TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን⬇️

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከማሺ ዞን እና በደቡብ ክልል ሸካና ከፋ ዞኖች የተከሰቱት #ግጭቶች ከቁጥጥር ውጪ ከመሆናቸው አስቀድሞ መንግስት አስፈላጊውን #እርምጃ እንዲወስድ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጠየቀ።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር አዲሱ ገብረእግዚአብሄር #ከሃዋሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ በእነዚህ ቦታዎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ እና ግጭቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውቀዋል።

በተለይም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ካማሺ ዞን በሚገኙ አምስት ወረዳዎች ላይ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ነው የገለፁት።

በእነዚህ ሶስት ዞኖች የዜጎች የመንቀሳቀስ እና ንብረት የማፍራት #መብት መገደቡን አስታውቀዋል።

ኮሚሽኑ ወደ ሶስቱም አካባቢዎች መርማሪዎችን ቢልክም ምርመራ እንዲያደርጉ የሚያስችል ሁኔታ አለመኖሩን እና መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን ነው የተናገሩት።

የፀጥታ አካላትም ግጭቶቹን ለማስቆም ተገቢውን እርምጃ እየወሰዱ አለመሆናቸውን ከአካባቢዎቹ መርማሪዎች ለኮሚሽኑ በስልክ ያደረሱት መረጃ እንደሚጠቁምም ገልፀዋል።

አሁን ላይ በይፋ በግጭቶቹ #የሞቱ እና #የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥርንም በዚህ ምክንያት በአግባቡ ማጣራት አለመቻሉን በማንሳት ይህም የችግሩን ስፋት እንደሚያሳይ ተናግረዋል።

በመሆኑም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ችግሩ በተፈጠረባቸው እነዚህ አካባቢዎች ገብቶ የማረጋጋት ፣ ህግ እና ስርዓትን እንዲሁም የዜጎችን መብት የማስከበር ስራ እንዲያከናውን ነው የጠየቁት።

እስካሁን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ግጭት ካለባቸው አምስት ወረዳዎች መካከል በሁለቱ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በመግባቱ የተሻለ ሁኔታ እየታየ መሆኑን ዶክተር አዲሱ አስታውቀዋል።

በእነዚህ መከላከያ በገባባቸው ቦታዎችም ኮሚሽኑ ከነገ ጀምሮ ምርመራ እንደሚጀመር ነው ያስታወቁት። ምርመራውንም በኃላፊነት መንፈስ ያከናውናል ብለዋል።

ዶክተር አዲሱ በመግለጫቸው በተለያዩ አካባቢዎች እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን መነሻ በማድረግ ችግሮቹ ከመከሰታቸው በፊት አስቀድሞ ለመከላከልና ሲከሰቱም በዘላቂነት ችግሮቹን ለመፍታት የሚያስችል ጥናት ኮሚሽኑ አድርጎ ለመንግስት ማቅረቡን አስታውቀዋል።

ምንጭ ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጀርባ ያለው አካል⁉️

አሁን አሁን በተደጋጋሚ የምንሰማው ለሚደርሱት ችግሮችና ለሚታዩት #ግጭቶች ማንነቱ #የማይታወቅ፣ በጀርባ #ተደብቆ የሚገፋ ሀይል
መኖሩ ነው፡፡ በግጭቶች ሰው ሲሞት፣ ፀጥታ ሲታወክ፣ አደጋ ሲደርስ፣ ከኋላ ሆነው አቀነባብረዋል የሚባሉ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች “አሉ” ይባላል እንጂ ማንነታቸው ይፋ ሆኖ ችግር ፈጣሪው አካል የሚታወቀው መቼ ነው ? ሁልጊዜ የማይታወቅ ተጠያቂ ማበጀት እያደር መተማመንን አያጎድልም ወይ ? በዚህ ዙሪያ የሸገር 102.1 ጋዜጠኛ ከባለሙያ ጋር ያደረገውን ቆይታ ከላይ አድምጡት።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጦር መሳሪያ ዝውውር‼️

የህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎች ዝውውር ጉዳይ ከአሳሳቢነት አልፎ #አስጨናቂ ወደ መሆን ደረጃ ያለፈ ይመስላል፡፡

መገናኛ ብዙሃን በተከታታይ ሳምንታት የሚዘግቡት በሺ የሚቆጠሩ ሽጉጦች፣ በመቶ የሚቆጠሩ የነፍስ ወከፍና የቡድን የጦር መሳሪያዎች፣ በ100 ሺ የሚቆጠሩ ጥይቶች መያዛቸውን ሆኗል፡፡

ቁጥሩ የሚያመለክተው የተያዙትን ብቻ እንጂ ከፀጥታ ሃይሎች ዓይን አልፎ የገባውና የተበተነው የጦር መሳሪያ ምን ያህል እንደሆነ አይታወቅም፡፡

ኢትዮጵያ በየአካባቢው በሚነሱ #ግጭቶች በምትታመስበት በአሁኑ ወቅት የጦር መሳሪያዎች ስርጭት አደጋውን እንዳያባብሰው ያስፈራል፡፡

ለመሆኑ የጦር መሳሪያዎቹ ዝውውርን መቆጣጠር ያልተቻለው ስለ ምንድን ነው?በአዘዋዋሪዎቹ ላይ ሕጉ የሚጥለው ቅጣትስ ማረሚያ በሚባል ደረጃ የተቀረፀ ነው ወይ? ከላይ ያለውን የሸገር FM 102.1 ወሬ በጥሞና ያዳምጡ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሶሳ🔝በቤኒሻንጉል ጉመዝ ክልል በአሶሳ ከተማ በክልሉ መስተዳድር ም/ቤት ትላንት በቀን 7/03/2011 ዓ/ም አክቲቪስት #ጃዋር_መሀመድና አቶ #በቀለ_ገርባ ክክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አሻዲል ሀስን፣ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ከአሶሳ ከተማ እና አካባቢዋ ማሀበረስብ ጋር በምዕራብ ኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉመዝ ክልል ድንበር አካበቢዎች በሚከሰቱ #ግጭቶች ዙሪያ መፍትሄ በሚያገኘበት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በመስቃንና ማረቆ አካባቢዎች በተደጋጋሚ እየተፈጠሩ ላሉ #ግጭቶች መንግስት ዘላቂ #መፍትሄ እንዲያፈላልግ የግጭቱ ተጎጂዎች ጠይቀዋል። ከሰሞኑ በዚህ አካባቢ በተፈጠረዉ ግጭት የዜጐች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ከቀዬአቸዉ ተፈናቅለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጥላቻ ንግግር ላይ አዲስ ህግ ሊወጣ ነው‼️

ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግር ላይ አዲስ ህግ ልታወጣ መሆኗን አስታወቀች።

ጠቅላይ አቃቤ ህግ #የጥላቻ_ንግግርን የተመለከተና ተጠያቂነትን የሚያመጣ አዲስ ረቂቅ ህግ እያዘጋጀ መሆኑን ገልጿል።

የጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ አቶ #ዝናቡ_ቱኑ እንደገለጹት በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተስፋፉ የመጡት ሃላፊነት የጎደላቸው መልዕክቶችና የሀሰት ወሬዎች በሀገሪቱ ለሚከሰቱ ግጭቶች ምክንያት በመሆናቸው መንግስት ይህን አደጋ ለማስወገድ ህጋዊ ተጠያቂነት እንዲኖር የሚያስችል አሰራር በማርቀቅ ላይ ነው።

ህጉ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እንዳይጋፋ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ምሁራን አስተያየት በመስጠት ላይ ናቸው።

የጥላቻ ንንግሮች የዓለማችን የወቅቱ ፈተና እንደሆኑ ይገለጻል።

በሃገረ አሜሪካ የጥላቻ ንግግር ሀሳብን በነጻነት ከመግለጽ መብት ጋር ተያይዞ ሰፊ የውይይት አጀንዳ የከፈተ ጉዳይ ነው።

አሜሪካ በህገመንግስቷ የመጀመሪያ ክፍል ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ሳይሸራረፍ እንዲከበር ማድርጓ ለጥላቻ ንግግር መበራከት አስተዋጽኦ አድርጓል የሚሉ ወገኖች ቢኖሩም ህዝብን ከህብ የሚያጋጩ፣ ሁከትን የሚፈጥሩና ሰላምን የሚያውኩ የጥላቻ ንግግሮች ላይ ግን አሜሪካ ጠበቅ ያለ ርምጃ ትወስዳለች።

የማህበራዊ ሚዲያዎች መምጣትና መስፋፋት ለጥላቻ ንግግሮች መበራከት አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚገልጹ የዘርፉ ባለሙያዎች ዓለማችን ከገጠሟት የጊዜው ብርቱ አደጋዎች አንዱ እንደሆነም ያስምራሉ።

ኢትዮጵያም የጥላቻ ንግግሮች ሰላባ ለመሆኗ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚከሰቱ #ግጭቶች አይነተኛ ማሳያ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የጥላቻ ንግግሮችና #ሀሰተኛ_ወሬዎች በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከሰቱ ላሉ ግጭቶች ሰበብ ምክንያት መሆናቸውን እንዳመነበት ገልጿል።

አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ አቶ ዝናቡ ቱኑ ይህን አደጋ ለመቀነስ የጥላቻ ንግግሮች ላይ ገደብና ተጠያቂነት የሚያሰፍን ህግ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።

አቶ ዝናቡ እንዳሉት ኢትዮጵያ አዲስ የተስፋ ምዕራፍ ላይ መገኘቷን ተከትሎ ለጀመረችው የለውጥ ጎዳና እንቅፋት የሚሆኑትን ጉዳዮች በመለየት በህግ ልትፈታቸው ተዘጋጅታለች።

በተለይም ለህዝብ የሚቀርቡ ንግግሮችና የሚተላለፉ መልዕክቶችን በተመለከተ ሃላፊነትና ተጠያቂነት ማስፈን እንደሚገባ ነው አቶ ዝናቡ የገለጹት።

የማህበራዊ ሚዲያዎች መበራከት ከጥቅማቸው እኩል ጉዳቶችንም ማስከተላቸውን የጠቀሱት አቶ ዝናቡ በጥላቻ ንግግሮችና ሃላፊነት በጎደላቸው እንቅስቃሴዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም ብለዋል።

በመሆኑም መንግስት እነዚህን ግጭት ቀስቃሽና ሰላም አዋኪ የሆኑ የጥላቻ ንግግሮችን ለማስቆም ረቂቅ ህግ በማዘጋጀት ላይ ሲሆን በቅርቡ ተጠናቆ ለሚመለከተው አካል ለውይይት እንደሚቀርብ ገልጸዋል።

አንዳንድ ምሁራን ጉዳዩ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እንዳይጋፋው ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።

በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚተላለፉ መልዕክቶችን ሳንሱር ማድረግ አስቸጋሪ እንደሆነ በመግለጽ ህጉ በምን ዓይነት መልኩ ችግሩን ለማስቀረት እንዳሰበ ለማወቅ አስቸጋሪ እንደሆነም ይገልጻሉ።

የጥላቻ ንግግሮችን በህግ ለማስቀረት የሚቻል ቢሆንም ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገው ነው ምሁራን የሚገልጹት።

ምንጭ፦የኢትዮጵያ ሳተላይት ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አምቦ🔝

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልልና በኦሮሚያ አዋሳኝ #ሊሙ ወረዳ #አርቁምቤ በሚባል አካባቢ በታጣቂዎች የተገደሉ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት በአምቦ ከተማ ሽኝት ተደረገላቸው። ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልልና በኦሮሚያ አዋሳኝ ወረዳዋች ቢያንስ 35 የኦሮሚያ ፖሊስና የኦሮሚያ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ አባላት በታጣቂዎች ተገለዋል።

በሌላ በኩል...

ነቀምትንና ሻምቡን ጨምሮ በምዕራብ ኦሮሚያ ከተሞች ሰልፎች ተካሂደዋል። ሰልፈኞቹ ለዜጎች ሞትና መፈናቀል ምክንያት የሆኑ፥ በክልሎች ወሰን አካባቢ የሚፈጠሩ #ግጭቶች እንዲቆሙ ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚነሱ #ግጭቶች የብሄር ልዩነት ምክንያት አለመሆኑን ትምህርት ሚንስትሯ #ሒሩት_ወልደማርያም አስታውቀዋል፡፡ ሚንስትሯ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መነሻ መክንያቶቹ ከፖለቲካ አጀንዳና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ የግለሰቦችን ጠብ ከብሄር ማንነት ጋር ማያያዝ ግን ይታያል፡፡ በተማሪዎች ግጭት ሳቢያ ረዘም ላለ ጊዜ ትምህርት ተቋርጦበት የነበረው ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ጥር 1 ይከፈታል፡፡

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአገሪቱ የሚታዩትን #ግጭቶች ለማስቆም ወጣቱ በውይይት የሚያምንና በምክንያት ላይ የተመሰረተ ሥራ ሊያከናውን እንደሚገባ ተገለፀ፡፡በሃይማኖት በዓላት ላይ የሚታየውን አንድነትም ግጭቶችን ለመፍታት መጠቀም እንደሚገባም ተመልክቷል፡፡ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ ሻለሙ ስዩም፣ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናሩት፤ በአገሪቱ የሚታየውን ግጭት ለማስቆም ወጣቱ የተለያዩ የአገሪቱ ጉዳዮችን በመተንተን ለግጭት ሊያደርስ የቻለውን ነገር በምክንያት ላይ ተመስርቶ በመለየት ችግሮችንም በውይይት መፍታት አለበት ብለዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ስጋት ፈጥሮብናል " - ኤምባሲዎቹ ሰሞነኛውን የሰሜን ኢትዮጵያን ጉዳይ አስመልክቶ በአዲስ አበባ የሚገኙት ፦ - የካናዳ፣ - የፈረንሳይ፣ - የጀርመን፣ - የጣሊያን፣ - የጃፓን፣ - የእንግሊዝ እና የአሜሪካ ኤምባሲዎች የጋራ አጭር መግለጫ አውጥተዋል። በዚህም ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ " #አወዛጋቢ " በሆኑት አካባቢዎች ከሰሞኑን የተፈጠረው ግጭት " ስጋት ፈጥሮብናል " ብለዋል። ሁሉም ወገኖች የታጣቂ…
#Raya #UNOCHA

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት 29,000 ሰዎች ከአላማጣ ገጠራማ አካባቢዎች ከቤታቸው ተፈናቅለው ፦
° በቆቦ / በሰሜን ወሎ
° ሰቆጣ / በዋግኽምራ በሚገኙ መጠለያዎች መጠለላቸውን ገልጿል።

23,000 ሰዎች ወደ ቆቦ ሰሜን ወሎ እንዲሁም 5,980 ሰዎች ወደ ሰቆጣ ዋግኽምራ ዞን ነው የተፈናቀሉት።

በአካባቢው ያለው ሁኔታ ሲታይ የተፈናቃዮች ቁጥር ከዚህ ሊጨምር እንደሚችል አመልክቷል።

ከተፈናቀሉት ዜጎች በዋነኝነት 70 በመቶዎቹ ህጻናትና ሴቶች ሲሆኑ ቀሩት ደግሞ አዛውንቶችና ታዳጊዎች ናቸው።

እንደ UN OCHA ሪፖርት ፦

🔘 ተፈናቃዮች ባሉበት ከበድ ያለ #የምግብ እና የውሃ እጥረት በመኖሩ አስቸኳይ የሆነ የህይወት አድን እርዳታ ያስፈልጋል።

🔘 ክፍት በሆኑ ቦታዎች ላይ የተጠለሉ ቤተሰቦች አስቸኳይ መጠለያ ያስፈልጋቸዋል።

ኦቻ ድጋፍ በሚያደርጉ #አጋር_አካላት የግብዓት እጥረት ምክንያት በጣም ተጋላጭ ለሆኑት የምግብ እና ውሃ ድጋፍ እየተደረገ ያለው መደበኛ ባልሆነ መንገድ በህብረተሰቡ ነው ብሏል።

ተጨማሪ ፦

🛑 እስከ ትላንት ድረስ በራያ አላማጣ ገጠራማ አካባቢዎች ላይ አንዳንድ መጠነኛ #ግጭቶች መከሰታቸውን ቢቀጥልም በአላማጣ ፣ ቆቦ ፣ ወልዲያ ከተሞች የጸጥታ ሁኔታው ​የተረጋጋ ነው።

⭕️ በአላማጣ እና በቆቦ መካከል ያለው መንገድ ተከፍቶ የንግድ ትራንስፖርት የቀጠለ ሲሆን እንደ ባንኮች ያሉ የህዝብ አገልግሎቶች ቀስ በቀስ ቀጥለዋል።

@tikvahethiopia