TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሲዳማክልል

🛑 " በፍርድ ቤት ሂደት ባለ ጉዳይ ፖሊሶች ጠመንጃ በመደቀን ቤተሰብ ላይ ድብደባ ፈጽመዋል " - ስሞታ አቅራቢዎች

🔵 " ከ200 በላይ ሰዎች ‘ይሰራልን’ ብለው አምነው ሁለት ሰዎች ካመጹ ምን ይደረጋል ? " - ሰሜን ሲዳማ ዞን አስተዳደር 

በሲዳማ ክልል፣ ሰሜን ሲዳማ ዞንዝ፣ ሲዳማ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ሁሩፋ ቀበሌ " በፍርድ ቤት ሂደት ባለ ጉዳይ በጸጥታ አካላት የድብደባና ንብረት ጭፍጨፋ " እንደተፈጸመባቸው ባለይዞታዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ቅሬታቸው በዝርዝር ምንድን ነው ?

" በፍርድ ቤት በሂደት የነበረ የመንገድ ጉዳይ ነበር። የዛሬ ሁለት ወር አካባቢ ነበር ነገሩ የተቀሰቀሰው። 

የተቀሰቀሰውም በግድ መንገድ ለማውጣት የቀበሌ አመራሮች ‘መንገድ ይወጣል’ ብለው ጀምረው ነበር የክሱ ሂደት የተጀመረው።

ቤተሰብ ተበትኖ፣ ንብረት ወድሞ እንዴት መኖር ይቻላል ? በሚል ክስ ተነስቶ ጠበቃ ቆሞ እየተካሰሰ ነው። ግን ትላንት የወረዳው ፓሊስ ሙሉ ፓትሮል መጥቶ በግድ ሙሉ ንብረት አውድመው ሂደዋል።  

በፍርድ ቤት ሂደት ባለጉዳይ ፖሊሶች ጠመንጃ በመደቀን ቤተሰብ ላይ ድብደባ ፈጽመዋል።

ድብደባ ካደረሱ በኋላ ስድብ፣ ማሸማቀቅና የዛቻ ቃል ተናግረዋል። ‘ለአርሶአሮቹ የሚያስፈልገው ሂደት ተሟልቶ ነው መንገድ መውጣት የሚችለው’ ተብሎ ውሳኔ አግኝቶ ነበር። 

እንዲህ የሚያደርጉት ምንም አይነት ወረቀት የላቸውም። ጉዳዩ ወረዳ ላይ በክስ ሂደት ያለ ነው። የሚያፈርሱት ቦታ እንሰት፣ መቃብር፣ ደን፣ ጎመን፣ ባሕር ዛፍ አለው።

ይዞታው የአቶ በቀለ በዶሬ እና አቶ አዲሴ አንጂሎ ሲሆን፣ ወደ 18 ሁለት የቤተሰብ አባላት የሚተዳደሩበት ነው " ብለዋል።


" መንገዱ ያስፈልጋል ከተባለ እንኳ የይገባኛል ጥያቄው ውሳኔውን ሳያገኝ፣ ካሳ ሳይታሰብ ማንም መጥቶ ነው እንዴ መንገድ የሚያወጣው ? " ሲሉ ጠይቀው፣ ባለድርሻ አካላት ለጉዳዩ በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

በፍርድ ሂደት ላይ ባለጉዳይ ለምን እንዲህ አይነት ድርጊት ተመፈጸመ ? ስንል የጠየቅናቸው የሰሜን ሲዳማ አስተዳደር አቶ አዱሱ ቃሚሶ፣ " በፍርድ ቤት የታገደ እኛ ጋ የመጣ ነገር የለም። ውሳኔው እስኪጸድቅ ድረስ ይሄ ቦታ ታግዶ ይቆይ የሚል አልደረሰንም " ብለዋል።

" የንብረት ጭፍጨፋ የተደረገው ከፍርድ ቤት ሂደት በኋላ ይሁን በፊት በሚለው ዙሪያ ያጣራሁት ነገር የለም ለጊዜው " ያሉት አስተዳዳሪው፣ ድብደባውን በተመለከተ ማጣራት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። 

በሁሉም አካባቢዎች መንገድ የመክፈት ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፣ " በእግርጥ መንገዱ የሚነሳው ያለ ካሳ ነው። ንብረቱ ብዙም አይደለም ከግራም ከቀኝም 3፣ 3 ሜትር ብቻ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ከ200 በላይ ሰዎች ‘ይሰራልን’ ብለው አምነውበት ሁለት ሰዎች ካመጹ ምን ይደረጋል? የሌሎቹ ተከፍቶ የሌላው አይተው ልማት ነው " ብለዋል።

" ጉዳዩ የእነርሱ ብቻ አይደለም። እስከ ቀበሌ ድረስ መንገድ ከፈታ እንዲደረግ እቅድ ታቅዶ ነበር። ህብረተሰቡ በመንገድ ተጠቃሚ መሆን አለበት "ነው ያሉት።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update #ሲዳማክልል

“ ከሀዋሳ ወደ ሻምና ለመሄድ የመኪና መንገድ የለም። መንገድ ለመክፈት ደግሞ አርሶ አደሩ መሬት መስጠት አለበት። የግድ በእነርሱ መሬት ላይ ነው መንገዱ የሚወጣው  ” - የሲዳማ ክልል ጸጥታ ቢሮ

በሲዳማ ክልል ሰሜን ሲዳማ ዞን ሲዳማ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ሁሩፋ ቀበሌ ባለይዞታዎች፣ “ ፓሊሶች በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ጠመንጃ በመደቀን ቤተሰብ ላይ ድብደባ ፈጽመዋል ” ሲሉ ለቲክቫህ ላቀረቡት አቤቱታ የክልሉ ጸጥታ ቢሮ ምላሽ ሰጥቷል።

ለዛውም በፍርድ ሂደት ላይ ባለ ጉዳይ “ ጠመንጃ በመደቀን ድብደባ መፈጸም ” ተገቢ ነው ? ስንል የጠየቅናቸው የክልሉ ጸጥታ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳዬሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ አሀመድ፣ “ ህዝቡ ተደብድቧል የሚል ቅሬታ አልመጣም። ተደብድቦ ከሆነ የምናጣራ ይሆናል ” ብለዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ በገለጹት መሠረት ቅር ያሰኛቸው መንገድ መከፈቱ ሳይይሆን ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሂደት እያለ ደርጊቱ መፈጸሙ፣ በፓሊስ ደብደባ ስለተፈጸመባቸው፣ በንብረት ላይ ውድመት ስለደረሰባቸው፣ ካሳ ስላልተከፈላቸው በመሆኑ ነውና ለዚህስ ምላሽዎ ምንድን ነው ? ስንል ላቀረብው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ሀሚድ አሀመድ

“ አዎ በእርግጥ ፍርድ ቤት ያለ ኬዝ ነው። ከላይ ያለ አካል አቅጣጫ ሲያስቀምጥ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የማይጠበቅበት ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ።

ከጠቅላይ ሚኒስቴር ትዕዛዝ ከመጣ እንደዚህ አይነት ጉዳዮች አንዳንድ ቅድመ ሁኔታዎች የሚጠቅባቸው አይነት ነገሮች ሳይመጡ ሲቀሩ ላይጠበቅ ይችላል።

የሚገመት አይነት ንብረት አይደለም። ፎቶውን ሳይ የተወሰነ አትክልት ነገር አለ ፤ ድንች ፣ ቀይ ሽንኩርት ነበረ። ካሰ የሚከፈል ከሆነ እንደ ካሳ ነው የሚነጋገሩት። ካልሆነ ደግሞ በሌላ ካሳ እንዲከፈላቸው ነበር ማድረግ የነበረባቸው።

‘ በጭራሽ መንገድ አይወጣም ’ ነው እነርሱ ሲሉ የነበሩት። ካሳ ተከፈለ አልተከፈለ የግድ ይላል ህዝቡ ያነሳው ጥያቄ መንገድ የለንም’ የሚል ነውና።

ከሀዋሳ ወደ ሻምና ለመሄድ የመኪና መንገድ የለም። መንገድ ለመክፈት ደግሞ አርሶ አደሩ መሬት መስጠት አለበት። የግድ በእነርሱ መሬት ላይ ነው መንገዱ የሚወጣው። 

የፍርድ ቤት ኬዛቸውንም ይከታተሉ። ይሄ ደግሞ እንዳይከታተሉ የሚያደርጋቸው ነገር አይደለም። ተከታትለው ከጨረሱ በኋላ ፍርድ ቤቱ ካሳ ሊያስከፍልላቸው ይችላል።


እኔ ጉዳዩን አጣርቻለሁ። ባለፈው ፕሬዝደንቱ እዛ ሂደው ነበር። አጋጣሚ የፓሊስ ግንባታ ፕሮጀክት ሊያስመርቁ በሄዱበት ‘ እዛ መንገድ እንዲወጣ ነበር ’ ያሉት። 

መንገድ በፊት ተከልክሎ ነበር እዚያ ቦታ እንዳይወጣና ፕሬዚደንቱ ካዩ በኋላ መንገዱ እንዲወጣ ነበር ያዘዙት። ባስቀመጡት አቅጣጫ መሠረት ነው መንገዱ እንዲወጣ የተደረገው።

የመንገድ ከፈታ የትም ያለ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሀዋሳ መጥተው በነበረበት ወቅት ማግስት ‘ምንድን ነው ችግራችሁ?’ ብለው ሲጠይቁ፣ ‘ሀዋሳ መውጫና መግቢያ መንገድ አጥተናል። ምንም መንገድ አልተከፈተልንም’ የሚል ቅሬታ ሲያነሱ ‘በሲዳማ ክልል ከተሞች የውስጥ መንገድ ሁሉም ቦታ እንዲከፈት ነበር አቅጣጫ አስቀምጠው የወጡት።

በክስ ያሉ ቦታዎች ነበሩ። መንገድ ከፈታ ላይ አንዳንድ ማህበረሰብ እንዲወጣላቸው ይፈልጋሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ እንዲወጣ አይፈልጉም። 

አንዳንድ ንብረት ይነካል። ይሄ ደግሞ የምንደራደረው ጉዳይ አይደለም። የምንጓዘው፣ መድኃኒት የሚደርሰው፣ ችግር የሚፈታው በመንገድ ነው። ግን ‘መንገድ አይከፈት’ በማለት ሁከት እንዲነሳ የሚፈልጉ አካላት አሉ።

ወደ 6፣ 7፣ 8 ሰዎች ሆነው ነው እዛ ሲጨቃጨቁ የነበረው። ነገር ግን አብዛኛው መንገድ እንዲከፈትላቸው የሚፈልጉ አሉ። በዚህም ከፌደራል እስከ ክልል ድረስ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ነው እንዲከፈት የተደረገው። ”


#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia