TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UNESCO #ETHIOPIA

#መስቀል
#ፍቼ_ጫምባላላ
#የገዳ_ስርዓት
#ጥምቀት

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (UNESCO ) ያስመዘገበቻቸው የቅርሶች ብዛት 13 ደርሷል። እነዚህ ቅርሶች በሚዳሰሱና በማይዳሰሱ ቅርሶች ዘርፍ የተመዘገቡ ናቸው። ከእነዚህም መካከል የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ አክሱም፣ የኮንሶ ባህላዊ እርከን ይገኙበታል። በሚቀጥለው ዓመት በማይዳሰስ ቅርስነት ይመዘገባል ተብሎ የሚጠበቀው አሸንዳ አሸንድዬ ይገኝበታል።

(BBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጥምቀት በዓል...

- ሀገራችን ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔሰኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት ካስመዘገበቻቸው ቅርሶች አንዱ የሆነው #ጥምቀት በዩኔስኮ ከተመዘገበ በኋላ ሲከበር ይህ የመጀመርያው ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ጥምቀት

የኢፌዴሪ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ዛሬ ባወጣው መግለጫ የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉን አሳውቋል።

የበዓሉ ታዳሚዎችና እንግዶች ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆንና በዓሉን በሰላም እንዲከበር ግብረ ኃይሉ ከወትሮው በተለየ መልኩ በቂ ዝግጅት በማድረግ ስምሪት ወስዶ ወደ ተግባር መግባቱን ገልጿል፡፡

ግብረኃይሉ ፥ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በርካታ የፀጥታ አካላት ማሰማራቱን ገልፆ በታቦታት ማደሪያ ስፍራዎችና በርካታ የበዓሉ ታዳሚዎች በሚገኙበት አካባቢ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

ከጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የደህንነት ስጋቶችን አስቀድሞ ለመከላከል የተከላከሉ ተግባራት ፦

• ከበዓሉ ጋር በተያያዘ ርችት መተኮስ ፍፁም የተከለከለ ነው።

• በዓሉ በሚከበርበት ስፍራ ከሚመለከተው አካል ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦች እና ተቋማት ድሮን ማብረር ወይንም ማንቀሳቀስ አይችሉም።

• ምንም አይነት የጦር መሳሪያ፣ ተቀጣጣይም ሆነ ስለታማ ቁሳቁስ ይዞ መንቀሳቀስ አይቻልም።

የበዓሉ ታዳሚዎች ለደህንነት ሲባል ፍተሻ የሚደረግ መሆኑን ከወዲሁ በማወቅ እና በመረዳት ትብብር እንዲያደርጉ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ በፍጥነት ለጋራ ግብረ-ኃይሉ ጥቆማ ለመስጠት በስልክ ቁጥር ፦
• +251115-52-63-03፣
• +251115-52-40-77፣
• +251115-54-36-78 እና
• +251115-54-36-81 እንዲሁም በ987፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች መጠቀምና በአካባቢው ላለ የፀጥታ ኃይል መረጃውን በአካል ማድረስ ይቻላል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#ጥምቀት

ጎንደር ከተማ በጥምቀት በዓል ሰሞን በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ እንግዶችን ለመቀበል የሚያስችላትን አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት ማድረጓ አሳውቃለች።

የጎንደር ከተማ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ፤ በጥምቀት በዓል ሰሞን እስከ 2 ቢሊየን ብር በቱሪዝሙ ምክንያት ኢኮኖሚው ገቢ ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም አሳውቋል።

በጥምቀት በዓል ወቅት ከ750 ሺ እስከ 1 ሚሊየን ጎብኚ ወደ ጎንደር እንደሚመጣ ይጠበቃል ያለው መምሪያው ለዚህም ከ400 በላይ ሆቴሎች እና ድንኳን የሚጣልባቸው ሥፍራዎች ዝግጁ መሆናቸውን ገልጿል።

እንደ ሚመጡ እንግዶች አቅም የማረፊያ፣ ምግብን ጨምሮ አስፈላጊ ነገሮችን መሸመቻ አማራጭ መሰናዳቱን መምሪያው አሳውቋል።

በተጨማሪ ከጥር 4 እስከ 9 ቀን 2015 ዓ.ም የባህል ሣምንት የሚከበር ሲሆን በዚህም የአካባቢውን ፣ የክልሉን ባህል፣ ወግና ትውፊት የሚያሳዩ ዝግጅቶች ይቀርባሉት ተብሏል።

እንዲሁም ጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም የአጼ ቴዎድሮስ ልደት ሀገራዊ አንድነትን በሚያፀና ሁኔታ እንደሚከበር መምሪያው መግለፁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ጥምቀት

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ #በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ።

መልካም የጥምቀት በዓል!
Baga Ayyaana Cuuphaa Nagaan Geessan! Ayyaana Gaarii
ርሑስ በዓል ጥምቀት !

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የ #ጥምቀት_በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እየተከበረ ይገኛል።

Photo Credit : EPA & EBC

@tikvahethiopia
#ከተራ #ጥምቀት

መንግስት የዘንድሮ ዓመት የከተራ እና የጥምቀት በዓል በመላው ሀገሪቱ #በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን አሳውቋል።

የበዓላቱን በሰላም መጠናቀቅ አስመልክቶ ዛሬ ማምሻውን በኮሚኒኬሽን አገልግሎት በኩል መግለጫ ያወጣው መንግሥት ፤ የከተራ እንዲሁም የጥምቀት በዓላት በድምቀት እና በሰላም እንዲጠናቀቁ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#EOTC

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ፦

(ባለፈው ዓመት የልደት በዓልን ጨምሮ ሌሎች መንፈሳዊ በዓላት አከባበርን በተመለከተ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ቀርበው የተናገሩት)

" ... ይህንን የልደት በዓል ስናከበር የት ነው የምንሄደው ? ቀድሞ በዓሉን ለማክበር የት ነው የምንሄደው ? ስንል ጭፈራ ቤት አይደለም፣ ሙዚቃ ቤት አይደለም ፣ ይሄ በዓል የሚከበረው በጭፈራም አይደለም፤ በዘፈንም አይደለም፣ በሙዚቃም አይደለም፤ በበዓላችን ላይ ሙዚቃ እየቀላቀላችሁ / ጭፍራ እያስገባችሁ የበዓሉን እሴት / ሃይማኖታዊ ትርጉም የምታበላሹት #የሚዲያ አካላት ናችሁ።

ይሄ በዓል የሚከበረው በጭፈራም አይደለም፤ በዘፈንም አይደለም፤ በሙዚቃም አይደለም።

የበዓሉን ትርጓሜውን ማወቅ ያስፈልጋል። ያን እለት መላእክትና ሰዎች አልዘፈኑም እኮ፣ አልጨፈሩም እኮ ፤ መላእክትና ሰዎች ደስታቸውን የገለጡት በምስጋና ነው። ዕለቱ የሚከበረው በምስጋና ነው። አባቶቻችን የበዓሉን አከባበር ወደኛ ያደረሱት በዚህ መንገድ ነው። እኛም ለትውልድ የምናስተለልፈው በዚህ ሁኔታ ነው።

የበዓሉን መንፈሳዊ ስነስርዓት በጠበቀ መልኩ ወደትውልድ ማስተላልፈ ይኖርብናል።

የበዓሉንም መንፈሳዊ ስነስርዓት እሴት ስንል ለምን ተወለደ ? የት ተወለደ ? ከሚለው ትርጓሜ ይጀምራል፤ ሲወለድ ምን ተከሰተ፣ ምን ተደረገ ? መላዕክት፣ እረኞች፣ ሰባሰገል ምን አደረጉ ? ድንግል ማርያም ምን አደረገች ? እንስሳትስ ምን አደረጉ ? የሚሉትን ነገሮች ነው የምንወስደውና የምናስበው። ስለዚህ እነሱ ያደረጉትን እያደረግን ነው ለትውልድ ማስተላለፍ የሚገባን።

ይህ ለልደት በዓል ብቻ ሳይሆን የ #ጥምቀት በዓልም፣ ሌሎች መንፈሳዊያን በዓላቶቻችን ሁሉ ፣ መንፈሳዊያን በዓላት እስከሆኑ ድረስ በመንፈሳዊ ስነስርዓት ነው ማክበር የሚገባን፣ ሃይማኖታዊ በዓል ብለን እስከሰየምን ድረስ ሃይማኖቱ በሚፈቅደው ስነስርዓት/እሴት ነው በዓላቱ ተከብረው መዋል ያለባቸው፤ ተከብረው ማለፍ ያለባቸው።

ትውልዱም ማወቅ እና መማር ያለበት በእንዲህ ያለ ሁኔታ ነው። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC " ሀገራችን ሰላም ትሁን፤ የሃይማኖት ሰዎች እንደ ሃይማኖት እናስብ፣ እንደ ሃይማኖት እንናገር፣ አላስፈላጊ ጀግንነትን እንርሳው " - ብፁዕነታቸው ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ምን አሉ ? - የማይደፈር ሲደፈር አይተናል፤ ቤተክርስቲያን ስትደፈር ዝም አንልም። - " ፖለቲካው የፖለቲካው መስመር ሲደፈር ዝም እንደማይል ሁሉ እኔም ደግሞ የመጀመሪያዋም የመጨረሻዋም…
#ጥምቀት

" በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች እየተላለፈ ያለውን የበዓል አከባበር ክልከላን የሚገልጹ የሐሰት ዜናዎች ቤተክርስቲያንን አይወክሉም " - ብፁዕ አቡነ አብርሃም

በዓለ ጥምቀትን አስመልክቶ የሚተላለፉ መልእክቶች የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ ላይ ብቻ ያተኮሩ እንዲሆኑ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መመሪያ አስተላልፈዋል።

ብፁዕነታቸው በተለያዩ ቋንቋዎች ለተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ቃለ መጠይቅና ምላሽ እንዲሰጡ ለተመረጡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በሰጡት አባታዊ መመሪያ የቅድስት ቤተክርስቲያን መልእክት የሚተላለፈው በማእከል በመሆኑ የማእከሉን መልእክት ብቻ እንዲያስተላልፉ መመሪያ የሰጡ ሲሆን ከግል አስተያየት መቆጠብ እንደሚገባም አበክረው አሳስበዋል።

ቤተክርስቲያኗ የሰላም ሰባኪ እንደመሆኗ መጠን የቤተክርስቲያን መልእክት ሲተላለፍ ሰላም ላይ ማተኮርና በዓል ለማክበር የሚወጡ ምእመናን በዓሉ በሰላም አክብረው እንዲመለሱ መልእክት ማስተላለፍ እንደሚገባ ግልጽ መመሪያ ሰጥተዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያዊ ሁሉም ሃይማኖቶች ተከባብረው የሚኖሩባት ሀገር መሆኗ ከሚገለጽባቸው መንገዶች አንዱ ይህ በዓል የሚከበርባቸውን ቦታዎች ለማጽዳትና ሥርዓት ለማስከበር ጥረት እያደረጉ ያሉ የሌሎች ሃይማኖት አባላትን በአባትነት ያመሰገኑት ብፁዕነታቸው ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች የሚገኙ የሌሎች ቤተ እምነቶችን ማክበር እንደሚገባ ለሁሉም ካህናትና ምእመናን አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች እየተላለፈ ያለውን የበዓል አከባበር ክልከላን የሚገልጹ የሐሰት ዜናዎች ቤተክርስቲያንን የማይወክሉና ቤተክርስቲያናችን በዓሉን በሰላም ለማክበር ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር እያደረገች ያለውን ጥረት ከግንዛቤ ያላስገባ መሆኑን ብፁዕነታቸው አሳውቀዋል።

#EOTCTV

@tikvahethiopia