TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈#የጤናባለሙያዎችድምፅ

" ከ15 ወራት በላይ የዱቲ ገንዘብ አልተከፈለንም በዚህ ኑሮ ውድነት በብድር በዬ ወሩ ተሰቃየን " - ጤና ባለሙያዎች

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፣ በጌዴኦ ዞን በዲላ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች የ15 ቀናት የዘመቻ አበልና ከአንድ አመት በላይ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመፈጸሙ ችግር ላይ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የጤና ባለሙያዎቹ ዝርዝር ቅሬታ ምንድን ነው ?

" እኛ ጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ የምንገኝ ጤና ባለሙያዎች በጣም ተቸግረናል። በሰራነውና በለፋነው ልክ ክፍያ እየተከፈለን አይደለም።

አሁን ላይ ትልቁ ችግራችን ቢግ ካቻፕ ተብሎ በመጣ ዘመቻ ላይ ከ15 ቀናት በላይ ስራ ላይ ያሳለፍን ሲሆን፣ ለጤና ባለሙያ የክፍያ ገንዘቡ መጥቷል።

ክትባቱ ከ5 ዓመት በታች ላሉ ሕፃናት የሚሰጡ Rota፣ Ipv፣ Mcv፣ Vitamin A፣ Vermox፣ BCG፣ Opv የመሳሰሉት የክትባት አይነት ነው።

በዘመቻ ሰዓት ODK ተብሎ በሁሉም ቤት እየገባን ልክ እንደ ቤት ቆጠራ ከኪሳችን እያዋጣን የሞላነው ገንዘብ ጭምር አልተከፈለንም።

የቢግ ካቻፕ የክትባት ዘመቻ በሁሉም በጌዴኦ ዞን ባሉት ወረዳ ላይ ገንዘቡ ቢሰጥም ሁሉንም ወረዳ ያማከለ አይደለም።

ለምሳሌ ይ/ጨፌ፣ ወናጎ፣ ራጴ፣ ገደብ ላይ ከ6,500 ብር በላይ ተሰጥቷል። ዲላ ዙሪያ ወረዳ ግን 1, 800 ብር ለመስጠት፣ ለማስፈረም ሲሉ ጤና ባለሙያ እያቀረበ ያለውን ቅሬታ ሰሚ አካል ለማግኘት አልቻለም።

በሌላ በኩል ከ15 ወራት በላይ የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም በዚህ ኑሮ ውድነት በብድር በዬ ወሩ ተሰቃዬን" የሚል ነው ቅሬታቸው።

ለተነሳው ለዚህ ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡ ወደ ጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ብንሞክርም ስልክ ለማንሳትም ሆነ መልዕክት ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆነም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM