TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ኤርዶጋን ምን አሉ ? የቱርክ ፕሬዝዳንት ሪሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት ዙሪያ ይህን ብለዋል ፦ - በሲቪሎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ወይም በሲቪል አካባቢዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ትክክል አይደለም፤ አንቀበለውም። - በእስራኤል ግዛት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ግድያ እንቃወማለን። - በጋዛ ውስጥ ንጹሃን  ያለየ ' #ጭፍጨፋ ' በፍጹም አንቀበልም። - አሳፋሪ ዘዴዎችን…
#እስራኤል #ፍልስጤም

ዛሬ አንድ ሳምንቱን የያዘውና ባለፉት ዓመታት ውስጥ ታይቶ አይታወቅም የተባለው እጅግ ደም አፋሳሹ የእስራኤል እና የፍልስጤሙ ሃማስ ጦርነት ቀጥሏል።

አጫጭር መረጃዎች ፦

- እስራኤል እየወሰደችው ባለው ጥቃት የሞቱ ፍልስጤናውያን ቁጥር 1,900 ደርሰዋል። ከሞቱት ውስጥ እጅግ በርከታ ህፃናት ይገኙበታል ተብሏል። 7,696 ሰዎች ደግሞ ተጎድተዋል።

- ሃማስ በሚፈፅመው ጥቃት በእስራኤል በኩል የሞቱ ሰዎች 1400 የደረሱ ሲሆን 3,418 ሰዎች ተጎድተዋል።

- በዌስት ባንክ ውስጥ 52 ሰዎች ሲገደሉ፣ 700 ተጎድተዋል።

- እስራኤል " ሃማስን እስከወዲያኛው አጠፋዋለሁ ፤ ላደረገው ድርጊትም ዋጋውን አስከፍለዋለው " እያለች ሲሆን አሁን ላይ እየወሰደች ያለው እርምጃ ገና መጀማሪያው እንዳሆነ ገልጻለች።

- እስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ ያሉ ሁሉም ሲቪሎች በሰዓታት ውስጥ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አስጠንቅቃለች። በሰሜናዊ ጋዛ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚገኙ ሲሆን ሀገራት እና ተቋማት እስራኤል ውሳኔዋን እንድታጥፍ እየጠየቁ ናቸው። እንደ ተመድ መረጃ በአስር ሺዎች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል።

- በጋዛ ላይ የነዳጅ፣ የምግብ፣ የውሃ እገዳው አሁንም እንደቀጠለ ነው።

- ሐማስ እስራኤል ላይ አሁንም የሮኬቶች ጥቃት መፈፀሙን ቀጥሏል።

- የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ የፍልስጤሙን " ሃማስ " በመደገፍ እንደሚሰለፍ አስታውቋል። ቡድኑ ጊዜው ሲደርስ ጦርነቱን ከሃማስ ጎን ሆኖ ለመሳተፍ ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ እንደሆነ ገልጿል። ባለፉት ቀናት በሊባኖስ በኩል አንዳንድ የግጭት ምልክቶች የታዩ ሲሆን እስራኤል ድንበሯን ጥሰው ሊገቡ ነበሩ ያለቻቸውን ሰዎች በድሮን መታ መግደሏ ተነግሯል።

- ሐማስ አግቶ ከወሰዳቸው ሰዎች ውስጥ 13 እስራኤላውያንን እና የውጭ አገራት ዜጎች እስራኤል በጋዛ እያደረገችው ባለችው የአየር ጥቃቶች መገደላቸው አሳውቋል።

- የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ወደ ጦርነቱ ቀጠና ሄደው ከእስራኤል ጠ/ሚ እስራኤል ውስጥ፣ ከፍልስጤሙ ፕሬዜዳንት ሞሀሙድ አባስ ጋር ዮርዳኖስ ውስጥ ተገናኝተው መከረዋል። በኃላም ወደ  አጋርናታችንን እናሳያለን ብለው ትላንት እስራኤልን ጎብኝተው ነበር። በኃላም ወደ ሳዑዲ አረቢያ አቅንተው ከሀገሪቱ አመራሮች ጋር ስለጦርነቱ መክረዋል።

- ጦርነቱ እንዲቆም እና መሄጃ ለጠፋባቸው ፍልስጤማውያን ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ በተለያዩ ወገኖች ጥሪዎች እየቀረቡ ይገኛሉ።

More  @BirlikEthiopia

https://t.iss.one/+LM-bJ8NzZMcxMjA8
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ፍልስጤም #እስራኤል

በጋዛ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ በተፈፀመ ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገደሉ።

ሃማስ ጥቃቱን እስራኤል ነው የፈፀመችው ብሏል።

የእስራኤል መከላከያ ደግሞ " ኢስላሚክ ጂሃድ " የተባለው ቡድን እስራኤል ላይ ያስወነጨፈው ሮኬት ዒላማው ሳይሳካ ቀርቶ የተፈጠረ ነው ብሏል።

ትላንት ጋዛ ውስጥ በሚገኘው "አልአህሊ ባፕቲስት ሆስፒታል " ላይ በደረሰ የአየር ጥቃት በትንሹ 500 ሰዎች መገደላቸውን በጋዛ  የሚገኘው ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሃማስ ጥቃቱን እስራኤል ነው የፈፀመችው ብሏል። ጥቃቱን " የጦር ወንጀል ነው" ሲል ገልጾ " ሆስፒታሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ የታመሙ እና የቆሰሉ ሰዎች ነበሩበት ብሏል።

የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ፤ በጋዛ የሚገኘው ሆስፒታል የተመታው ባያልተሳካ የ " እስላሚክ ጂሃድ " ቡድን ሮኬት ነው ብሏል።

ያልተሳካ ሮኬት ያስወነጨፈው ይኸው ቡድን ለሆስፒታሉ መመታት ተጠያቂ ነው ሲል ገልጿል።

" እኛ ሆስፒታሉ ላይ ጥቃት አልፈፀምንም " ብሏል።

የ " ፍልስጤም እስላሚክ ጂሃድ " ድርጅት የእስራኤል ክስ ሀሰተኛ እና ምንም መሰረት የሌለው የተለመደ ቅጥፈት ነው ብሏል። እስራኤል ከተለመደው ጭፍጨፋ ተጠያቂነት ለማምለጥ በፍልስጤማውያን እና ' ኢስላሚክ ጂሃድ ' ላይ ጣቷን ለመጠቆም የፈጠረችው ሀሰተኛ ፈጠራ ነው ሲል ገልጿል።

" ፍልስጤም እስላሚክ ጂሃድ " እኤአ 1981 የተመሰረተ ሲሆን በጋዛ እና ዌስት ባንክ ውስጥ ይንቀሳቀሳል።

በሌላ በኩል ፤ የፍልስጤም ፕሬዜዳንት ማሃሙድ አባስ በሆስፒታሉ ላይ በተፈፀመው ጥቃት እና በጠፋው የሰው ህይወት ምክንያት የ3 ቀን ሀዘን አውጀዋል።

በሆስፒታል ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ሀገራት እና ተቋማት እያወገዙ ይገኛሉ። በተለያዩ ከተሞችም እስራኤልን የሚያወግዙ ሰልፎች እየተደረጉ ይገኛሉ።

ዓለም ለጋዛ ሆስፒታል ለደረሰው ጥቃት ምን ምላሽ ሰጠ ?

እስራኤል የአየር ጥቃቱን ፈፅማለች ብለው የከሰሱና ያወገዙ ፤ በጉዳቱ ሀዘናቸውን የገለፁ ፦

🇪🇬 የግብፅ ፕሬዝዳንት
🇯🇴 የዮርዳኖስ ንጉስ
🇸🇾 የሶሪያ ፕሬዝዳንት
🇨🇺 የኩባ ፕሬዝዳንት
🇮🇶 የኢራቅ መንግስት
🇸🇦 የሳዑዲ አረቢያ መንግስት
🇹🇷የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
🇻🇪 የቬንዙዌላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
🌍 የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሃላፊ
🇮🇷 የኢራን ፕሬዝዳንት (እስራኤል ብቻ ሳትሆን አሜሪካም ጭምር ከእስራኤል ጋር ሀላፊነት ትወስዳለች ብለዋል)

ጥቃቱን ያወገዙ ነገር ግን ማንንም ያልወቀሱ ፤ ይልቁንም ምርመራ እንዲደረግ የጠየቁ ፦

🇪🇺 የአውሮጳ ዲፕሎማሲ ኃላፊ
🇫🇷 የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት
🇳🇱 የኔዘርላንድስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
🇪🇸 የስፔን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
🇬🇧 የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት
🇯🇵 የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
🇺🇸 አሜሪካ ማንም ሳትከስ ነገር ግን ስለ ተፈጠረው ሁኔታ ተጨማሪ መረጃዎችን ሰበስባለሁ ብላለች።

" ማስረጃ አቅርቢ " - ሩስያ

🇷🇺 የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስራኤል በጥቃቱ ላይ የለሁበትም ካለች የሳተላይ ምስሎችን በማስረጃነት ታቅርብ ብሏል።

እኤአ ጥቅምት 7 ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ ባደረሰችው ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ከ3,200 በልጠዋል።

በእስራኤል ውስጥ በሃማስ ጥቃት የተገደሉ ከ1,400 በላይ ሰዎች ሆነዋል።

More 👉 @Birlikethiopia