TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ለረጅም ጊዜ ኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦባት የቆየችው ላሊበላ ከተማ ዛሬ እንደገና የኤሌክትሪክ ኃይል እንዳገኘች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል። ከላሊበላ ከተማ በተጨማሪ ላስታ ወረዳና ሙጃ ከተማ ኤሌክትሪክ እንዳገኙ ተገልጿል። እነዚህን አካባቢዎች መልሰው ኃይል ያገኙት በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የአላማጣ - ላሊበላ የ66 ኬ.ቮ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ…
#Update

" የሁመራና ወልቃይት ከተሞች #በአጭር_ጊዜ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያኙ ይሰራል ። " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

የሁመራ - ወልቃይት - ሽሬ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እየተጠገነ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ ገልጿል።

በጦርነት የወደሙ መሰረተ ልማቶችን ለመጠገን ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ስራዎቹን በአጭር ጊዜ አጠናቆ ህብረተሰቡ #ብርሃን እንዲያገኝ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።

#የሁመራ - #ወልቃይት - #ሽረ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች እና የማከፋፈያ ጣቢያ የፍተሻና የጥገና ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የገለፀው ተቋሙ " ከሁመራ እስከ ሽሬ ባለው ባለ 230 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር በተደረገው የፍተሻና ጥገና ሥራ 67 ቦታዎች ላይ የኮንዳክተር እንዲሁም 3 ቦታዎች ላይ የፋይበር ኦፕቲክስ መቆራረጥ አጋጥሟል። " ብሏል።

የሁመራና ወልቃይት ከተሞች እና አካባቢያቸው ለረጅም ጊዜ ያህል ኃይል ተቋርጦ የቆየ በመሆኑ #በአጭር_ጊዜ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያኙ ይሰራል ሲል አክሏል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
 " ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከተለው ነገር ሁሉ የአማራ ክልል ሙሉውን ኃላፊነት ይወስዳል " - የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ምን አለ ? " የአማራ ክልል የትግራይ መሬት በካርታው በማስፈር የትምህርቱ ሰርዓቱ አካል በማድረግ እያስተማረበት ይገኛል " ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ከሰሰ። " ክልሉ የትግራይ መሬት በሚመለከት በስርዓተ ትምህርቱ ያሰፈረው…
ራያ ላይ ምን እየሆነ ነው ?

“ ህወሓት የፕሪቶርያውን ስምምነት በግልፅ በመጣስ ራያ ላይ ጦርነት ከፍቷል ” - የአላማጣና አካባቢው አመራር

የትግራይ እና አማራ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ ከሚያነሱበት አንዱ በሆነው ራያ አላማጣ አካባቢ ትላንትና " ህወሓት " ተኩስ መክፈቱን፣ በዚህም በሰው ሕይወት ላይ ሞትና የአካል ጉዳት ሙድረሱን አካባቢውን ከሚያስተዳድሩ አመራሮች (ባለስልጣን) አንደኛው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አንድ የአካባቢው አመራር (ባለስልጣን) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ ራያ ላይ  አዲስ ነገር አለ። ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በግልፅ በመጣስ ራያ ላይ ጦርነት ከፍቷል ” ብለዋል።

“ ቀን ላይ አንድ ሰው ሕይወቱ አልፏል። ሁለት ቆስለው ወደ ደሴ ሪፈር ተብለዋል። ደንበሩን በማለፍ የራያ አላማጣ ወረዳ አዳዲስ ቀበሌዎች ተቆጣጥሯል ” ሲሉ አክለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጦርነቱ የተከፈተው በምን ሰዓት ነው ? በዬት በኩል ነው የተከፈተው ? አሁን ተኩስ አለ ? በቁጥጥር ስር የሆኑት ቀበሌዎች እነማን ናቸው ? ከሰሞኑን ለጦርነት አመላካች ጉዳዮች ነበሩ ? ሲል ለአመራሩ ጥየቄ አቅርቧል።

አመራሩም ፣ “ ጦርነቱን የጀመሩት ሰኞ ሌሊት 6:00 አከባቢ ሲሆን፣ እስከ ቀን 6:30 ድረስ ነበር። መከላከያ ለራያ ምሊሻ ‘ወደ ኋላ ተመለሱ እነርሱም ይመለሳሉ’ በማለቱ ምክንያት ጦርነቱ ቁሞ የራያ ምሊሻ ወደ ኋላ ቢልም TDF መልሶ ቦታውን ተቆጣጥሮታል ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ተኩሱ የተጀመረበትን ልዩ ቦታ በተመለተ በሰጡት ምላሽም ፣ “ የተጀመረበት ቦታው ‘ጮጓራ’ ይባላል። የራያ አላማጣ ቦታ ነው። አሁንም እሱን በማለፍ ወደ ‘ኮስም’ የሚባል አከባቢ እየተጠጉ ነው። ተጨማሪ ኃይልም እያስጠጉ ይገኛሉ ” ብለዋል።

የአካባቢው አመራር የተኩሱን መነሻ በገለጹበት አውድ ፣ “ የዚህ ዋናው መንስኤ አማራ ክልል #ወልቃይት እና #ራያ በስርዓተ ትምህርቱ ካርታ ላይ ተካተዋል በሚል በወጣው መግለጫ ነው ” ሲሉ አስረድተዋል።

“ የራያ ህዝብ የዘመናት ትግሉ በህጋዊ መንገድ ፍትህ ማግኘት እንጂ ጦርነት አይፈልግም። እነሱ እየተከተሉ ደጋግመው እያቆሰሉት ነው ” ሲሉም አክለዋል።

በህወሓት ተከፈተ ስለተባለው ተኩስ በትግራይ ክልል በኩል እስካሁን በይፋ የተባለ ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በትግራይ ያሉ አስታዳዳሪዎችን አግኝቶ የነበረ ሲሆን ስብሰባ ላይ እንደሆኑና ወደ በኃላ ማብራሪያ እንደሚሰጡን ገልጸዋል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ፣ “ የአማራ ክልል የትግራይ መሬት በካርታው በማስፈር የትምህርቱ ሰርዓቱ አካል በማድረግ እያስተማረበት ይገኛል " ማለቱ አይዘነጋም።

አስተዳደሩ ፤ በአማራ ክልል መንግሥት በኩል በትግራይ ህዝብ ላይ ግፍ እና በደል ሲፈፀም እንደቆየ አሁንም እንደቀጠለ ገልጾ ክልሉ የሰላም ስምምነቱን የሚያናጋ ጠብ አጫሪ ተግባራትን እየፈፀመ እንደሆነ ከሶ ነበር።

የፌደራል መንግስት በካርታው ላይ ምንም አይነት እርማት እንዳልሰጠ ፣ የአማራ ሕዝብም ሆነ ሌለው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ጎን እንዲቆሙ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከተለው ነገር ሁሉ ግን የአማራ ክልል ሙሉውን ኃላፊነት ይወስዳል " ሲል አስጠንቅቆ ነበር።

መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia