TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Earthquake : እየተከሰተ ያለው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬም ቀጥሏል። ዛሬ ረቡዕ ከጥዋት አንስቶ እስከ ምሽት በተለያየ ጊዜ በሬክተር ስኬል ከ4.5 እስከ 4.9 ድረስ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ ፈንታሌና አካባቢው ተከስቷል። ሰሞኑን ጠንከር ያለውና ተደጋግሞም እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አፋር ላይ የንብረት ጉዳት አድርሷል። ወገኖቻችን የመሬት መንቀጥቀጡ ካየለባቸው ቦታዎች…
#Earthquake

ዛሬ በሬክተር ስኬል 5.1 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ገልጿል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከአዋሽ በሰሜን 36 ኪ/ሜ በኩል ነው የተመዝገበው።

የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት አዲስ አበባ እና ቦታዎችም የተሰማ ሲሆን በተለይ በአዲስ አበባ ንዝረቱ በደንብ ይሰማ ነበር።

አንድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ፥ " የመሬት ንዝረት እየተሰማ ነው ፤ ያለሁት ቦሌ አካባቢ መኪና ውስጥ ነው ፤ በደቂቃዎች ልዩነት ሁለቴ አጋጥሟል " ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ሌላ አንድ የቤተሰባችን አባል  " መኪናዬ ውስጥ ሆኜ ትንሽ ንቅንቅ ስል ተሰምቶኛል ወደ አያት አካባቢ ቆሜ ባለሁበት " ሲል ገልጿል።

ከሰሞኑን የተለያየ መጠን ያላቸው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች እየተመዘገቡ ሲሆን የዛሬው 5.1 ከፍ ካሉት አንዱ ነው።

በሬክተር ስኬል 5.1 ከተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ በኃላ በሬክተር ስኬል 4.5 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥም ነበር።

አፋር ላይ በተለይ የመሬት መንቀጥቀጡ አይሎ በሚሰማባቸው ቦታዎች ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በርካቶችም ከቤታቸው ሸሽተው ሄደዋል።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
😭1.13K🙏237172🕊80🤔58😢44😱36🥰34👏32😡12
TIKVAH-ETHIOPIA
" ዱአ ያስፈልጋል !! " " አፋር ክልል ገቢ ረሱ ዞን ሀን ሩካ ወረዳ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ህዝቡን ከመኖሪያ ቤቱ አውጥቶ ሜዳ ላይ እያሰደረው ነው። በተለያየ ግዜ በጎርፍ አደጋ ሲጠቃ የኖረው የአፋር ህዝብ ዛሬም አላህ ይድረስለት። ሁሉም ሰው ቤት ውስጥ መተኛት አቁሞ ውጭ በረንዳ ላይ ወጥቶ እየተኛ ነው። ዱአ ያስፍልጋል !! " - መሀመድ ኢሴ @tikvahethiopia
" የአሁኑ ከእስከዛሬው ሁሉ ይለያል ፤ በጣም ያስፈራ ነበር " - ነዋሪዎች

በርካቶችን ለሊት ከእንቅልፍ የቀሰቀሰ ጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ ትላንት ለሊት ተከስቷል።

ከለሊቱ 9:52 ላይ ከአቦምሳ 56 ኪሎ ሜትር ርቀት በሬክተር ስኬል 5.8 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

ንዝረቱ አዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች በከፍተኛ ሁኔታ ተሰምቷል።

የቤተሰብ አባላቶቻችን ምን አሉ ?

➡️ " ሩፋኤል አካባቢ ነው ያለሁት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የሰማሁት ያስፈራል እስካሁን አዲስ አበባ ላይ ሲባል ነው ስስማ የነበረው። "

➡️ " በጣም በሚያስፈራ ሁኔታ ከእንቅልፍ ነው የቀሰቀሰኝ። እንዲህ ከፍ ብሎ ተሰምቶኝ አያውቅም። "

➡️ " ሰሚት ነው የምኖረው ፤ እግዚኦ የአሁኑ 9:52 የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት እና የቆየበት ሰከንድ ያስፈራ ነበር። "

➡️  " የአሁኑ በጣም ከበድ ያለ እና ረዘም ያለ ነው ከአያት ኮንዶሚኒየም። "

➡️ " ከአራብሳ ኮንዶሚኒየም ነበር። የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ በጣም ከፍ ያለ ነው። "

➡️ " ከእስካሁኑ ጠንካራውን ንዝረት ነው የሰማነው። ከቦሌ አራብሳ ኮንዶሚኒየም። እቃዎች ሲወድቁም አስተውያለሁ። "

➡️ " በከባዱ ነበር የዛሬው ደግሞ ከሌሎቹ የተለየ ነበር። "

➡️ " እኔ ባለሁበት ቀጨኔ ከወትሮው ርዝማኔው የጨመረ የመሬት መንቀጥቀጥ ጠንከር ያለ ንዝረት ተከስቷል። "

➡️ " ዱከም ነው ያለነው ንዝረቱም ጠንክሮ እዚህም ተሰምቷል። "

➡️ " ኧረ ያአሏህ ጎሮ ሰፈራ ላይ ነኝ ያለሁት እና የመሬቱ መንቀጥቀጥ ንዝረት ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ ወይስ በህልሜ ይሁን ያረቢ ብቻ ከባድ ነው በጣም ነው የሚያስጠነግጠው። "

➡️ " በከሚሴ  የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ተሰምቶናል። በጣም ያስፈራ ነበር  አሏህ መጨረሻችንን ያሳምርልን ! '

➡️ " ከለሊቱ 9:53 ላይ ለ5 ሰከንድ የቆየ ከፍ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ነበር። የካ ክፍለ ከተማ ነው። ድምጹም ከመኝተየ የቀሰቀሰኝ የቤታችን ቁም ሰጥን ሲንቀጠቀጥ ሰምቸ ነው። መሬቱም በጣም ነበር ከተኜውበት የቀሰቀሰኝ። ያስፈራ ነበር። "


በሬክተር ስኬል 5.8 ከተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ በኃላ ዳግም በሬክተር ስኬል 4.4 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥም ተከስቶ ነበር።

ውድ ቤተሰቦቻችን " ነገሩ ተለምዷል ፤ ምንም ሊፈጠር አይችልም " ብላችሁ እንዳትዘናጉ በድጋሚ አደራ እንላለን።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
😭1.53K🙏421234😢67🕊58😱37👏30🤔23🥰22😡8
TIKVAH-ETHIOPIA
የመሬት መንቀጥቀጡ እየተከሰተ ባለበት አፋር ክልል አዋሽና አካባቢው ህዝቡ ለበርካታ ሳምንታት ቀን እና ለሊት ከአሁን አሁን ምን ሊፈጠር ነው እያለ በሰቀቀን እያሳለፈ ነው የሚገኘው። ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፣ ሰዎች ቤታቸውን ጥለው ሄደዋል። በርካቶች ቤት ውስጥ ማደር አቁመው ውጭ በረንዳ ላይ ለማደር ተገደዋል። ከየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ በላይ ፤ የአፋር ነዋሪዎች ተደጋጋሚና ሊቆም ያልቻለው የመሬት…
🚨#ጥንቃቄ

ውድ ቤተሰቦቻችን ሆይ ፤ የመሬት መንቀጥቀጥ ድንገተኛ ፣ ቅፅበታዊ መቼ እንደሚፈጠር መቼስ እንደሚቆም የማይታወቅ ክስተት ነው።

መሬት መንቀጥቀጥ ክስተትን መተንበይ የሚባል ነገር የለም ፤ የት አካባቢ እንደሆነ እንጂ መቼ ይከሰታል የሚባለውን ተመራማሪዎች መተንበይ አይችሉም።

ስለዚህ በየትኛውም ሰዓት፣ ጊዜ ሊከሰት ይችላል ፤ ሊመጣ ይችላል ብሎ ማሰብ የግድ ይላል።

" አሁንማ እኮ ተለመደ " ተብሎ መዘናጋት አይገባም።

" ፈጣሪ ክፉን ሁሉ ያርቅልን " እያልን መማፀኑ እንዳለ ሆኖ በዚህ ወቅት ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች በአግባቡ ማወቅ ያስፈልጋል።

የሰሞነኛው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት እንዳለ ሆኖ የትላንት ለሊቱ ከፍተኛ የሆነ የማንቂያ ደውል ነው።

ብዙዎች ተኝተው ከነበሩበት ቀስቅሷል ፣ ፎቅ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ወዲያና ወዲህ ብለዋል፣ እቃዎች ከላይ ወደ ታች ወድቀዋል።

ሰዓቱ ለሊት የመኝታ ሰዓት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አንዳንዶች ያልሰሙት ይሆናል እንጂ ጥንካሬው ከእስከዛሬው ሁሉ የተለየ ፤ " ሰምተን እናውቅም " ያሉ ሰዎች ሁሉ የሰሙት ሆኗል።

አዲስ አበባ ብዙ ህንጻዎች ያሉባት በመሆኑ ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል።

በመሆኑም ውድ ቤተሰቦቻችን ፍጹም አትዘናጉ ! ፈጣሪያችንን ከክፉ ሁሉ ነገር እንዲጠብቀን እየተማፀንና ሳንደናገጥ ንቁ ሁነን የጥንቃቄ እርምጃዎችን ለመተግበር በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ መሆን ይገባናል።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
489🙏254😭70🕊32🥰16👏9😢4😱2
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የልደት በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

" ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል። " (ሉቃ. 2÷11)

መልካም የልደት በዓል !
Ayyaana Qillee Gaarii!
ርሑስ በዓል ልደት!

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
987🙏159😡36🕊34🥰18😭9🤔6😢6😱1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya ትላንት ምሽት በኢትዮጵያ ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ክፍሎች በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ብርሃን ያላቸው የቁስ አካላት ስብስብ በኬንያ ሰሜናዊ ምስራቅ ክፍልም ታይተዋል። እነዚህ ቁስ አካላት በኬንያ ቱርካና፣ ማርሳቢት፣ ሞያሌ አካባቢ መታየታቸውን የኬንያ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ገልጸዋል። ምንም እንኳን ቁስ አካላቱ " የጠፈር ፍርስራሾች ናቸው በገጠሪቱ…
" የቁስ አካላቱ ሞያሌ ላይ አልወደቁም " - ነዋሪዎች

በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቁስ አካላት ስብስብ  ነገር ሞያሌ ላይ አለመዉደቁን ነዋሪዎች ገለጹ።

ትላንት ምሽት በደቡባዊ የሀገራችን ክፍሎች ሰማይ ላይ ከተለመዱት ተወርዋሪ ኮከቦች በተለየ መልኩ በመጠን የገዘፈና በዘገምተኛ አኳሃን ሲጓዝ እንደነበር የተገለጸው ብርሃናማ የተቀጣጠሉ ቁስ አካላት " ሞያሌ አከባቢ ወድቋል " እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ ምንጫቸው ያልተረጋገጠ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር።

ዛሬ ማለዳ ጀምሮ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሞያሌ ኢትዮጵያ እና ጋምቦ አካባቢዎች ባደረገው ማጣራት ብርሃናማዉ አካል በተመሳሳይ መልኩ በሞያሌ ሰማይ ላይ ወደ ሶማሊያና ምስራቃዊ ኬንያ አቅጣጫ ማለፉንና በአከባቢው አለመዉደቁን ለማወቅ ችሏል።

በሞያሌ ጋምቦ የሚገኘው የመረጃ ምንጫችን ስለጉዳዩ በሰጠው ቃል " በሰሞኑ የመሬት መንቀጥቀጥ አፋር አከባቢ መደጋገሙን ስንሰማ ስለነበር በዚህም ክስተት ሰዉ ሁሉ ደንግጦ ነበር፤ ነገሩ በሞያሌ ሰማይ ላይ ሲያልፍ አይቻለሁ " ብሏል።

አክሎ " ሪችት ይመስላል-ሞያሌ ወደቀ የሚል ነገር ሰምቼ እስከ ማርሳቤትና ናይሮቢ ድረስ ደዋዉዬ አጣራሁ ያሉኝ ነገሩ ናይሮቢ አልደረሰም፤ ነገር ግን የማርሳቤት ሰዎች ሰማይ ላይ አይተነዉ ኡጂሩ በተባለች የኬንያ ድንበር አድርጎ ወደ ሶማሊያ መሄዱን ነግረዉኛል " ሲል ገልጿል።

አንዳንድ ጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የስነ ከዋክብትና ስፔስ ሳይንስ አጥኝዎች ይኸው ተቀጣጣይ ነገር " የጠፈር ፍስራሾሽ " ሊሆኑ ይችላሉ ብለዋል።

በኢትዮጵያም ይሁን በኬንያ ተቋማት በኩል ቁርጥ ያለ ነገር ባይነገርም በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በኩል ጉዳይን በዝርዝር ለማሳወቅና ለማብራራት ስራዎች እየተሰሩ ነው።

ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት ማገባደጃ በኬኒያ ሙኩኩ በተባለ ገጠራማ መንደር 500 ኪ.ግ የሚመዝን ቀለበታማ የጋለ ብረት  መውደቁ የተነገረ  ሲሆን የሀገሪቱ ስፔስ ኤጀንሲ ብረቱ በስፔስ ላይ ከሚገኙ ሮኬቶች ተገንጥሎ የወደቀ ሊሆን እንደሚችል ማስታወቁ አይዘነጋም።

#TikvahEthiopiaFamily #Moyalle #Gambo

@tikvahethiopia
🙏15672😭40🤔34🕊15😢12🥰9😱2😡2
#ጥምቀት

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ ! በዓሉ በደስትና በረከት የተሞላ እንዲሆን ከልብ እንመኛለን።

መልካም የጥምቀት በዓል !

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
862🙏124🕊27🥰24😢18😡15🤔5😭4
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ፈጣሪ ይጠብቀን እንጂ የዛሬውስ እጅግ ያስፈራ ነበር " - ነዋሪዎች

ለሊት ከ8:46-8:48 ባለው ጊዜ ከወትሮ የተለየ በርካታ ሰዎችን ከተኙበት ጥንልቅ እንቅልፍ ሁሉ ሳይቀር የቀሰቀሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

እስካሁን ባለው መጠኑን  የዓለም አቀፍ ተቋማት ከ5.0 - 5.3 በሬክተር ስኬል መዝግበውታል።

የጀርመን ጂኦ ሳይንስ ጥናትና ምርምር ማዕከል መንቀጥቀጡ ከጭሮ ሰሜን ምዕራብ 60 ኪሎሜትር ላይ የተከሰተ ነው ብሏል።

የአሜሪካው ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ደግሞ ቦታውን በተመሳሳይ ገልጾ መጠኑ በሬክተር ስኬል 5.3 ነው ሲል አመልክቷል።

በርካታ አፋርና አካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች መልዕክታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል።

" አላህ ይጠብቀን ምን አይነት አስፈሪ መንቀጥቀጥ እንደነበር በቦታው ያለ ሰው ብቻ ያውቀዋል " ሲል አንድ የቤተሰባችን አባል ክስተቱን ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ከሌሎች በርካታ ከተሞችም ከቤተሰቦቹ መልዕክቶችን እየተቀበለ ይገኛል።

ንዝረት ከነበረባቸው ከተሞች መካከል አዲስ አበባ እና አካባቢዋ ዋነኞቹ ናቸው።

የሽሮ ሜዳ፣ ጎሮ፣ ፊሊዶሮ፣ ፓስተር ፓውሎስ ሆስፒታል፣ አባዶ፣ አያት ፣ ጀሞ፣ ሰፈራ፣ ጋርመንት ፣ ፈንሳይ፣ ሰሚት ፣ ባልደራስ ፣ ገርጂ፣ ኮዬ ፈጬ፣ ላፍቶ፣ ሰሜን ማዘጋጃ ፣ ቱሉ ዲምቱ፣ ኮዬ ፈጬ ... ሌሎችም አብዛኛው የአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ሰፈሮች የሚኖሩ ነዋሪዎች ንዝረቱ ከፍ ብሎ ተሰምቷቸዋል።

አንድ የቤተሰባችን አባል 5ኛ ፎቅ ላይ እንደምትኖር ገልጻ " እጅግ ያስፈራ ነበር የዛሬው ከሁሉም ነው የተለየብኝ ህንፃው ተደረመሰ እያልኩ ነው ያለፈው " ብላለች።

ሌላኛው ፤ " ፈጣሪ ይጠብቀን እንጂ የዛሬው ያስፈራ ነበር። እኔ አልጋው እየተነቃነቀ መስሎኝም ነበር ከዚህ በፊት እንዲህ ተሰምቶኝ አያውቅም በድንገት መሆኑ ደሞ ሁላችንንም አስፈርቶ ነበር " ብሏል።

ሌላ አንድ የቤተሰባችን አባል ደሞ ፥ " እኔን ጨምሮ ሁሉም ቤት ውስጥ ያለነው ተነስተን ቁጭ ለማለት ተገደናል ፤ እንዲህ ተሰምቶን ስለማያውቅ ተደናግጠናል በተለይ የህንፃው ከፍተኛው ወለል ላይ ስሜቱ ያስታውቅ ነበር " ብሏል።

ምንም እንኳን የዓለም አቀፍ ተቋማት መጠኑን ከ5. 0 እስከ 5.3 በሬክተር ስኬል ቢመዘግቡትም ስሜቱ ግን ከወትሮ የተለየና ጠንካራ ነበር።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
😭1.07K🙏403259🕊101😱58😢45👏33🤔29😡25🥰23😁1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
መልካም የዐቢይ ጾም !

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለውድ ቤተሰቦቹና ለመላ ምዕመናን መልካም የዐቢይ ጾም እንዲሆን ይመኛል።

ጾሙ የፈጣሪን በረከት ፣ ዕርቅ ፣ ምህረት ፤ ለመላው ሀገራችን ፍጹም ሰላምና ዘላቂ መረጋጋትን የሚያመጣ እንዲሆን ከልብ ይመኛል።

ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የጾመ ኢያሱስ ሱባዔ (ዐቢይ ጾም) መልዕክት የተወሰደ ፦

" ከጌታችን ጾም የምንወስደው ብዙ ትምህርት አለ ፤ ከሁሉ በፊት ሰው በሕይወት መኖር የሚችለው በእንጀራ ብቻ ኣይደለም ብሎናል።

ይህ ኣባባል በሕይወት ለመኖር እንጀራ አያስፈልግም ማለት ኣይደለም፤ ሕይወትን ማኖር የሚቻለው በእንጀራ ብቻ እንደ ሆነ አድርገን እንዳናስብ ግን ቃሉ ያስተምራል ፤ ይህም በዓለማችን በየዕለቱ የምናውቀው ሓቅ ነው፤ ብዙ ሰዎች እንጀራን ሳያጡ በየዕለቱ ሕይወትን ያጣሉ፤ ምክንያቱም በሕይወት ለመኖር የእግዚአብሔር ቃልም እንጂ እንጀራ ብቻው በቂ አይደለምና ነው።

ዓለማት ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል ሁኑ ተብለው በቃሉ እንደተፈጠሩ፤ በቃሉም ጸንተው እንደሚኖሩ ኋላም በቃሉ እንደሚያልፉ ሁሉ የሰው ሕይወትም በዚህ ቃል ይወሰናል።

እንጀራ ኖረም አልኖረ ቃሉ በቃ ካለ ያበቃል ፤ ኑር ካለ ደግሞ እንጀራ ባይኖርም ይኖራል፤ ስለዚህ በሕይወታችን ወሳኝ ሥልጣን ያለው የእግዚአብሔር ቃል እንጂ፣ እንጀራ ብቻ ኣለመሆኑ ጌታችን በዚህ ኣስተምሮናል።

ጾመ ኢየሱስ እያልን በየዓመቱ የምንጾመው የታላቁ ጾማችን ዓላማ ዲያብሎስን ለማሸነፍ ነው፤ የዲያብሎስ ማሸነፊያ ስልት የመልካም ኅሊና ልዕልና ነው። "

መልካም የዐቢይ ጾም !

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
53.56K🙏740🕊97🥰84😡39👏32😭21🤔18😱18😢14
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የኢትዮጵያውያንድምጽ “ ወደ 29 ኢትዮጵያውያን ይበልጥ የከፋ ቦታ ተወስደዋል። ” - ኢትዮጵያዊያን በማይናማር ካሉበት ችግር እንዲያወጣቸው መንግስትን በተደጋጋሚ የተማጸኑ ፣ ማይናማር “ ታይሻንግ ካምፕ ” ታግተው የነበሩ 29 ኢትዮጵያውያን እስከዛሬ ሲደርስባቸው ከነበረው የከፋ ስቃይ ወዳለበት ስፍራ ተገደው መወሰዳቸውን ጓደኞቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። የተወሰዱት “ ዋልዋይ ” የተሰኘ ማይናማር…
🔈 #የኢትዮጵያውያንድምጽ

" እዚህ ያለነው ወደ 70 ኢትዮጵያውያን ነን ፤ ያለንበት ሁኔታ አስከፊ ነው ፤ ያናገረን አንድም አካል የለም " - ማይናማር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን

በማይናማር / ማይዋዲ KK2 የሚባለው ስፍራ የሚገኙ በቁጥር 70 የሚሆኑ ወጣቶች ከቦታው የሚያስወጣቸውን አጥተው ጭንቀት ላይ እንደሆኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ያሉበት ቦታ በማይናማር ወታደራዊ ሰዎች እየተጠበቀ እንዳለ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያውያኑ " እኛ በጣም አስከፊ ሁኔታ ላይ ነን። 70 እንሆናለን። ማንም መጥቶ የጠየቀን የለም። መቼ እንደምንወጣም አናውቅም። ሁሉ ነገር ጨልሞብናል " ብለዋል።

" የሚሰጠን ምግብ የማይበላ ነው። ማደሪያ የለንም እንጨት ላይ ነው የምንተኛው ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለን ለመናገር ይከብዳል ስቃይ ላይ ነን " ሲሉ ገልጸዋል።

" ባለፈው አንድ ወንድማችን በጣም ታሞ በስንት መከራ ነው ህይወት የዘራው " ሲሉ አክለዋል።

" ያሉትን የMilitary ሰዎች ጠይቀናቸው ነበር አብረውን ካሉት ውስጥ ' የህንድ መንግሥት ዜጎቹን ለመውሰድ accept ስላደረገ እነሱ ይወጣሉ በእናተ በኩል ምንም ምላሽ የለም ' ብለውናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ቢያንስ ትወጣላችሁ የሚለን የለ ወይ ስለኛ የሚናገር የለም እባካችሁ ስቃያችንን ስሙን " ሲሉ ተማፅነዋል።

" ህንዶቹ ነገ እና ከነገ ወዲያ ይወጣሉ ዛሬ እየተዘጋጁ ነው ከኛ ሀገር በኩል ያናገረን የለም በጣም ተጨንቀናል " ብለዋል።

እኚህ ወጣቶች ህይወትን ለማሸነፍ ሲሉ ታይላንድ ተብለው ወደ ማይናማር በግዳጅ የተወሰዱና በዛም በማፊያዎች ስንትና ስንት ስቃይ ያዩ ሲሆን ከዛ ስፍራው እንዲወጡ ከተደረጉ በኃላ አሁን ደሞ ሌላ ስቃይ እያዩ እንደሆነ አመልክተዋል።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭1.3K🙏118114😡62🕊31😢22🥰18😁18👏3😱3
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የጤናባለሙያዎችድምጽ 🔴 " በየጊዜው ቃል ከመግባት የዘለለ ምንም መፍትሄ የሰጠን አካል የለም !! " - የጤና ባለሙያዎች ➡️ " ከ8 ወራት በላይ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ስላልተከፈለን ለ2ኛ ጊዜ ስራ ለማቆም እየተገደድን ነዉ !! " በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሎካ-አባያ ወረዳ ሀንጣጤ ሆስፒታል የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች በበዓላት፣ በማታና የእረፍት ቀናት የሰሩበት ከ6 እስከ 9 ወራት የትርፍ ሰዓት…
#Update

" ተመላላሽ የሕክምና ቀጠሮ ቢኖረንም ሆስፒታሉ ዝግ ስለሆነ አገልግልት ማግኘት አልቻልንም " - ተገልጋዮች

➡️ " ከ6 እስከ 9 ወራት ታግሰን የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመከፈሉ ከአቅማችን በላይ ሆኖ ስራ አቁመናል" - የጤና ባለሙያዎች

🔴 " የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም ብለዉ መደበኛ ስራቸዉን በሚያቆሙ ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን " - የዞን አስተዳዳሪ

በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ በሀንጣጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ከ6 እስከ 8 ወራት የሰሩበት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመክፈሉ ስራ ለማቆም እንደሚገደዱ በመግለፅ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታቸዉን አሰምተዉ ነበር።

በወቅቱ የዞኑ አስተዳዳሪ ቅሬታዉ ተገቢ መሆኑን በመግለፅ " ከክልል ብድር ጠይቀናል በጥቂት ቀናት ስለሚፈፀም የ5 ወራት ክፍያ በአንድ ላይ በመፈፀምና ቀሪዉን በየወሩ እንዲከፈላቸዉ ይደረጋል " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዉ ነበር።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸዉን ዳግም ያደረሱት የሆስፒታሉ ጤና ባለሙያዎች " ከቅሬታዉ ምላሽ በኋላ ተጨማሪ አንድ ወር ታግሰን ለሙያ ቃል ኪዳናችንና ሕብረተሰቡን ማገልገል ስላለብን በችግሮች ዉስጥ አልፈን እየሰራን ብንቆይም አሁን ላይ ከአቅማችን በላይ በመሆኑ ስራ አቁመናል " ሲሉ ገልፀዋል።

" ከ6 እስከ 9 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ካለመፈፀሙም ባሻገር አመራሮች ነገሮች እንዲመቻቹላችሁ ' የብልፅግና ፓርቲ ሕንፃ ግንባታ መዋጮ የአንድ ወር ደመወዝ አዋጡ ' ብለዉን ሁሉም ባልተስማማበት ከመደበኛ ደመወዝ እየቆረጡ ነዉ ፤ በዚህም ለዘርፈ ብዙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀዉሶች ተዳርገናል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ዶክተር ሆነህ ' ቸገረኝ አበድረኝ ' ማለት ያሳቅቃል ይህ በሞራልም እየጎዳን ነዉ " ሲሉ ስሜታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያጋሩ ዶክተሮች ተናግረዋል።

እንዲሁ ሌላ የጤና ባለሙያ " ለህክምና የመጣች አንዲት ታካሚ ዱቤ ልትጠይቀኝ መስሎኝ ተደብቅያለሁ " ሲል እያሳለፉ ስላለው ህይወት ተናግረዋል።

ተገልጋዮች ምን አሉ ?

" በሀንጣጤ ሆስፒታል የሕክምና ክትትል ስለነበረን ግን ወደ ሆስፒታሉ  ቅዳሜ ጠዋት ስንሄድ ግቢዉ ዝግ ነበር፤ ጥበቃዉ የጤና ባለሙያዎች አለመግባታቸውን ነገረን " ሲሉ አንድ የሆስፒታሉ ተገልጋይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

እኚሁ ተገልጋይ አማራጭ አጥተዉ በስልክ ከሕክምና ባለሙያዎች ባገኙት ምክር ከግል የጤና ተቋማት መድሐኒት ለመግዛት መገደዳቸውን ገልጸዋል።

ሳምንቱን በስራ ላይ አሳልፈዉ ለልጃቸዉ ሕክምና ቅዳሜ ወደ ሆስፒታሉ ቢመጡም ሐኪሞች ባለመኖራቸው ለሰዓታት ጠብቀዉ መዉጣታቸውን የገለፁት ሌላኛዉ የሀንጣጤ ከተማ ነዋሪ ከእሳቸዉም ዉጪ ሌሎችም አገልግሎት ለማግኘት መጥተዉ ሲያማርሩ ማየታቸዉንና ችግሩ ከጤና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት ክፍያ ጋር የተያያዘ መሆኑን መስማታቸውን ተናግረዋል።

ሆስፒታሉ ለአከባቢዉ ሕብረተሰብ ከሚሰጠዉ አገልግሎት አንፃር የሚመለከታቸዉ አካላት ፈጣን መፍትሔ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

የዞን አስተዳዳሪ ምን አሉ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያም የማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆስፒታሉ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ መንግስቱ ማቴዎስን ለምን በተገባላቸዉ ቃል መሰረት ክፍያው አልተፈፀመላቸዉ ሲል ጠይቋል ? አቶ መንግስቱ በምላሻቸው " አሁን ጥረት እያደረግን ነዉ፤ ከላይ በጀት ሲገኝ ነዉ ችግሩ የሚፈታዉ " ያሉ ሲሆን " ልጆቹም ስራ ለመስራትም ፈቃደኛ አይደሉም፣ መስራት የሚፈልግ ይቀጥላል ያልተመቸዉ ሊለቅ ይችላል " ብለዋል።

" ኖሪማሊ ጉዳዩ እኔን የሚመለከተኝ አይደለም፤ ወረዳዉ ነዉ ባለቤቱ " የሚሉት የዞኑ አስተዳዳሪ " ሠራተኞቹ እየሄዱበት ያለው አካሄድ ተገቢ አይደለም፤ የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም ብለዉ መደበኛ ስራቸዉን በሚያቆሙ ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የሆስፒታሉ ሰራተኞች የትርፍ ሰዓት ስራ ብቻ ማቆማቸዉንና በተደጋጋሚ ቃል እየተገባ ስለማይፈፀምላቸዉ ስራ ማቆማቸዉን ገልፀዉልናል ይህን ማድረጋቸው ያስጠይቃቸዋል ወይ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላነሳላቸዉ ጥያቄ  " መደበኛ ስራ ነዉ እያቆሙ ያሉት፣ ከደሞዝ መቁረጥ እስከ ማሰናበት እርምጃ ይወሰድባቸዋል " ብለዋል።

" በአንፃሩ የትርፍ ሰዓት ስራ ማቆም መብታቸዉ ነዉ ሲሉም " ተደምጠዋል።

ሰራተኞች ስራ ከማቆማቸዉ በፊት በጽሑፍ ለወረዳ ፣ ለዞኑና ለክልሉም ጤና ቢሮ ጭምር ቅሬታቸዉን ማቅረባቸውን ገልፀዉልናል ፤ በሆስፒታሉ የጤና ክትትል የበራቸዉና ለሕክምናም መጥተዉ በዕረፍት ቀናት አገልግሎት ባለማግኘታቸዉ የተቸገሩ ተገልጋዮችም ቅሬታቸዉን አሰምተዉናል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላነሳላቸዉ ጥያቄ አቶ መንግስቱ " በአካል ካልመጣችሁ ከዚህ የበለጠ መረጃ ልሰጣችሁ አልችልም ! " በማለት አቋርጠዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገዉ ሙከራ በድጋሚ አልተሳካም፤ ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ስንችል የምናካትት ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
😭450131😡101👏51🙏22😢17🥰14🕊12😱10🤔8💔8