TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " የህወሓትን ህጋዊነት መመለስ አስመልክቶ ከፌደራል መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ፓነል የሚወያይ ልኡክ እንደ አዲስ ይደራጃል ሲል " በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት ገለጸ። በህወሓት ምክትል ሊቀመንበር የሚመራው ህወሓት ከመስከረም 20 አስከ 22 /2017 ዓ.ም ለሦስት ቀናት ያካሄደውን የማእከላዊ ኮሚቴ እና የከፍተኛ ካድሬዎች ስብሰባ ማጠቃለሉ በማስመልከት የአቋም መግለጫ አውጥቷል። …
#TPLF

" ህዝብ በማደናገር ላይ ይገኛሉ " - በዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የማዕከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን

በህወሓት አመራሮች መካከል ያለው ክፍፍል ተቀራርቦ ከመፈታት ይልቅ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ እየተካረረ መጥቷል።

" ከህወሓት አባልነት የተባረሩ በማንኛውም ቦታና ጊዜ በህወሓት ስም ፓለቲካዊ ስራና እንቅስቃሴ ማድረግ አይችሉም " ሲል በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የማእከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን አሳውቋል።

የቁጥጥር ኮሚሽኑ ባወጣው የአቋም መግለጫ ፥ ጉባኤ ያካሄደው በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት " ህጋዊ ነው " ብሏል።

" የህወሓት መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 8 ቁጥር 4 በውሳኔ አሰጣጥ ላይ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው በብዙሃን ተገዢ መሆን እንዳለባቸው ያስቀምጣል " ያለው መግለጫው " በዚሁ መሰረት በ14ኛው የህወሓት ጉባኤ ከጠቅላላ ተሳታፊ 83 በመቶ ጉባኤተኛ የተገኘበት " ህጋዊ ነው !! " ብሎታል።   

ስለሆነም " ህጋዊ አለመሆኑን እያወቀ ህጋዊ መስሎ ማደናገር አግባብነት እና ተቀባይነት ያለው አይደለም " ሲል በምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ህወሓት ከሷል።

" ከጉባኤ ራሳችን አግልለናል ወይም ወደ ጉባኤ አንገባም ያሉት በድርጅቱ መተዳደሪያ ህገ ደንብ መሰረት ከድርጅት አባልነታቸው እንደተባረሩ እውነት ነው ፤ በተግባር ግን የህወሓት ስም ፣ አርማ ፣ ሎጎ እና የድርጅቱ ሃላፊነት በመጠቀም ህዝብ በማድናገር ላይ ተጠምደዋል " ብሏል የማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን መግለጫ።  

" ከጉባኤ በመሸሽ ሁሉም አይነት ክህደት በድርጅቱ ላይ ፈፅመህ ስታበቃ እኔ ህወሓትን ነኝ የሚል የከሰረ የማደናገር  ፓለቲካ ማራመድ ህጋዊ ፣ ፓለቲካዊ ፣ ሞራላዊ እና ታሪካዊ ተጠያቂነት የሚያስከትል ሆኖ አግኝተነዋል " ሲል አክሏል።

" የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ከድርጅቱ የተባረሩት አካላት #ከያዙት_ፓለቲካዊ_ስልጣን_እንዲነሱ ፤ በህወሓት ስም የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያቆሙ የማድረግ ሃላፊነቱን እንዲወጣ እንጠይቃለን " ብሏል።

ቁጥጥር ኮሚሽኑ ፥ " ህዝብ በማድናገር ላይ ይገኛሉ " ሲል ክስ ያቀረበባቸው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን የህወሓት ቡድን " ህዝብ እንዲታገላቸው " ሲል ጥሪ አስተላልፏል። 

" ህወሓት ለ2 እንደተከፈለ ተደርጎ የሚቀርበው ተረክ ከህወሓት አልፎ ህዝብ ስለሚጎዳ በፍጥነት መታረም አለበት " ብሏል።

በምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት  መስከረም 23 /2017 ዓ.ም ባወጣው  መግለጫ  " የህወሓት ህጋዊነት መመለስ አስመልክቶ ከፌደራል መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት ፓነል የሚወያይ ልኡክ እንደ አዲስ ይደራጃል " ማለቱን መዘገባችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተጠናቋል " - ፖሊስ

በአዲስ አበባ የተከበረው የ2017 ዓ/ም የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ፥ " በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብና አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እና ከጎረቤት ሀገራት የመጡ እንግዶች እንዲሁም የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች የታደሙበት የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተጠናቋል " ሲል ገልጿል፡፡

ለበዓሉ በሰለም መጠናቀቅ ላደረጉት አስተዋጽኦ ፦
- ለአባገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች፣
- ለበዓሉ ታዳሚዎች፣
- ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣
- ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎች
- ለሰላም ሠራዊት ወጣቶች
- ስምሪት ተሰጥቷቸው ኃላፊነታቸውን በትጋት ለተወጡ የፀጥታና ደኅንነት አካላት ምስጋና አቅርቧል።

ነገ መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ የሆራ አርሰዲ የኢሬቻ በዓል ይከበራል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

መንገዶች ተከፍተዋል።

ከኢሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ተዘግተው የነበሩ መንገዶች ተከፍተዋል።

@tikvahethiopia
" ለአንድ ዓመት ሞከርኩት "

ዛሬ በይፋዊ የፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የX ገጽ ላይ የወጣው ፅሁፍ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።

ፅሁፉ " እነ ጥላሁን ገሠሠ : ቴዲ አፍሮ : አሊ ቢራ : ማህሙድ አህመድ ... ድንቅ ድምጻውያን መካከል ናቸው " ይላል።

ቀጥል አድርጎ ፥ " ' የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው : መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው ' ማህሙድ ' ዝምታ ነው መልሴ' ን ሲያዜም " ሲል ይገልጻል።

መጨረሻ ላይ " ለአንድ ዓመት ሞከርኩት " የሚል ያልተቋጨ ፅሁፍ ታክሎበታል።

ፕሬዜዳንቷ ገጽ ላይ ፅሁፉ ስለምን ጉዳይ እንደሆነ በግልጽ የተብራራ ነገር አልሰፈረም።

በተረጋገጠው አካውንታቸው የወጣውን ፅሁፍ ግን በርካቶች እየተቀባበሉት ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
ኮሚሽነር ግርማይ ማንጁስ !

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ እና ህይወታቸው እስካላፈበት ጊዜ ድረስ የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ግርማይ ማንጁስ) መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ኮሚሽነር ግርማይ ባደረባቸዉ ህመም ምክንያት ህክምናቸውን ሲከታተሉ በቢቆዩም በተወለዱ በ60 ዓመታቸው ህይወታቸው አልፏል።

ከነሐሴ 01 ቀን 1994 ዓ/ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ከዋና መምሪያ እስከ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ኃላፊነት ሠርተዋል።

እስከ ህልፈታቸው ጊዜ ድረስም የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ህዝባቸውን ሲያገለግሉ ነበር።

ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ግርማይ ማንጁስ) የ3 ሴት ልጆች አባት ነበሩ።

ዛሬ አስክሬናቸው በልዩ ወታደራዊ አጀብ እና ሃይማኖታዊ ስነርዓት ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ተሸኝቷል።

የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው ነገ እሁድ ከጠዋቱ  3፡00 ሰዓት በመቐለ ጽርሃ አርያም ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸም ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

#FederalPolice #Tigray #CommissionerGirmayKebede

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ለአንድ ዓመት ሞከርኩት " ዛሬ በይፋዊ የፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የX ገጽ ላይ የወጣው ፅሁፍ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። ፅሁፉ " እነ ጥላሁን ገሠሠ : ቴዲ አፍሮ : አሊ ቢራ : ማህሙድ አህመድ ... ድንቅ ድምጻውያን መካከል ናቸው " ይላል። ቀጥል አድርጎ ፥ " ' የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው : መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው ' ማህሙድ ' ዝምታ ነው መልሴ'…
#ኢትዮጵያ

ዛሬ በኢትዮጵያ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ትልቅ መነጋገሪያ የሆነው በፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ X ኦፊሻል ገጽ ላይ የሰፈረው ፅሁፍ ነው።

ፅሁፉ ላይ የማህሙድን ዘፈን ' ዝምታ ነው መልሴ 'ን በማንሳት " የሰው ልጅ ሆዱ ሲከፋው ጊዜም እንደ ሰው ሲገፋው: መሄጃ መውጫ ሲጠፋው ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው " የሚለው ግጥም ተጋርቷል። መጨረሻ ላይ " ለአንድ አመት ሞከርኩ " የሚልም ሰፍሯል።

ፅሁፉ ስለምን ጉዳይ እንደሆነ ፤ ለምንስ ይህንን ግጥም ነጥሎ እንደተጻፈ በግልጽ የሚያብራራው ነገር የለም።

ያም ሆኖ ግን ፅሁፉን ላይ በርካቶች የየራሳቸውን አስተያየት እየሰጡ ይገኛሉ።

አንዳንዶች ፤ " አሁን ባለው ስርዓት በከፍተኛ ጫና ውስጥ ወድቀው ነው እየሰሩ ያሉት ፤ በተለያዩ ጉዳዮች አለመግባባት ውስጥም እንደነበሩ ብዙ ጊዜ በሚዲያ ይሰማ ነበር ፤ ለመናገር እንኳን እድል የላቸውም ፤ ባገኙት አጋጣሚ ግን በገደምዳሜው ስሜታቸውን ስለ ሀገራቸው ይናገሩ ነበር ፤ አሁንም ቦታውን ሲለቁ ስለዚህ ስርዓት ብዙ የሚናገሩት ይኖር ይሆናል " የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።

አንዳንዶች፤ " በዚህ ልክ ትልቅ የስልጣን እርከን ይዘው ህዝብን ግራ የሚያጋባ ድፍንፍን ያለ ፅሁፍ በገጻቸው መጋራቱ ሳያንስ እውነትም እሳቸው መሆናቸውን በግልጽ አለማብራራታቸው ትክክል አይደለም ፤ ችግር ካለም እውነታውን ለህዝብ ማሳወቅ አለባቸው እንዲህ የዘፈን ግጥም ከሚያስቀምጡ " ብለዋል።

ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ " የ6 ዓመት የስልጣን ዘመናቸው ሲያበቃ ይህን አይነት ነገር በገጻቸው መፃፋቸው የህዝብ ተቀባይነት ለማግኘት ነው እስከዛሬ በሀገሪቱ ብዙ ነገር ብዙ ግፍ ሲፈጠር ባላየ ሲያልፉ ነበር ፤ አንዳንዱን ደግሞ እየመረጡ ሲናገሩ ነበር ፤ ለምን አሁን ? በዚህ ስልጣን እንደማይቀጥሉ ስለሚያውቁ ነው ፤ ስልጣንም መልቀቅ ከነበረባቸው ቀድሞ ተናግሮ እንጂ አሁን ላይ ይህን አጀንዳ ለህዝብ መስጠት ትክክል አይደለም ፤ ጊዜያቸው አብቅቷል ይሰናበታሉ ፤ እሱንም ስለሚያውቁ ነው " ሲሉ ፅፈዋል።

በኢትዮጵያ የፕሬዜዳንት ስልጣን ዘመን 6 ዓመት ሲሆን ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ወደ ስልጣን የመጡት ጥቅምት 15 ቀን 2011 ዓ/ም ላይ ነበር።

ሌሎች ደግሞ " እንዲያው በደፈናው ድምዳሜ ላይ ከመድረስ የእሳቸውን ሙሉ ሀሳብ በትዕግስት ጠብቆ መስማት ይገባል " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ ግን ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ የፕሬዝዳንትነት የስልጣን ድርሻው ምንድነው ? ፕሬዝዳንት የሚኮነው እንዴት ነው ? ምን ምን ይሰራል በዝርዝር ? ሲሉ የጠየቁ አሉ።

ለዚህ ምላሽ ይሆን ዘንድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ህገ መንግስቱ ስለ ፕሬዜዳንቱ የሚለውን ከዚህ በታች አቅርቧል።

የኢፌዲሪ ህገ መንግስት ስለ ሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት ስልጣንና ተግባር ምን ይላል ?

(የኢፌዴሪ ህገ መንግስት)

ምዕራፍ ሰባት
ስለ ሪፐብሊኩ ኘሬዚዳንት
አንቀጽ 69
ስለ ኘሬዚዳንቱ

ኘሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ርዕሰ ብሔር ነው፡፡

አንቀጽ 70
የፕሬዜዳንቱ አሰያየም
1. ለፕሬዜዳንትነት ዕጩ የማቅረብ ሥልጣን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው።
2. የቀረበው ዕጩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ ከተደገፈ ፕሬዜዳንት ይሆናል።
3. የምክር ቤት አባል ፕሬዜዳንት ሆኖ ከተመረጠ የተወከለበትን ምክር ቤት ወንበር ይለቃል።
4. የፕሬዜዳንቱ የሥራ ዘመን 6 ዓመት ነው። አንድ ሰው ከሁለት ጊዜ በላይ ለፕሬዜዳንትነት ሊመረጥ አይችልም።

አንቀጽ 71
የኘሬዚዳንቱ ሥልጣንና ተግባር
1. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽኑን ምክር ቤት ዓመታዊ የጋራ ስብሰበባ ይከፍታል፡፡
2. በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቃቸው ሕጐችና ዓለምአቀፍ ስምምነቶች በነጋሪት ጋዜጣ ያውጀል፡፡
3. ሀገሪቷን በውጭ ሀገሮች የሚወክሉትን አምባሳደሮችና ሌሎች መልክተኞች በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት ይሾማል፡፡
4. የውጭ ሀገር አምሳደሮችንና የልዩ መልዕክተኞችን የሹመት ደብዳቤ ይቀበላል፡፡
5. በሕግ መሰረት ኒሻኖች እና ሽልማቶችን ይሰጣል፡፡
6. በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕግ በተወሰነው መሰረት ከፍተኛ የውትድርና ማዕረጐችን ይሰጣል፡፡
7. በሕግ መሰረት ይቅርታ ያደርጋል፡፡

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም የኢሬቻ ሆራ አርሰዲ በዓል ዋዜማ በቢሾፍቱ ከተማ #Irreechaa2017 #HoraaHarsadee

Photo Credit - Visit Oromia

@tikvahethiopia