TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መልዕክት

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ልደትን አስመልክተው " የእንኳን አደረሳችሁ " መልእክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸው የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ አንስተው አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ቅዱስናታቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፥ " ቸርነቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር አምላክ በአሁኑ ጊዜ #በሀገራችን የተከሠተው ችግር በከፊልም ቢሆን ረገብ ብሎ የሰላም ጭላንጭል እንድናይ አድርጎናል " ያሉ ሲሆን " ይህ ሰላም የእግዚአብሔር ስጦታ ነውና #ልንወደው #ልናከብረውና #ልንጠብቀው ይገባል " ብለዋል።

" ሰላም በጠፋ ጊዜ በወገኖቻችን ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ በዓይናችን አይተናል። " ያሉት ቅዱስነታቸው " ይህ ዓይነቱ ክሥተት ሊቆም እንጂ ሊቀጥል አይገባም " ሲሉ አስገንዝበዋል።

የተገኘው የሰላም ጭላንጭል ወደ ፍጹም አስተማማኝ ደረጃ በሙሉነት እንዲያድግ ሁሉም በኃላፊነት እንዲሰራ በአጽንዖት አደራ ብለዋል።

በተከሠተው አለመግባባት በአጠቃላይ በሕዝብ ላይ የደረሰው ስብራት ከባድ በመሆኑ የዓለም ማኅበረሰብ የተቻለውን ድጋፍ ሁሉ በማድረግ ሕዝባችንን እንዲያግዝ  መንግሥትና ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች የተጀመረውን የሰላም ጉዞ እንዳይቀለበስ በከፍተኛ ኃላፊነት እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ቅዱስነታቸው ፤ " ኢትዮጵያውያን የሆናችሁ ልጆቻችን በተለመደው የመተጋገዝ ቅዱስ ባህላችን መሠረት እርስ በርስ #በመረዳዳት ይህንን ፈተና እንድናልፈው በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን ከአደራ ጋር እናስተላልፋለን። " ብለዋል።

(የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያያዟል)

@tikvahethiopia