TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ለልምድ ልውውጥ " በሚል ከተላኩበት ኖርዌይ ያልተመለሱት የፓርቲ አባላት ምን አሉ ?

🔴 " በተደጋጋሚ የግድያ ሙከራም ተደርጎብኛል መመለስ የማልችልበት ውስብስብ ጉዳይ ነው የገጠመኝ " -ወ/ሮ አበበች ደቻሳ

🔵 " መመለስ የማልችልባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ በማወቄ ላለመመለስ ወስኛለሁ " -ወ/ሮ ቅድስት ግርማ


የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) የሴቶች ጉዳይ ሃላፊ ወ/ሮ አበበች ደቻሳ እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ የነበሩት ወ/ሮ ቅድስት ግርማ በመስከረም አጋማሽ ለልምድ ልውውጥ ወደ ኖርዌይ በሄዱበት እዛው መቅረታቸውንና ወደ ሀገር አለመመለሳቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ሁለቱ የፓርቲ አባላት ወደ ኖርዌይ ያቀኑት መስከረም 18/2017 ዓ/ም የነበረ መሆኑን እና በፖለቲካ ችግሮች ምክንያት እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ መገደዳቸውን ከሚገኙበት ሃገር ሆነው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል።

ከሃገር እስከወጡበት ጊዜ ድረስ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የድባጤ ወረዳ የውሃ ፣ማዕድን እና ኢነርጂ ጽ/ቤት ሃላፊ እና በቦዴፓ የሴቶች ዘርፍ ሃላፊ የነበሩት ወ/ሮ አበበች ደቻሳ ፥ " ብዙ መስዋዕትነት ከፍያለሁ በተደጋጋሚ እኔም ባለቤቴም ለእስር ተዳርገናል አባቴም በግፈኞች ተገድሏል አለመመለሴ እርግጥ ነው ላለመመለስም ወስነናል " ብለዋል።

የመቅረት ውሳኔው የታሰበበት ሳይሆን ድንገተኛ ውሳኔ መሆኑን ጠቁመው " ስወጣ ሄጄ እቀራለሁ ብዬ አስቤበት አልነበረም ከነ ችግሩ በሃገሬ እታገላለሁ ብዬ እንጂ፣ ነገር ግን ከተመለስኩ ካሳለፍኩት በላይ የሆነ ችግር እየጠበቀኝ መሆኑን ስላረጋገጥኩ ነው የቀረሁት " ሲሉ ገልጸዋል።

" የሃገሪቱ ፖለቲካ ችግር ውስብስብ ከመሆኑም በላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ነው " ያሉት ወ/ሮ አበበች " በክልሉ ያለው አመራር በኢንቨስትመንት መሬት እና በማዕድን ቦታዎች ዝርፍያ ተሰማርቷል " ሲሉ ከሰዋል።

በወረዳው የማዕድን ጽ/ቤት ሃላፊነት ላይ በነበሩበት ወቅት የታዘቡትን ሲያስታውሱ " ትልቁ ችግር ሙስና ነው ይህንን ተቃውመህ በህይወት መኖር አትችልም ይህን አዕምዬ ሊቀበል አልቻለም ብዙ ታግያለሁ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎች ይደርሱኝ ነበር በመጨረሻም ለእስር ተዳርጌ ነበር በተደጋጋሚ የግድያ ሙከራም ተደርጎብኛል መመለስ የማልችልበት ውስብስብ ጉዳይ ነው የገጠመኝ " ብለዋል።

ከሃገር ከመውጣታቸው በፊትም ከባለቤታቸው እና ከልጆቻቸው ጋር ለእስር ተዳርገው እንደነበር ገልጸው ባለቤታቸው ብቻ በተለያዩ ጊዜያት ለ3 ወራት ያህል ለእስር ተዳርገው እንደነበር አስታውሰዋል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዉ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ የነበሩት ወ/ሮ ቅድስት ግርማ በበኩላቸው ላለመመለሳቸው ምክንያት ፓርቲያዊና ሃገራዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን እንደምክንያት ጠቅሰዋል።

" እንዳልመለስ ያደረጉኝ ድንገተኛ ምክንያቶች ቢኖሩም እዚህ ከመጣሁ በኃላ መመለስ የማልችልባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ በማወቄ ላለመመለስ ወስኛለሁ " ብለዋል።

" ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለኢትዮጵያ ያስፈልጋል ብዬ የማምን ሰው ነኝ " ያሉት ወ/ሮ ቅድስት ፥ " ነገር ግን እያደረግናቸው ያሉ ሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግሎች ቆመንለታል ያልነውን ማህበረሰብ ከመገደል ፣ መፈናቀል እና ሞት አላዳነውም " ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

" ምንም እንዳላየ ሆኖ መቀጠል ከአዕምሮ በላይ ነው ሃገር ውስጥ ሆኖ ይህን ማድረግ አይቻልም ለህዝቤ ድምጽ መሆን ያስፈልጋል ብዬ ስለማምን ነው ይሄን ውሳኔ የወሰንኩት " ሲሉ ከሀገር ወጥተው የቀሩበት ምክንያት አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ የኢዜማ አባል ፤ አባሏ በስራ ገበታቸው ላይ አለመኖራቸው በማስረዳት " ለምን እንዳልተመለሱ የምናውቀው ነገር የለም " ማለቱ ይታወሳል።

ወ/ሮ ቅድስት በበኩላቸው " ከመቅረቴ ቀደም ብዬ ያለውን ነገር እና ላለመመለስ መወሰኔም ለፓርቲው ስራ አስፈጻሚዎች አሳውቄያለሁ ኢዜማ ውስጥ ያለው መቧደን እና መገፋፋቱ ፓርቲው እደርስበታለሁ የሚልበት ቦታ ላይ የማያደርስ በመሆኑ ፣ ይህም ለእኔ ፈታኝ መሆኑን እና የእኔ መገፋት ከመንግስት ብቻ ሳይሆን ከፓርቲውም ጭምር መሆኑን አሳውቅያለሁ " ብለዋል።

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኩል ለልምድ ልውውጥ ወደ ኖርዌይ ያቀኑት የምክር ቤቱ የሴቶች ክንፍ ስራ አስፈጻሚዎች ውስጥ የሚገኙ የኢዜማ ፣ ቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፣ ኦነግ እና የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ወብን) ፓርቲ አባላት የነበሩ ሲሆን
#የኦነግ እና #የወብን አባላት የልምድ ልውውጡን አጠናቀው በወቅቱ ወደሃገር ተመልሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia