TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ፦ የ2017 ኢሬቻ ' ሆራ ፊንፊኔ ' በዓል ዋዜማ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ #ኢሬቻ2017 #Irreecha2017

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ለጋራ ደህንነት ፍተሻዎች ስለሚኖሩ ትብብር አድርጉ " - ፖሊስ

በአዲስ አበባ በተለይም የኢሬቻ ' ሆራ ፊንፊኔ ' በዓል በሚከበርበት አካባቢ እና መስመሮች ላይ ፍተሻ አለ።

በዓሉን ለመታደም ወደ ስፍራ የሚመጡ ታዳሚዎች ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ መኖሩን ተገንዝበው አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር እንዲያደርጉ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

#ኢሬቻ2017 #Irreecha2017

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የሞቱት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው " - በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰሞኑን በጅቡቲ የባህር ዳርቻ በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ በአደጋው የሞቱት ዜጎች በሙሉ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው መረጋጋገጡን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡ መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም ማምሻውን ከየመን ወደ ጅቡቲ 320 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞች ይዘው የተነሱት ሁለት የስደተኞች ጀልባዎች በጅቡቲ ባህር…
" ... ሕገወጥ አስተላላፊዎቹ ጀልባዎቹ ባሕሩ መሃል ላይ ሳሉ ፍልሰተኞቹን እንዲወርዱ ነው ያስገደዷቸው " - አይኦኤም

በቅርቡ በጂቡቲ ባሕር ዳርቻ ሰጥመው የሞቱት ፍልሰተኞችን ጉዳይ በተመለከተ የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ለቪኦኤ በሰጠው ቃል " ፍልሰተኞቹ ባሕር ውስጥ የሰጠሙት ጀልባዎቹ ዳር ሳይደርሱ ሕገ ወጥ አስተላላፊዎቹ ፍልሰተኞቹን እንዲወርዱ በማስገደዳቸው ነው " ብሏል።

የአይኦኤም የአፍሪካ ቀንድ እና ደቡባዊ አፍሪካ ዲሬክተር ፍራንትዝ ሰለስቲን ፥ " በሁለት ጀልባዎች ውስጥ ተሳፍረው ከነበሩት 310 ፍልሰተኞች ውስጥ 48 ሲሞቱ፣ 154 የሚሆኑት ደግሞ ከአደጋው ተርፈዋል።  108 ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም ወይም ሕይወታቸው አልፏል " ሲሉ ተናግረዋል።

በአንደኛው ጀልባ ላይ 100 ፍልሰተኞች ተሳፍረው የነበር ሲሆን በሁለተኛው ጀልባ ላይ ደግሞ 210 ፍልሰተኞች ተሳፍረው ነበር።

ፍልሰተኞቹ ከየመን ወደ ጂቡቲ በማቅናት ላይ የነበሩ ሲሆን፣ የጂቡቲን ባሕር ዳርቻን በመቃረብ ላይ ሳሉ ሕገወጥ አስተላላፊዎቹ ጀልባዎቹ ባሕሩ መሃል ላይ ሳሉ ፍልሰተኞቹን እንዲወርዱ ማስገደዳቸውን ሃላፊው ተናግረዋል።

በርካታ ቁጥር ያላቸውና መዋኘት ያልቻሉት ፍልሰተኞች ሰጥመው መምታቸውን አስታውቀዋል።

ባለፈው ሰኞ በተፈጠረው በዚህ ክስተት እስከ አሁን ያልተገኙትን በተመለከተ ፍለጋው መቀጠሉን ነገር ግን ከተቆጠሩት ቀናት አንጻር ሕይወታቸው ሊያልፍ ይችላል ብለው እንደሚሰጉ ፍራንትዝ ሰለስቲን ተናግረዋል።

በሕይወት የተረፉት ፍልሰተኞች ድርጅቱ በጂቡቲ መጠለያና የሕክምና ዕርዳታ እንደሰጣቸው አመልክተዋል።

በባሕር መሥመሩ የሚተላለፉት ኢትዮጵያያን እና ሶማሊያውያን እንደሆኑ፣ በአብዛኛው ግን #ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ ለቪኦኤ ሬድዮ ገልጸዋል።

በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰሞኑን በጂቡቲ ባሕር ዳርቻ ሰጥመው የሞቱት ፍልሰተኞች ሁሉም ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ ማሳወቁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#MPESASafaricom

የ5% ተመላሻችንን ይዘን በሀገር ዉስጥ በረራ ወዳሰብንበት እንቅዘፍ ፤ በM-PESA ከፍለን ጉዞውም ፈጣን ፤ ተመላሹም የኛ!

የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

 #FurtherAheadTogether
Baga Ayyaanaa #Irreechaa geessan !

Ayyaana Gaari ! Happy Irreechaa !

#Irreechaa2017

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም የኢሬቻ ' ሆራ ፊንፊኔ ' በዓል አከባበር በአዲስ አበባ #Irreechaa2017

Photo Credit - Vist Oromia & Social Media

#AyyaanaGaari ! #HappyIrreechaa !

@tikvahethiopia