TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #Somalia ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የ #AUSSOM ተልዕኮ ውጤታማ ለማድረግ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳወቀ። በመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በሶማሊያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጉ ተነግሯል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባሰራጨው መረጃ ፥ የልዑካን ቡድኑ ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ ማህሙድ ጋር ውጤታማ ውይይት…
#Ethiopia 🤝 #Somalia

በሶማሊያ በሁለትዮሽ ስምምነት መሠረት ተሰማርቶ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሁኔታን በተመለከተ አሠራር ለመዘርጋት የሁለቱ አገራት የጦር አዛዦች ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በኢትዮጵያው መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና በሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ኃይሎች የመከላከያ ሠራዊት አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ኦዳዋ ዩሱፍ ራጌ መካከል የተደረሰው ስምምነት በሶማሊያ ያለው የኢትዮጵያ ጦር ስምሪትን፣ እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም አጠቃላይ ክንዋኔዎች የሚመለከተውን 'ስታተስ ኦፍ ፎርስ አግሪመንት' ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ ነው።

አንዲት አገር ጦሯን በሌላ ውጭ አገር በምታሰማራበት ወቅት የጦሩ ስምሪት፣ ተግባራት፣ ኃላፊነት፣ መብቶችን የሚመለከተው በአገራቱ መካከል የሚደረስ አሳሪ (ሕጋዊ ስምምነት) ስታተስ ኦፍ ፎርስ አግሪመንት ይሰኛል።

ይህ 'ስታተስ ኦፍ ፎርስ' ስምምነት በአውሮፓውያኑ 2023 በአገራቱ መካከል የተፈረመው የመከላከያ ትብብር የመግባቢያ ስምምነት ዋና አካል እንደሚሆን ተነግሯል።

በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሚመራ ልዑክ በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ የካቲት 15/2017 ዓ.ም. ባደረገው የአንድ ቀን ይፋዊ ጉብኝት ይህንን ስምምነት ጨምሮ ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በሶማሊያ እና በቀጠናው ሰላም፣ ደኅንነት፣ ፀጥታ እና የመረጋጋት ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ሁለቱ የጦር አዛዦች የአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ (ኤዩሶም) ጅማሮ አድንቀው ከዚህ ቀደም በነበረው የአፍሪካ ኅብረት የሰላም እና የፀጥታው ምክር ቤት አትሚስ ስኬቶች ማስቀጠል አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በኤዩሶም ስምሪት ላይ እንዲካተት የጦር አዛዦቹ በዚህ ወቅት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

በሶማሊያ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ውዝግብ በአንካራ ስምምነት መፈታቱን ተከትሎ ሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮችን በአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ (ኤዩሶም) ውስጥ ላለማካተት አሳልፋው የነበረውን ውሳኔ ልትቀለብስ እና በተልዕኮው ለማካተት እያጤነች እንደሆነ ከዚህ ቀደም ተዘግቦ ነበር።


#SomaliaNationalTV #BBCAMAHRIC

@tikvahethiopia