TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ምዕራብ_ጎንደር

በሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት የተለያዩ ሀገር ዜጎች ከግጭቱ በመሸሽ በምእራብ ጎንደር ዞን #መተማ_ዮኋንስ ከተማ በኩል እየገቡ መሆኑን የምዕራብ ጎንደር ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

የተፈጠረውን አለመረጋጋት ሸሽተው የሚመጡ የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜጎችን የምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮኋንስ ከተማ በሰላም እያስተናገደች ትገኛለች።

ሱዳን ላይ በተፈጠረው የውስጥ አለመረጋጋት ምክኒያት ጦርነቱን ሸሽተው ከካርቱም ወደ ጎረቤት ሀገር ኢትዩጵያ የሱዳን ዜጎችን ጨምሮ የ23 ሀገራት የተለያዪ ሃገራት ዜጎች እንደገቡና ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እየሄዱ ይገኛሉ።

በዚህም የምዕራብ ጎንደሯ የፍቅር ከተማ መተማ ዮሃንስ ከተማ እንግዶቿን እያስተናገደች ሲሆን በቀን ከ15-20 የሚሆኑ መኪናዎች ወደ ጎንደር እየሄዱ ይገኛሉ።

በዚህ የጦርነት ስጋት ሽሽት ህፃናት፣ ሴቶች እና አቅመ ደካሞች ይገኙበታል።

የመተማ ዮሃንስ ከተማ አስተዳደር፣ የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላትም ዜጎች ያለምንም እንግልት ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እንዲደርሱ ሰብአዊ ተግባራትን እያከናወኑ እንደሚገኙ ተገልጿል።

መረጃ / ፎቶ፦ የምዕራብ ጎንደር ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia