TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሶማሊያ ጦር 41 የአልሸባብ ታጣቂዎችን ገደለ።

ጦሩ በዛሬው ዕለት በመዱግ ክልል ውስጥ የወሲል ከተማን ሊያጠቁ ነበር / ጥቃት ሊከፍቱ ነበር ያላቸውን 41 የአልሸባብ ታጣቂዎችን ገድሏል።

በነበረው ግጭት 3 ከሶማሊያ ጦር እንዲሁም 5 ከጋልሙዱግ የዳርዊሽ ኃይሎች መገደላቸው ተሰምቷል።

በሌላ መረጃ የሶማሊያዋ #ፑንትላንድ ዛሬ 21 የአልሸባብ አባላትን ዛሬ ረሽናለች።

አባላቱ ጋልካዮ፣ ቃርዶ እና ጋሮዊ በተባሉ የተለያዩ ሶስት አካባቢዎች ላይ መረሸናቸውን የፑንትላንድ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዳኛ ጄነራል መሃሙድ አብዲ መሃመድ አረጋግጠዋል፡፡

በፍርድ ቤቱ ውሳኔ የተገደሉት የአል ሸባብ አባላቱ ባለፉት 13 ዓመታት ውስጥ በተለያዩ የፑንትላንድ አካባቢዎች በተፈጸሙ ግድያዎች ጥፋተኛ ነበሩ ተብሏል፡፡

ከጎሳ መሪዎችን፣ ጋዜጠኞች፣ ከመንግስት ባለስልጣናት ግድያ ጀርባ እንደነበሩ ፍርድ ቤት ገልጿል።

መረጃው ከጎብጆግ ፣ አልዓይን ኒውስ ፣ SNTV (የሶማሊያ ብሄራዊ ቴሌቪዥን) የተውጣጣ ነው።

@tikvahethiopia
#Puntland #Somalia

ፑንትላንድ ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ዕውቅና መስጠት ማቆሟን ይፋ አድርጋለች።

ከፊል ራስ ገዝ የሆነችው #ፑንትላንድ በሞቃዲሾ ለሚገኘው ለሶማሊያ የፌደራል መንግሥት ከዚህ ቀደም ሰጥታው የነበረውም ዕውቅና አንስታለች።

የፑንትላንድ መንግሥት ካቢኔ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዶ ፑንትላንድ የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ተቋማት ላይ የነበራትን መተማመን በማጣቷ ትሰጥ የነበረውን ዕውቅና እንዳነሳች አሳውቋል።

ምክንያቱ ምንድነው ?

የሶማሊያ መንግሥት ፓርላማ ብዙ ባወዛገበ ሂደት በአገሪቱ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።

የሕገ መንግሥት ማሻሻያው ፕሬዝዳንቱ የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር የማሰናበትን ሙሉ ሥልጣን የሚሰጥ ሲሆን ‘ አንድ ሰው አንድ ድምጽ ’ የሚለውን ዓለም አቀፍ የምርጫ መርህ ተግባራዊ እንዲሆን የሚያደርግና ሌሎችም ማሻሻያዎች አሉበት።

NB. በሶማሊያ #ውስብስብ የሆነውን እና በጎሳ መሠረት የሚደረገውን ምርጫ ከ50 ዓመታት በላይ ስትጠቀምበት ቆይታለች፡፡ አሁን ' አንድ ሰው አንድ ድምፅ ' የሚለው ማሻሻያ በፑንትላንድ ባለልስጣናት ተቃውሞ ገጥሞታል።

በአጠቃላይ የፌዴራል መንግሥት ያካሄደው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ በፑንትላንድ አልተወደደም ውድቅም ተደርጓል።

ፑንትላንድ ፤ " በጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት ሕገ መንግስታዊ ሂደት እስከሚፈጠር ድረስ የፑንትላንድ አስተዳደር ለፌዴራል ተቋማት እውቅና አይሰጥም፣ ተቋማቱ ላይም እምነት የለውም " ብላለች።

ሕዝበ ውሳኔ (#ሪፈረንደም) የሚደረግበት ሕገ መንግስት እስከሚወጣ ድረስ፣ ፑንትላንድ የራሷ የሆነ መንግስታዊ ስልጣን እንደሚኖራት አስታውቃለች፡፡

ከአሁን በኋላ ፍላጎቷን ለማስጠቅ ከማዕከላዊ የሶማሊያ መንግሥት እውቅና ውጪ በራሷ አማካይነት #የውጭ_ግንኙነቶችን እንደምታደርግ ገልጻለች።

ይህ የፑንትላንድ ውሳኔ ከሶማሊያ ተነጥሎ ነጻ አገርነትን ከማወጅ ጋር ሊስተካከል እንደሚችል በመጥቀስ #ከሶማሊላንድ ቀጥሎ ለፌደራል መንግሥቱ ሌላ ራስ ምታት እንደሚሆን ተንታኞች እየገለጹ ነው።

ፑንትለንድ በተፈጥሮ ሃብቶችና #በቦሳሶ_ወደቧ በመተማመን እ.አ.አ 1998 ነው ከፊል ራስ ገዝ መሆኗን ያወጀችው። እራሷን እንደ ነጻና ሉኣላዊ ሀገር የምትቆጥረው የሶማሊላንድ ጎረቤትም ናት።

መረጃው ከቪኦኤ እና ቢቢሲ የተውጣጣ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሶማሊያ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት #ለማቋረጥ በመወሰን በአገሪቱ የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደር እና ዲፕሎማቶች ለቀው እንዲወጡ ማዘዟ ተሰምቷል። አዲስ አበባ ያሉትን አምባሳደሯንም ጠርታለች። የሶማሊያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስቴር ይፋ እዳደረገው በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር…
#Update

" የቀን ህልም ነው ... ምንም የማይረባ ፤ እኛን አያሳስበንም " - ሶማሌላንድ

" የሶማሊያ መንግሥት አንዳች ስልጣን የለውም " - ፑንትላንድ

#ፑንትላንድ እና #ሶማሌላንድ የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥትን ማስጠንቀቂያ ውድቅ አደረጉ።

የሶማሊያ መንግሥት ፤ #ኢትዮጵያ ከሶማሌላድ ጋር ያደረገችውን የመግባቢያ ስምምነት ምክንያት በማድረግና " በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ እየገባሽ ነው " በማለት ሞቃዲሹ ያሉት የኢትዮጵያ አምባሳደር በ72 ሰዓታት ውስጥ ከሀገሪቱ ለቀው እንዲወጡ አዟል።

ከዚህ ባለፈ ግን በሶማሌላድ ፣ #ሀርጌሳ እና በፑንትላንድ፣ #ጋሮዌ የሚገኙት የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤቶች በ7 ቀን እንዲዘጉ አስጠንቅቋል። ኢትዮጵያ ዲፕሎማቶችም በ1 ሳምንት ውስጥ ሀገር ለቀው እንዲወጡ አዟል። ካልሆነ ወደሌላ እርምጃ ገባለሁ ብሏል።

ለዚህ ማስጠንቀቂያ ፑንትላንድ እና ሶማሌላንድ ምላሽ ሰጥተዋል። የሶማሊያ ፌዴራል መንግስትን ማስጠንቀቂያም ውድቅ አድርገዋል።

ዛሬ ምሽት ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ሶማሊኛ ክፍል አጭር ቃላቸውን የሰጡት የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚንስትር አምባሳደር ሮዳ ጃማ ፥ " የቀን ህልም ነው፤ ...ምንም የማይረባ ፤ እኛን አያሳስበንም " ሲሉ ማስጠንቀቂያውን አጣጥለዋል።

የሶማሊያ መንግሥት ስልጣኑ በቪላ ሱማሊያ እና በሙቃዲሾ ዘሌን ቤዝ የተወሰነ መሆኑን በመግለጽ " በውስጥ ጉዳዩ ላይ ቢያተኩር ነው የሚሻለው ... ከአቅሙ በላይ በሆነ ጉዳይ ጊዜ ማባከኑን ማቆም አለበት " ብለዋል።

የፑንትላንድ የማስታወቂያ ሚኒስትር ማህሙድ አይዲድ ድሪር  በበኩላቸው " የሶማሊያ ፌደራል መንግስት በጋሮዌ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት የመዝጋት አንዳችም ስልጣን የለውም " ብለዋል።

@tikvahethiopia