TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
' ስካይ ላይት ሆቴል ' ውስጥ ተሸሽገው ነበር የተባሉ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ኃላፊ ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልደታ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማት ጽ/ቤት ተወካይ ሃላፊ የነበሩት አቶ ቴዎድሮስ ፀጋዬ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ታሰሩ።

ግለሰቡ ሲፈለጉ ቆይተው ዛሬ ' ስካይ ላይት ሆቴል ' ውስጥ ተደብቀው ከነበሩበት መያዛቸውን የከተማ አስተዳደሩ አመልክቷል።

" ተጠርጣሪው በኮሪደር ልማት ስም ከመንግስት አሰራር እና ውሳኔ ውጪ  #በመደራደር ባልተገባ መንገድ ለግል ጥቅም ለማግኘት ሲሉ የካሳ ግምት በማናር ውስን የሆነዉን የህዝብ እና የመንግስትን መሬት ከአሰራር ውጪ በማሰተላለፍ ለግለሰቦች አላስፈላጊ ጥቅም በማዋል  ተጠርጥረው " መያዛቸው ነው የተገለጸው።

በተጨማሪ በክ/ከተማው ወረዳ 4 ዉስጥ በኮሪደር ልማት ኘላን ልማት ውስጥ የማይካተት ከመመሪያና አሠራር ዉጪ  6 መኖሪያ እና አንድ የንግድ ቤት የሆነውን  ከ ' ዋይልድ አፓርትመንት ' የተባለ ህንፃ ባለቤት ጋር ተመሳጥረው ቤቶቹን እንዲፈርሱ በማድረግና ለህንፃው ማስፋፊያ እንዲሆን የሰጡ መሆኑ ተመላክቷል።

የመንግስት ቤት ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ግለሰቦችም የእቃ የማጓጓዥያ ሳይከፈል እንዲነሱ በማድረጉ እንዲሁም " ምትክ ቦታ እስጣቿለው " ፤ " አንደኛ ቦታ አስቀይርላቿለው " እና የተለያዩ የማጭበርበር ወንጀሎችን በማድረግ ህብረተሰቡ ሲያደናግሩ ፤ ያልተገቡ ጥቅሞችን ሲያደርጉ ነበር ተብሏል።

ከተሸሸጉበት ' ስካይ ላይት ሆቴል ' ውስጥ የተያዙት ግለሰቡ " ከሀገር ውጪ ወተዋል " አስብለው እንደነበር ተገልጿል።

@tikvahethiopia