TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.6K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

“ ገንዘብ የማይቀጣ በእስር ይለወጥለታል። በእስር የማይቀጣ ደግሞ አጭር የሆነ የሰውነት ማሟሟቂያ ቅጣቶችንም ይቀጣል ” - ባለስልጣኑ

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 ዓ/ም የዘጠኝ ወራት ሪፓርት ግምገማን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቶ ነበር።

በዚህም፣ “ ከአምናው ዘጠኝ ወር ጋር ሲነጻጸር የዘንድሮው የዘጠኝ ወሩ አፈጻጸማችን 64% የደንብ ጥሰት የቀነሰበት ነው ” ብሏል።

ይህን ያሉት የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ ከኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ በመንገደኞች ላይ የሚጣለውን ቅጣት ተመጣጣኝ አለመሆን በተመለከተ ስለሚነሳው ቅሬታ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል።

ምን መለሱ ?

“ ህጎች፣ ደንቦች የሚወጡበት የህዝቡን ጥቅም ለማስጠበቅ ነው። ሌላ ተልዕኮ የለውም። እንደ ራሳችን ሰውነት፣ ልብስ የምንከባከብበት ቱሩፋታችን ነው ማለት ይቻላል የኮሪደር ልማቱ።

በሳይክል መንገድ የሚሄድ ሰው በሳይክል መንገድ እንዲሄድ ፤ እግረኛውም በእግረኛው መንገድ እንዲሄድ የተደረገበት፣ በሳሮች፣ ፋውንቴሽኖች አካባቢ ቆሻሻ እንዳይጣል የተደረገበት በርካታ ስልጠናዎች ተሰጥዋል።

ቀጥሎ ህግ የማስከበር ሥራ ስራ ነው። ቅጣቱ የዚህን ያህል የጎላምና በጣም የከፋም አይደለም። የቅጣት ደረጃዎች አሉ።

ገንዘብ የሚቀጣ ይቀጣል። ገንዘብ የማይቀጣ በእስር ይለወጥለታል። በእስር የማይቀጣ ደግሞ አጭር የሆነ የሰውነት ማሟሟቂያ ቅጣቶችንም ይቀጣል።

አህያ በኮሪደር ላይ መንዳት (በተለይ በቪአይፒ መንገዶች ከቦሌ እስከ ቤተ መንግስት ሌሎችም አካባቢዎች ላይ) ተቀባይነት የሌለው ነው። 

ማህበረሰቡም ሚዲያዎችም እንዲያውቁት የምንፈልገው በከተማችን ውስጥ ምንም አይነት የእንስሳት ዝውውር የማይፈጠርባት ከተማን ከመፍጠር አንፃር አጠንክረን የምንሰራበት ይሆናል። 

የቀጣናቸውም ቅጣቶች እንደሚባለው ሳይሆን በሁለት፣ ሦስት (በቦሌ፣ በጊዮርጊስ የፈጸምናቸው) አካባቢዎች አሉ። እሱም ደግሞ የተጋነነ ቅጣት አይደለም ተመጣጣኝ የሆነ ቅጣት ነው። ግን ወደ ፊት አጠናክረን የምንሄድበህ ይሆናል ” ብለዋል።

ከወንዝ ዳር ልማት ጋር በተያያዘ ትላልቅ ተቋማትና ፋብሪካዎች ይቀጣሉ፣ ሁልጊዜ ግንዛቤ እየተፈጠረላቸው ነው ይባላል፤ ግን በመቶ ሺዎች፣ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ይቀጣሉ ምክንያቱ ምንድን ነው ? የሚል ጥያቄም ቀርቦላቸዋል።

ሻለቃ ዘሪሁን ምን መለሱ?

“ የደንብ ቁጥር 181 የወንዝ ዳርቻ ደንብን በተመለከተ ተቋማችን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ ከአረንጓዴና ውበት ቢሮና ከመንገዶችና ውሃ ባለስልጣን ጋር በመሆን አብረን ነው እየሰራን ያለነው። 

በወንዝ ዳርቻ ላይ በርካታ ግንዛቤዎች ተሰጥተዋል። አንደኛ ጥናቶች ተጠንተዋል። ትላልቅ የሚባሉ ሰባት ወንዞች አሉ። በተለይ ፍሳሾችን ወደ ወንዝ የሚገቡበት ሁኔታ አለ። ያ ተጠንቷል። በተጠናው መሠረት ተጋላጭ ናቸው የተባሉ የመንግስት የግል ተቋማትና የግለሰብም ጭምር ግንዛቤ ተሰጥቷል።

ግንዛቤ የመስጠት ችግር የለም። ሰው ያንን ተቀብሎ የመተግበር ችግር ነው። የምናስተካክለው ህግን በማስከበር ነው ማለት ነው። ስለዚህ ህግን በማስከበር በርካታ ርቀቶች ሂደናል። 

በፋብሪካዎች፣ በትላልቅ የመንግስትም ሆነ የግል ሆስፒታሎች የሚወጡ ፍሳሾች አደገኝነታቸው በናሙና ይወሰዳል፣ በላብራቶሪ ተረጋግጦ እንደአደገኝነቱ መጠን በደንቡ ላይ የተቀመጠ የህግ መቀጮ ስላለ በዚያ መሠረት ይቀጣል።

በዚህ ያገኘነው ውጤት፥ ወደ 2,850 በላይ ወደ ወንዙ የሚገቡ ከተለያዩ ተቋማት የሚፈሱ ፍሳሾች ቆመዋል። የራሳቸውን ስፍቲ ታንከር የመስራት ለውጥ አለ ” ነው ያሉት።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
😡373👏201105🤔20🕊14💔12🙏9😭9🥰6😱4😢4
#AddisAbaba : በአዲስ አበባ ተቋርጦ የነበረውን የመኖርያ ቤት ህብረት ሥራ አገልግሎት ለማስቀጠል ተጠንቶ የቀረበ ውሳኔ ሃሳብ ላይ ካቢኔው ውሳኔ አሳለፈ።

የከተማው ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው 4ተኛ አመት 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

ከነዚህም አንዱ ተቋርጦ የነበረዉ የመኖርያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት አገልግሎትን የሚመለከት ነበር።

በዚህም አገልግሎቱን ለማስቀጠል ተጠንቶ የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ የመልካም አስተዳደር ጥያቄን ሊፈታ በሚችል አግባብ የውሳኔ ሀሳብ ማሳለፉ ተነግሯል።

ሌላኛው ፦
- የብርሃን አይሰውራን፣
- የመነን
- የገላን ቦርዲንግ ትምህርት ቤቶች ካላቸው ልዩ ስምሪት፣ የጥራት ደረጃ እና ከሚያንቀሳቅሱት ሀብትና ንብረት አስተዳደር አንፃር ህጋዊ ሰውነት ኖሯቸው እንዲተዳደሩ እና ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለከተማዉ ትምህርት ቢሮ እንዲሆን የቀረበዉን ደንብ መርምሮ አጽድቋል።

ካቢኔው ሀገራዊ ፋይዳ አላቸው ባላቸው ፕሮጀክቶች የቀረበ የመሬት ማስፋፊያ ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ አጽድቋል።

@tikvahethiopia
👏20374😡47🙏46🤔35😢17😭12🕊11🥰10💔2
#AddisAbaba

" በ3 ወራት ውስጥ 943 ፍቺዎች እንዲሁም 53 ውሳኔ የተሰጠባቸው ጉዲፈቻዎች ምዝገባ ተከናውኗል !! "

የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከፌደራል የመጀመርያ ፍርድ ቤት ጋር  የፍቺ እና ጉዲፈቻ ውሳኔዎችን መዝግቦ በአንድ መስኮት አገልግሎት ለመስጠት የጋራ ስምምነት ፈጽመው እየሰሩ ሲሆን ላለፉት 3 ወራት ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን አፈፃፀም በጋራ ገምግመዋል።

በዚህም ወቅት በቀረበ ሰነድ 996 ተገልጋዮች በ3 ወራት የኩነት ምዝገባ አገልግሎቱን በፍርድ ቤቶች በአንድ መስኮት ማግኘታቸው ተመላክቷል።

ከዚህም ውስጥ ውሳኔ ያገኙ 943
#ፍቺዎች እንዲሁም 53 ውሳኔ የተሰጠባቸው #ጉዲፈቻዎች በወቅቱ ምዝገባ በማድረግ በአንድ ማዕከል በፍ/ቤቶች አገልግሎት መሰጠቱ ተመላክቷል።

Via
https://t.iss.one/addisvaitalpress/9155

@tikvahethiopia
😭36472😱28🤔26🕊16💔14👏12🥰11😢9🙏4
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ 1,735 የንግድ ቤቶች ለጨረታ ቀረቡ።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ክ/ከተሞች ተገንብተው በተጠናቀዉ የ40/60 የጋራ ህንጻዎች ላይ የሚገኙ 1,735 የንግድ ቤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ለማስተላለፍ እንደሚፈልግ አሳውቋል።

ኮርፖሬሽኑ ለጨረታ ያቀረባቸውን የ40/60 ንግድ ቤቶች ተወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 21 የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ) ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ምሽት 11:30 ድረስ በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00 / አንድ ሺህ በመክፈል መግዛት ይችላል ተብሏል።

የጨረታ ሰነድ የሚሸጥባቸው ስፍራዎች የት ናቸው ?

- ቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት (ባምቢስ አካባቢ)
- የካ ክ/ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት (መገናኛ)
- አራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት (አራት ኪሎ)
- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት (ቃሊቲ መናኸሪያ ፊት ለፊት)
- አ/አ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅ/ጽ/ቤት (40/60 በሻሌ ሳይት ብሎክ 13)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
🤔168118😭33🙏25😱24😡19👏17🕊14🥰12💔10😢6
#አቢሲንያ_ባንክ
የሁሉም ምርጫ !


ሸሪዓውን መሠረት አድርገውና ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል አካተው፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተመሰከረለት የአይማል ኮር ባንኪንግ ሲስተም እየታገዙ ዳጐስ ያሉ ጥቅሞችን ለአስቀማጮች የሚያስገኙትን፤ የሴቶች (ዘህራህ)፣ የወጣቶች (ፊትያህ)፣ የባለውለታዎች (ሙስኒን)፣ የሃጅ እና ዑምራ፣ የዕድር (ጀሚአህ)፣ የዕቁብ (ሱንዱቅ) እና የጊዜ ገደብ ተቀማጭ ሙዷረባህ ትርፍ አጋሪ ሂሳቦችን በመክፈት፤ ከባንካችን ጋር ኢንቨስት አድርገው በተሻለ ትርፍና በከፍተኛ ጥቅም የወደፊት ህልምዎን እውን ያድርጉ!
አቢሲንያ አሚን
ዕሴትዎን ያከበረ!
#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
🥰4319😭16🙏4🤔2
#AddisAbaba

ከለሊት 10:00 ጀምሮ በአዲስ አበባ መንገዶች ይዘጋሉ።

116ኛው የኢትዮጵያ ፖሊስ ምስረታ በዓል ነገ እሁድ ሚያዚያ 26/2017 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ወታደራዊ ትርኢቶች ይከበራል።

በዚህም ምክንያት መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

➡️ ከ22 አደባባይ ወደ ወደ ቅዱስ ዑራኤል -መስቀል አደባባይ (22 አደባባይ በተመሣሣይ ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ ላይ)

➡️ ከአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ (አትላስ መብራት እና ፒኮኪ መብራት ላይ)

➡️ ከቦሌ ወሎ ሠፈር መታጠፊያ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)

➡️ ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ውስጡን ወደ ዋናው መንገድ የሚያስወጡት

➡️ ከመስቀል ፍላዎር አደባባይ ወደ ጋዜቦ አደባባይ (መስቀል ፍላዎር አደባባይ ላይ)

➡️ ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ኤግዚብሽን ውስጥ ለውስጥ ወደ ፊላሚንጎ (ጋዜቦ አደባባይ ላይ)

➡️ ከቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን ወደ ለገሃር መብራት ( ቅዱስ ቂርቆስ ወደ ጋዜቦ ላይ)

➡️ ከአጎና መስቀለኛ ወደ ጥላሁን አደባባይ

➡️ ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሀር መብራት (ሜክሲኮ አደባባይ ላይ)

➡️ ከፓርላማ መብራት ወደ ውጭ ጉዳይ (ፓርላማ መብራት ላይ)

➡️ ከጥይት ቤት ወደ ቅዱስ ገብርኤል (ጥይት ቤት መታጠፊያ ላይ )

➡️ ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ ላይ) ከለሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ።

በተጨማሪም፦
- ከቅዱስ ዑራኤል ወደ መስቀል አደባባይ
- ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከጥላሁን አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከለገሃር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም
- ከብሔራዊ ቤተመንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ ከዛሬ ጀምሮ ዝግ ተደርጓል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
1😡1.07K325👏88😭65🕊48🙏45🤔44😢27💔22🥰15😱13
TIKVAH-ETHIOPIA
ነገ ሚያዚያ 27 ቀን የአርበኞች (የድል) ቀን በዓል ነው። በዓሉ በሀገርአቀፍ ደረጃ  ተከብረው ከሚውሉ ብሔራዊ በዓላት አንዱ ሲሆን  የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሕዝብ አገልግሎት ዝግ ሆኖነው ይውላሉ። @tikvahethiopia
#AddisAbaba

ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል።

ነገ ሚያዚያ 27/2017 ዓ/ም የአርበኞች መታሰቢያ ቀን ይከበራል።

በዚህም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ አሳውቋል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ተገቢው መረጃ እንዲኖረው ተብሏል።

@tikvahethiopia
703👏121😡101🙏68🤔28🕊21😢16😭16🥰14
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጎሮ ገብርኤል በተለምዶ " ጉሊት " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተከሰተ የእሳት አደጋ ሱቆች መውደማቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

አደጋው የተከተሰው ከጠዋቱ 4 ሰዓት ገደማ እንደሆነ ምክንያቱን ገና እንዳላወቁት፣ በሰዎች ላይ ጉዳት ባይደርስም በርካታ ሱቆች መውደማቸውን ነዋሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በመደዳው የተደረደሩ ሱቆችም በእሳት ቃጠሎው ነደዋል።

የከተማዋ እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ሠራተኞችና ተሽከርካሪዎች በቦታው እንደተገኙ፣ የእሳት ቃጠሎው በቁጥጥር ስር እንደዋለም በቦታው ያሉ የዓይን እማኞች ነግረውናል።

አንድ ቃላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የሠፈሩ ነዋሪ፣ " በአደጋው ሱቆቹ ሙሉ ለሙሉ አመድ ሆነዋል " ሲሉ አስረድተዋል።

እኚሁ አካል ከቦታው ያጋሩን ቪዲዮና ፎቶ የእሳት ቃጠሎ አደጋ በተባለው ቦታ ቃጠሎ መከሰቱን የሚያሳይ ሲሆን፣ ሁሉም ከላይ ተያይዟል።

በአደጋው ዙሪያ የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽንን ለማነጋገር ጥረት እያደርግን እንገኛለን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
😭25356🤔40🙏22😢16🕊14🥰4😱4👏3😡3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#አቢሲንያ_ባንክ

በጉርሻ 1.6 ሚሊዮን ብዙ ነው? ግን እውነት ነው! ክፍያዎችን በአቢሲንያ ባንክ በመቀበል ብቻ ቢዝነስ የሚደጉም ጉርሻ!!

#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
37🤔2😱2
#AddisAbaba

" አሰራሩ ብክነትን ከመከላከል በተጨማሪ አላግባብ የፓርኪንግ ክፍያ የሚጠይቁ ግለሰቦችን ያስቀራል " - ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን ከጥር 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ አውቶማቲክ ኢንፎርስመንት እና ፓርኪንግ ማኔጅመንት ሲስተም የተሰኘ አሰራር አበልጽጎ ወደ ስራ አስገብቷል።

የዚህ መተግበሪያ ተግባራዊ መሆን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን በየአመቱ ለደረሰኝ ህትመት ያወጣው የነበረውን ከ17 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚያስቀር ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አማረልኝ ታረቀኝ " የቁጥጥር ስራው በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን ለማድረግ በሚል " አሰራሩ ተግባራዊ መደረጉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አብራርተዋል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በዝርዝር በሰጡን ሃሳብ ምን አሉ ?

" ከዚህ ቀደም ማንዋል የነበረ አሰራር ነበር የነበረው ደረሰኞችን በመስጠት የቅጣት አይነቱ ምንድነው የሚለውን በመጻፍ የሚደረግ ሂደት ነበር።

የአሁኑ አሰራር ግን የደንብ ተላላፊዎችን እንግልት በእጅጉ የሚቀንስ ሆኗል ምክንያቱም የቅጣት አይነቱ ተፈጻሚ የሚሆነው መንጃ ፈቃዳቸውን በመቀበል መረጃቸውን ስካን ተደረጎ በኤስ ኤም ኤስ (SMS) ቴክስት ነው።

ክፍያውን በስልኩ በሚገኙ የመክፈያ አማራጮች ያከናውናል መንጃ ፈቃድ መስጠትም ሆነ ሰሌዳ ማስፈታት አይጠበቅባቸውም።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣው የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 557/2016 አለ እሱ ላይ የተጠቀሱ ህጎችን በሙሉ ወደ ሲስተሙ በመጫን ተግባራዊ እየሆነ ነው።

አንድ ተላላፊ ምን አይነት ጥፋት ነው ያጠፋው ፣በዛሬው ዕለት ስንት ደንብ ተላላፊዎች ተመዝገቡ ፣የትኞቹን እርከን የጥፋት አይነቶች ነው የተላለፉት ፣ማን የሚባል ተቆጣጣሪ የት ቦታ ላይ ምን አይነት ቅጣት ወሰደ የሚለውን የተሟላ መረጃ ቀጥታ ማግኘት የሚቻልበትን አሰራር ነው የዘረጋነው።

አሁን የገጠመን ችግር ሙሉ በሙሉ ከመተግበር አኳያ ሁለት ነገሮች ይፈልጋል የመጀመሪያው የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የመዘገባቸውን 1,124,000 (አንድ ሚሊየን አንድ መቶ ሃያ አራት ሺህ) መንጃ ፈቃዶችን እና 772,000 የተሽከርካሪ መረጃዎችን ነው የወሰድነው።

እዚህ ምዝገባ ውስጥ ያሉ በሙሉ በአዲሱ የአገልግሎት ሲስተም እንዲገለገሉ ለማድረግ እድሉ አለ ነገር ግን የክልሎች መንጃ ፈቃድ እና ሰሌዳዎች በአግባቡ ተመዝግበው ወደ እኛ የመረጃ ቋት ባለመግባታቸው ምክንያት ማንዋሊ አገልግሎቱን ለመስጠት የምንገደድበት ጊዜ አለ።

ሁለተኛው በመረጃ ቋታችን የተመዘገቡትም ቢሆኑ አድራሻቸውን በትክክል ያለገለጹና መደበኛ ስልክ ቁጥሮችን ያስቀመጡ መረጃው ላይደርሳቸው የሚችልበት እድል ስለሚኖር እና ከ10 ቀን በላይ ቅጣታቸውን ያልከፈሉ አሽከርካሪዎች በደንቡ መሰረት የቅጣቱን 5 በመቶ ወለድ እየጨመረ የሚሄድ በመሆኑ እክል ይፈጠራል።

በእኛ በኩል በመረጃ ቋት ውስጥ የሌሉ አሽከርካሪዎች ለአንድ ጊዜ በማንዋል ከተቀጡ በኋላ ለሁለተኛው ምዝገባቸውን አከናውነው በሲስተሙ የሚስተናገዱ ይሆናል።

ጎን ለጎን በክልሎች የሚገኙ የተሽከርካሪ ባለንብረቶችም አድራሻቸውን በትክክል የሚገልጽ መንጃ ፈቃድ መረጃቸው እንዲሰጠን ጥያቄ አቅርበናል በቅርቡ መረጃዎቹም ልናገኝ እንችላለን።

ይህ በሁሉም ክልሎች ያሉ መረጃዎች እስከሚመጣ ግን በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉ የተመዘገቡ መንጃ ፈቃዶች እና የተሽከርካሪ መረጃዎች ላይ ተግባራዊ አድርገን እየሰራን ነው።

የፓርኪንግ አሰራራችንም ለብክነት የሚዳርግ ፣ ሰአታቸው በትክክል የማይገለጽ እና ማንዋሊ በደረሰኞች የሚሰሩበት ሁኔታዎች ያሉበት እንደሆነ ይታወቃል ይህንንም ለማስቀረት የፓርኪንግ ሲስተሙን በ13 ሳይቶች ላይ ተግባራዊ አድርገናል።

ተሽከርካሪው የገባበትንን ፣ የወጣበትን ሰዓት እና አጠቃላይ ክፍያው ባስመዘገበው ስልክ ቁጥር በSMS መልእክት እንዲደርሰው ይደረጋል።

አሰራሩ ብክነትን ከመከላከል በተጨማሪ አላግባብ የፓርኪንግ ክፍያ የሚጠይቁ ግለሰቦችን ያስቀራል።

አሁን በ13 ሳይቶች ቢጀመርም ሙሉ በሙሉ በከተማችን እያሰፋን ተግባራዊ እንዲሆን ይደረጋል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
441😡108👏91🙏45🤔19😭18🥰15😢14💔14🕊9😱2