TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ🔝

በባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ #በድጋሜ የእሳት ቃጠሎ ተከሰተ። ባለፋት ሳምንታት ለተከታታይ ስድስት ቀናት እንዲሁ በጥበቃ ቦታው ላይ የዚህ አይነት የእሳት ቃጠሎ በመነሳት ስፋት ያለው በአስታ ደን የተሸፈነ የፓርኩ አካል መውደሙ የሚታወቅ ነው።

በሌሎቹ የጥበቃ ቦታዎቻችንም ቢሆን እንዲሁ የዚህ አይነት ቃጠሎ በሰው ሰራሽ ችግር ምክኒያት በተደጋጋሚ የሚከሰት ሲሆን በመከላከያ ሠራዊት፣ በፌደራል ፓሊስ፣ በፈቃደኛ ወጣቶችና በአካባቢው ነዋሪ ህብረተሰብ እርብርብ እየተደረገ የተነሳውን እሳት መቆጣጠሩ የተለመደ ነው።

የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ በአገራችን ከሚገኙት ከፍተኛ ተራሮች መካከል የቱሉ ዲምቱ እና የሰናቴ ፕላቶዎች የሚገኙበት በመሆኑ አብዛኛው የመሬቱ አካል በአስታ ዛፎች የተሸፈነ ነው። በተጨማሪም የዚህ እጽዋት ዝርያዎች በቀላሉና በፍጥነት በእሳት የሚቀጣጠል ከመሆኑም በተጨማሪ ወደ ስሩ አካባቢ ያለው ግንድ እሳቱን ይዞ ስለሚቆይ የጠፋ ይመስልና ንፋስ ሲያገኝ እንደገና ይቀጣጠላል። ይህ ባህሪው አካባቢውን ከእሳት ለመታደግ አስቸጋሪ ያደርገዋል።

አሁን ላይ በባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ ቀናትን ያስቆጠረ ሲሆን እንደተለመደው እሳቱን ለመቆጣጠር የፀጥታ ሃይሉና ህብረተሰቡ ወደ ቦታው በመሄድ እሳቱን እያጠፋ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በተጨማሪም የቃጠሎውን መንስሄ ለማወቅ በሚደረገው ጥረት የአካባቢው ፓሊስ #የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በህግ #ቁጥጥር_ስር አውሎ ምርመራ እያከናወነ መሆኑን የፓርኩ ሃላፊ አቶ አስቻለው ገልፀውልናል።

Via ኢ.ዱ.ል.ጥ.ባ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች
ፎቶ፦ TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#fanaTv ቀን በነበረው የቀጥታ ስርጭት በፋና ቴሌቪዥን መከታተል ያልቻላችሁ #በድጋሜ ከጥቂት ደቂቃ በኃላ ይተላለፋል መከታተል ትችላላችሁ! እንኳን አደረሰን በድጋሚ!!

#ሁለተኛው_ዓመት የTIKVAH-ETH ምስረታ በዓል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ። የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። በሁለት ዙር ለተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና የተሰጠው የማለፊያ ነጥብ የተለያየ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች…
" በትምህርት ሚኒስቴር የተቆረጠው ማለፊያ ነጥብ የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ እና ችግር ታሳቢ ያላደረገ ነው " - አቶ አለሙ ደባሽ

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በጋዝጊብላ ወረዳ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 229 ተማሪዎች 30 ተማሪዎች ወይም 13 በመቶ ብቻ ማለፋቸውን የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት አስታውቋል።

በወረዳው ቤላ አምባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለፈተናው ከተቀመጡ 44 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሁለት ተማሪዎች ብቻ ያለፉ ሲሆን ፈተናውን ከወሰዱ 139 የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች 28 ተማሪዎች ብቻ አልፈዋል።

በተመሳሳይ በወረዳው በመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለፈተናው ከተቀመጡ 10 የተፈጥሮ ሳይንስ እና 36 የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ምንም ተማሪ ማለፍ አለመቻላቸውን የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አለሙ ደባሽ ገልጸዋል።

አካባቢው ከአንድ ዓመት በላይ በጦርነት ቀጠና ውስጥ መቆየቱ እና ፈተናው በሚሰጥበት ወቅት ተማሪዎቹ ሙሉ ጊዜያቸውን እና ህይወታቸውን ለጦርነት አሳልፈው በመስጠት ላይ የነበሩ በመሆኑ ለፈተናው ያለበቂ ዝግጅት መቀመጣቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ የነበሩበት ሁኔታ እየታወቀ በትምህርት ሚኒስትር ውሳኔ ካሉበት እና ተፈናቅለው ከተሰደዱበት እንዲመጡ በማድረግ ያለምንም ዝግጅት ለፈተና መቀመጣቸውን ኃላፊው ተናግረዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የተቆረጠው ማለፊያ ነጥብ የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ እና ችግር ታሳቢ ያላደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመሆኑም ሚኒስቴር ለአካባቢው የተወሰነውን የከፍተኛ ትምህርት ማለፊያ ነጥብ #በድጋሜ_በማጤን ማስተካከያ እንዲያደርግ ሲሉ ጠይቀዋል።

More : @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#ለጥንቃቄ " በፎሬክስ ትሬዲንግ የኦንላይን ስራ ትርፋማ እናደርጋችኋለን " የሚል የፌስቡክና የቴሌግራም ማስታወቂያ በሚያስነግሩ የተደራጁ ቡድኖች መጭበርበራቸውን ተበዳዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።  እነዚህ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገጾች ስያሜአቸው ከፎሬክስ ትሬዲንግ ጋር የተያያዘ ሲሆን " ትሬድ እናደርጋለን ትርፋማ ትሆናላችሁ " የሚል ቃል በመግባት ከሰዎች ገንዘብ እያስላኩ የማጭበርበር ስራ…
#በድጋሜ⚠️

ውድ ቤተሰቦቻችን ጥንቃቄ አድርጉ።

በሀገራችን ያለውን ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ጫናን ለመቋቋምና ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ብዙ ሳይደክሙ በርካታ ገንዘብ ለማግኘት በሚደረግ ጥረት በርካታ የሀገራችን ልጆች ደክመው በላባቸው ያገኙትን ፤ ከቤተሰብም ለስራ በሚል የተቀበሉትን ብር በኦንላይን አጭበርባሪ ዘራፊዎች በየዕለቱ እየተበሉ ይገኛል።

ከዚህ ቀደም መላው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በኦንላይን ከሚደረጉ የማጭበርበር ስራዎች እራሳችሁን እንድትጠብቁ የአደራ ማሳሰቢያ መላክችን ይታወሳል።

አሁንም ሰዎች በመቶ ሺህ የሚቆጠር ብራቸውን እየተበሉ ይገኛል።

እባካችሁን በ " ዋትአፕም " ይሁን በ " ቴሌግራም " አድራሻችሁን አግኝተው የሚያናግሯችሁን የማታውቋቸውን ሰዎች መልዕክት አትመልሱ።

" በተለያየ ኦንላይን ስራ ፣ በፎሬክስ ትሬዲንግ እና በሌሎችም በትንሽ እና በማያደክም ስራ ትርፋማ እናደርጋችኋለን ፤ ይሄን ይሄን ስራ ስሩ በዚህ አካውንት ገንዘብ አስገቡና እኛም መልሰን ትርፉን እናስገባለን " የሚሉ አጭበርባሪዎች ተንሰራፍተዋልና ተጠንቀቁ።

በነገው ዕለት ከዚህ ጋር በተያያዘ ስላጋጠመ ክስተት እናጋራችኃል። ለአሁኑ ግን ምናልባት " ይሄን ስራ ስሩና ትርፋማ ትሆናላችሁ ፤ ገንዘብ ላኩና ትርፉን እንልካለን " በሚል እያባበሉ ገንዘብ እድትልኩ የሚጠይቋችሁን ሰዎች ከማናገር ተቆጠቡ፤ ምንም ገንዘብም አትላኩላቸው።

@tikvahethiopia