆቻቸው ጋር ባሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ይታወቃል።

ግድያው " ማንነታቸው ለጊዜው አልታወቀም " በተባሉ ኃይሎች መፈጸሙን የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከትን ዋቢ በማድረግ ያመለከተው ጠቅላይ ቤተክህነት ግድያው በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ የተፈጸመ ነው ብሏል።

ጠቅላይ ቤተክህነት በዚህ አሰቃቂ ግድያ ሕይወታቸውን ባጡ የቤተክርስቲያኗ አገልጋዮችና ቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

" ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባህርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የደረሰውን አስደንጋጭ ሀዘን ከሰሙ ጊዜ ጀምሮ ጉዳዩን በልዩ ትኩረት እየተከታተሉት ይገኛሉ " ብሏል።

ዝርዝር ሁኔታውን በሚመለከት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገርና እስከ መጨረሻው ጫፍ በመድረስ ሕጋዊ እልባት  እንዲያገኝ እንደሚደረግ ገልጿል።

@tikvahethiopia