TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EMA

ከ600 በላይ የሕክምና ባለሙያዎችና ውሳኔ ሰጪዎች ውይይት ሊያደርጉ መሆኑን የኢትዮጵያ ሕክምና ማኀበር ገለጸ።

የማኀበሩ ራዕይ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ማግኘት የሚችል ጤናማና የበለጸገ ማህበረሰብ እውን ለማድረግ ይረዳ ዘንድ ከሚመለከታቸው የመንግሥት መ/ቤቶች የጤና ሚኒስትርን ጨምሮ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከስፔሻሊቲ ሶሳይቲዎች፣ ከማኀበሩ አባላት ጋር በመሆን ምክክር የሚያደርግበት ዓመታዊ ጉባዔ ያካሂዷል።
      
በዚሁ መሠረት ዘንድሮ 60ኛውን ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ የጤና አውደ ርዕይ ከየካቲት 29 እስከ 30/2016 ዓ/ም በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ለማካሄድ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን አስታውቋል።

በዓመታዊ የሕክምና ኮንፈረንሱ (AMC፣ በውስጥ እና ውጭ ሀገራት የሚኖሩ እውቅ የህክምና ባለሙያዎች ያላቸውን እውቀት፣ የምርምር ግኝቶችን፣ የሕክምና ልምዶችን ለመለዋወጥ የሚረዳ መድረክ መሆኑንም አመላክቷል።

በጉባዔው የዓመቱን መሪ ቃል መነሻ በማድረግ የፓናል ውይይቶች እንደሚካሄዱ፣ CEU የሚያስገኙ የሙያ ማሻሻያ ስልጠናዎች እንደሚሰጡ እንዲሁም የሳይንሳዊ ግኝቶች የሚቀርቡበት ክፍለጊዜም እንደተዘጋጀ ተጠቁሟል።

በማህበሩ 60ኛው ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ የጤና አውደ ርዕይ፦ 

* ከ600 በላይ የተከበሩ የሕክምና ባለሙያዎች
* ከሁሉም ክልል የሚመጡ የማህበሩ አባላት ተወካዮች፣ 
* ከተለያዩ የጤና ባለሙያዎች ማኀበራት፣
* ከስፔሻሊስቶች ማኀበራት የተውጣጡ ተወካዮች፣
* የሕክምና ኮሌጅ ኃላፊዎች
* የመንግሥት አካላት
* የጤና አውደ ርዕይ ከ100 በላይ ድርጅቶች 
* ከ2,000 በላይ ሰዎችም ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል። 

በተጨማሪም በየዓመቱ ተጠባቂው የኢትዮጵያ ሕክምና ማኀበር የሽልማት መርሀ ግብር ግብርም በ2016 ዓ/ም በአራት ዘርፍ ማለትም ፦

• “የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የአመቱ ምርጥ የህክምና ተማሪዎች
• የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የሕይወት ዘመን 
• የኢትዮጵያ ሕክምና ማኀበር ተፅዕኖ ፈጣሪ እና ምርጥ ወጣት ሀኪም
• የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የ2016 የዓመቱ ምርጥ ተቋም ሽልማት የሚሰጥ ይሆናል” ተብሏል።

የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር ከተመሰረተ 1954 ዓ/ም ጀምሮ በሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፣ በታካሚዎች ደኀንነት እና በአጠቃላይ በሕክምናው ዘርፍ ቁልፍ ሚና በመጫዎት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ማኀበር ነው፡፡ 

#AddisAbabaTikvahFamily

@tikvahethiopia
#DigitalEthiopia

ዛሬ " የዲጂታል ኢትዮጵያ " የግምገማ መድረክ በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ተካሂዷል።

ጠ/ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ የፌደራል እንዲሁም የክልል ከፍተኛ አመራሮች እና የዘርፉ ተዋናዮች በመድረኩ ተሳታፊ ነበሩ።

የ " ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 " ስትራቴጂ በዋናነት የዲጂታል መሰረተ ልማት በመገንባት እና በማስፋት የአገሪቱን ምጣኔ ኃብታዊ እድገት ማፋጠንን ዓላማ ያደረገ ሲሆን በአምስት ዓመታት ውስጥ ለመተግበር የታቀደ ነው።

ዛሬ ላይ የስትራቴጂውን የ4 አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል።

- ዲጂታል ሊትረሲን ለማስፋት፤
- የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቱን የማሳደግ
- የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፤
- የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትና የሳይበር ጥበቃ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በሚመለከታቸው የመንግሥት ኃላፊዎች ገለጻ ተደርጎባቸዋል።

በዚህ መድረክ በቅርቡ በንግድ ባንክ ላይ ያጋጠመው ጉዳይ በስፋት እንደማሳያ ሲቀርብ ነበር።

ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የብሔራዊ ባንክ ገዢው አቶ ማሞ ምህረቱም አስተያየት ሰጥተው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን አሉ?

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ " በሳይበር ጥቃት በ2022 በዓለም ላይ 9 ትሪሊዮን ዶላር በጠላፊዎች ተመዝብሯል" ብለዋል።

" ይህ ያጋጠመው ችግር ሰዎች አቅደው አምሯቸውን ተጠቅመው ለማለት ያስቸግራል፤ ከውስጥ ያሉ ሰዎች የፈጠሩት ችግር ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ይሄ ማለት [የሳይበር ጥቃት] አይከሰትም ግን ማለት አይደለም። በሺዎች የሚቆጠሩ አታኮች በየቀኑ ተቋሞቻችን ላይ ይፈጸማሉ፤ ኢንሳ ብትመጡ ይሄንን ትመለከታላችሁ " ብለዋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዢው ምን አሉ?

አቶ ማሞ ምህረቱ " የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ችግር በውስጥ ሰዎች የተፈጠረ ነው [ Human Error] ነው " ብለዋል።

" በዚሁ አጋጣሚ የፋይናንስ ሥርዓቱ ግልጽ ነው። ምን አይነት ገንዘብ የት እንደተላከ ከየት እንደወጣ የት እንደገባ ይታወቃል። በእንደዚህ አይነት ስህተቶች የሚጠፋ ገንዘብ አይኖርም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" አሁን ላይ 80 በመቶ የወጣው ገንዘብ ተመላሽ ተደርጋል " ብለዋል።

ብሔራዊ ባንክ የዚህን ክስተት ሙሉ የምርመራ ውጤት በሳምንት ውስጥ ይፋ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

#AddisAbabaTikvahFamily

@tikvahethiopia