TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ስለ ሀገሬ ምን ያህል አውቃለሁ ?

" ፊቼ ጨምባላላ "

የሲዳማ ሕዝብ የጨረቃና ከዋክብትን አቀማመጥ በማጥናት አዲስ ዓመት ያከብራል ፤ ይኸው በዓል ፊቼ ጨምበላላ ነው የሚባለው።

እንደ ሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች " ፊቼ ጫምባላላ " መከበር ከጀመረ ከ1800 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል።

በዓሉ የሲዳማ ሕዝብ ማንነቱን ከተረዳበት ጊዜ አንስቶ በድምቀት ሲከበር ቆይቷል፤ አሁንም እየተከበረ ይገኛል።

ፊቼ ጨምበላላ በዓል የሚከበርበት ቋሚ ቀን የለውም። በዓሉ የሚከበርበት ቀን በአያንቱዎች ጥቆማ መሰረት ነው የሚቃረጠው።

'የፊቼ ጨምበላላ ዋነኛ ትርጉም ሰላም ነው' ፤ አንድነትና ፍቅር የበዓሉ መለያ ነው። በዚህ በላይ የተጣሉ ሰዎች ይታረቃሉ። ሃዘን ላይ የነበሩ ሰዎችም የሃዘን ልብሳቸውን ይቀይራሉ።

በዚህ በዓል ከቀዬው ርቆ የነበረ ሰው ወደቀዬው ይመለሳል፤ ለዚህ በዓል ተብሎ እርድ አይፈጸምም፤ ስጋም አይበላም። ክብቶችን #መምታትም ክልክል ነው። ላሞች ሳር የበዛበት መስክ ላይ ይሰማራሉ።

ሌላው በሲዳማ ሕዝብ ዘንድ በፊቼ ጨምበላላ በዓል ወቅት ማረስ #ነውር ነው፤ ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ የፊቼ ጨምበላላ በዓል የሲዳማ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን #የተፈጥሮም ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው።

" ፊቼ " የአዲስ ዓመት በዓል ዋዜማ ሲሆን፤ " ጨምበላላ " ደግሞ የአዲስ ዓመት መጀመሪያው ቀን ሲሆን የሲዳማ ሕዝብ አዲስ ዓመትን ሲቀበል፤ ዓመቱ የብልጽግና እንዲሆንላቸው 'ፊቼ ጄጂ' ይላሉ።

ፊቼ ጄጂ !
#ኢትዮጵያ
#ሲዳማ

@tikvahethiopia