TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የጁባላንድ መንግሥት ከሶማሊያ ፌዴራሉ መንግሥት ጋር ያለውን ግንኙነት ማቋረጡን ይፋ አደረገ። የጁባላንድ ካቢኔ ስብሰባ ካደረገ በኃላ ይፋ እንዳደረገው  " ሙሉ በሙሉና በይፋ ከሶማሊያ የፌዴራል መንግሥት ጋር ያለውን የስራም ሆነ ማንኛውንም ግንኙነት " አቋርጧል። የጁባላድ መንግሥት ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድን ፦ - ኃይላቸውን ያለ አግባብ በመጠቀም - የእርስ በእርስ ጦርነት በማነሳሳት…
#Jubaland #Somlaia

ከሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ጋር ሁሉንም ግኑኝነቴን አቋርጫለሁ ፤ ተቆራርጫለሁ ያለው የጁባላንድ አስተዳደር እና የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ዛሬ ወደ ግጭት ገብተዋል።

ዛሬ ከቀትር ጀምሮ ራስኮምቦኒ ላይ ከፍተኛ ውጊያ መደረጉ ተነግሯል።

ሁለቱም ወገኖች ግጭት መነሳቱን ገልጸው ግጭቱን ማን አስጀመረ በሚለው ላይ እርስ በእርስ እየተወነጃጀሉ ነው።

@tikvahethiopia
#Somalia #Eritrea

የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ኤርትራ ናቸው።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኤርትራ ፣ አስመራ መግባታቸው ተነግሯል።

አስመራ ሲደርሱ ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ነው ኤርፖርት ተገኝተው የተቀበሏቸው።

የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ ፣በቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ብለዋል።

ፕሬዜዳንቱ በቱርክ፣ አንካራ ከኢትዮጵያ ጋር ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቃሚነት ጉዳይ ላይ ስምምነት ከፈረሙ በኃላ ነው ኤርትራ የሄዱት።

አንደንድ ዘገባዎች የኤርትራው እና የሱማሊያው መሪ የአንካራውን ስምምነት አጀንዳቸው ሊያደርጉት እንደሚችሉ አሳይተዋል።

የሶማሊያው መሪ ከዚህ ቀደም ወደ ኤርትራ በመመላለስ የሚታወቁ ሲሆን በተለይ ግን ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከፈረሙ በኃላ እንዲሁም ኢትዮጵያ ለህዝቦቼ የባህር በር ያስፈልጋቸዋል ይህ የህልውና ጉዳይ ጭምር ነው በማለት አቋማን ይፋ ካደረገችና ዓለም አቀፍ አጀንዳ ካደረገችው በኃላ ደጋግመው ኤርትራ ፣ አስመራ ኢሳያስ ጋር ተመላልሰዋል።

የኤርትራው መሪ በነዚህ ወቅቶች አንድም ጊዜ ሶማሊያ፣ ሙቃዲሾ ለጉብኝት ብለው ሄደው አያውቁም።

ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ የግብፅ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ መሪዎች በአስመራ የሶስትዮሽ ጉባኤ አካሂደው የሶማሊያ ተቋማት እና ጦር ድንበሯን ለመጠበቅ እና የግዛት አንድነቷን ለማስጠበቅ የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸው የሚዘነጋ አይደለም።

#Somlaia #Eritrea

@tikvahethiopia