TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ለጥንቃቄ🚨

“ በጀኔተር ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ የ1 ሰው ሕይወት አልፏል ” - አቶ ንጋቱ ማሞ

ትላንት ምሽት 3:03 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ማርያም ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በእሳት አደጋ የ1 ሰው ሕይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና ሥራ አመራር ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው አቶ ንጋቱ ማሞ በሰጡት ቃል፣ “ ኤሌክትሪክ በመቋረጡ ጀነሬተር ለማስነሳት ነዳጅ በመጨመር ላይ የነበረ የ26 ዓመት የሆቴል ሠራተኛ በጀነሬተሩ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ ወዲያው ሕይወቱ አልፏል ” ብለዋል።

“ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በስፍራው ፈጥነው ቢደርሱም በጀነሬተሩ ላይ በተፈጠረው ከፍተኛ እሳት አስቀድሞ ሕይወቱ  አልፏል ” ነው ያሉት።

አቶ ንጋቱ፣ “ በጄኔሬተር የነዳጅ ታንከር ውስጥ ነዳጅ ከተጨመረ በኋላ #ቫልቩ በአግባቡ መዘጋቱን ማረጋገጥ ፣ እንዲሁም ጄነሬተሩ አስቀድሞ አገልግሎት ሲሰጥ ከቆየና ግለት ካለ ነዳጅ ከመጨመር መቆጠብ ያስፈልጋል ” ሲሉ አስገንዝበዋል።

በሌላ በኩል ፥ የበዓል ስራዎች እንቅስቃሴዎች አሁንም ድረስ ያልጠተናቀቁ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከኮሚሽን መስሪያ ቤቱ እየተላለፉ ያሉ የጥንቃቄ መልዕክቶች እንዲተገብር አሳስበዋል።

የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ሲያጋጥሙ ፣ እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት ማህበረሰቡ በኮሚሽኑ ስልክ #በ939 ላይ ፈጥኖ ደውሎ እንዲያሳውቅ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪ መረጃ ፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በስሊንደር ፍንዳታ ምክንያት የ1 ሰው ህይወት ማለፉን ገልጿል።

የድሮው ቄራ አካባቢ ትላንት ቀን 9:30 በአነስተኛ መጠጥ ቤት ውስጥ ድስት ተጥዶበት በነበረ ስሊንደር ላይ በተፈጠረው ፍንዳታ ዕድሜው 30 ዓመት የሚገመት 1 ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን በ3 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና ተወስደዋል።

ፖሊስ በበዓል ወቅት የምንጠቀማቸውን ምግቦች ስናበስል #ከሲልንደር_አጠቃቀም ጋር በተያያዘ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia