TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከ200 በላይ #የጥፋት_ሀይሎች በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ወረዳ ገንገን ቀበሌ ህገ ወጥ #ወታደራዊ_ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ከ200 በላይ ወጣቶች በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል፡፡

የክልሉ የሰላም ግንባታ እና የፀጥታ ቢሮ ም/ሀላፊ ኮማንደር አብዱላዚም መሀመድ ለኢቢሲ እንደተናገሩት ወጣቶቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የብሄራዊ መረጃና ደህንነት፣ የመከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ እና የክልሉ የፀጥታ ሀይል በጋራ ባካሄዱት ኦፕሬሽን ነው።

የጥፋት ሀይሎቹ ከጥር 25/2011 ጀምሮ ከገንገን በመነሳት በሆሞሻ፣ ሸርቆሌ እና መንጌ ወረዳዎች አቋርጠው ወደ ኦዳ ቢልዲጊሉ ወረዳ በማቅናት የጥፋት እቅዳቸውን ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ ነው በቁጥጥር የዋሉት ብለዋል ኮማንደር አብዱላዚም።

#የጥፋት_ሀይሎቹ ሲጠቀሙበት የነበረ4 ክላሽንኮቭ፣ 1 ጅምስሪ፣ 1 ብሬን እና 4 ኋላ ቀር መሳሪያ በቁጥጥር መዋሉን ኮማንደር አብዱላዚም ተናግረዋል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉምዝ‼️

በአሶሳ ወረዳ ከ190 በላይ የሚሆኑ የሚሊሺያ አባላት ከክልሉ መንግስት እውቅና ውጭ #ወታደራዊ ስልጠና መውሰዳቸው ተገለፀ። ይህን ባደረጉ አመራሮች ላይም ህጋዊ #እርምጃ ተወስዶባቸዋል።

በክልሉ የሰላም ግንባታና የፀጥታ ቢሮ የሚሊሺያ ዘርፍ ሃላፊ አቶ #ደርጉ_ዚያድ ለኢቢሲ እንደተናገሩት በክልሉ ደረጃ የሚሊሺያ ሰራዊትን በአዲስ መልክ ለማደራጀት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከሰሞኑ የሚሊሺያ ሰራዊት አባላት ግምገማ የተካሄደ ሲሆን ለውጡን ማስቀጠል የሚችል የሚሊሺያ ሰራዊት መዋቅር ለመዘርጋት በሚያስችል መልኩ ግምገማ ተካሂዷል። በዚህም ከአሶሳ ወረዳ ብቻ 140 የሚሊሺያ አባላት በክብር ተሰናብተዋል። እንዲሁም ሰኔ 17 በአሶሳ ከተማ ተከስቶ በነበረው ግጭት የተጠረጠሩ 9 የሚሊሺያ አባላት በህግ #ቁጥጥር ስር ውለዋል።

በአሶሳ ወረዳ 190 የሚሆኑ የሚሊሺያ ሰራዊት ከክልሉ መንግስት እውቅና ውጭ ወታደራዊ ስልጠና ወስደዋል ያሉት አቶ ደርጉ ይህን ባደረጉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸው ብለዋል። የክልሉን የሚሊሺያ ሰራዊት በአዲስ መልክ ለማደራጀት እየተሰራ መሆኑን አቶ ደርጉ ለኢቢሲ ተናግረዋል።

Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia