TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኙ የአዲስ አበባ ቆሬ አካባቢ አደጋ፦

[ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1]

- አደጋው የደረሰው 5:30 አካባቢ ከብስራተ ገብርኤል ወደ ጀሞ ሲሄድ የነበረና አጠና የጫነ IVECO ግልባጭ መኪና ቆሬ ዓለም ሰላም ድልድይ ውስጥ ባሉ ቤቶች ላይ ወድቆ ነው።

- በአደጋው የሶስት ሰዎች ህይወታቸው አልፏፋ። በአንድ ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። ከሟቾች ውስጥ የ11 ወር ህፃንና ንፍሰጡር ሴትም ይገኛሉ። ነፍሰጡር ሴቷ የ25 ዓመት ወጣት እና የህፃኑ አክስት እንደሆነች ተገልጿል።

- የ28 ዓመት ወጣት የሆነው አሽከርካሪም በአደጋው ህይወቱ አልፏል።

- የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

#ShegerFM #EliasMeseret
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ቢሾፍቱ ውስጥ ኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የያዘው ሰው ተገኝቷል በሚል በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑ ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ተሰምቷል።

የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ የሆኑት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በሰጡት መረጃ ከቻይና ከተመለሰች 12 ቀን የሆናት እና የቫይረሱን የሚመስሉ ምልክቶች ያሳየች አንድ ግለሰብ ቢሾፍቱ ውስጥ ተገኝታ እንደነበር አንስተው ግለሰቧ ወደ ለይቶ ማቆያ ተወስዳ፣ ምርመራ ሲደረግላት ነፃ ሆና ተገኝታለች ብለዋል።

#EliasMeseret
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለሚመለከተው አካል፦

ይህ አዲስ አበባ ከተማ ወሎ ሰፈር አደባባዩ ላይ ያለዉ የድልድይ አካል ቢወድቅ ከስር ባሉ በተላላፊዎች ላይ ጉዳት ስለሚያስከትል ይታሰብበት!

#DrivinginAddis #EliasMeseret

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
42ኛው የካራማራ የድል በዓል የመታሠቢያ ቀን!

የዛሬ 42 አመት ተስፋፊው የመሀመድ ዚያድባሬ ኃይል ካራማራ ላይ አከርካሪው ተሠበረ። በውጤቱም በምስራቅ 700 ኪ.ሜ እንዲሁም በደቡብ 300 ኪ.ሜ ዘልቆ በወረራ ይዞት ከነበረው የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ተጠራርጎ ወጣ ።

ወድቃ የነበረችው ሰንደቃችንም ዳግም ተነስታ በክብር ከፍ አለች።

ይህን በአባቶቻችን ደምና አጥንት እና በእናቶቻችን ደጀንነት ያገኘነውን የመላ ኢትዮጵያውያን የጋራ ደማቅ የድል ታሪክ ለማክበር ድሉ በተገኘበት ዛሬ የካቲት 26 ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በኢትዮ ኩባ ወዳጅነት ፓርክ (በትግላችን ሐውልት) ላይ ለማክበር ዝግጅት ተጠናቋል።

በዝግጅቱ ላይ፦

- በጦርነቱ ወቅት በአመራር ላይ የነበሩ የቀድሞ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች (ጀኔራሎችን ጨምሮ ) ሌሎች መስመራዊ መኮንኖች

- ለድሉ መገኘት ቁልፍ ሚና የተወጡ የጀግናው አየር ኃይላችን አብራሪዎች

- በጦርነቱ የተሳተፉ ባለሌላ ማዕረግተኛ ወታደሮች (የጀብድ ሜዳይ የተሸለሙ ጭምር )

- በጦርነቱ ቤተሠቦቻቸውን ያጡ የኩባ ተማሪዎችና የህፃናት አንባ ልጆች

- ለኢትዮጵያ ድጋፍ በመስጠት በጦርነቱ የተሳተፉ ሀገራት አምባሳደሮች /ተወካዮቻቸው እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ።

በመሆኑም ታሪክና ሀገር ወዳድ የሆናችሁ ዜጎች በዕለቱ በቦታው ላይ ተገኝታችሁ የመታሠቢያ በዓሉን በድምቀት እንድታከብሩ ተጋብዛችሗል።

የበዓሉ ጊዜያዊ አስተባባሪዎች፣ ኮረማሽ የጉዞ ማህበር ከማይክ መላከ የኢትዮ- ኩባ ወዳጅነት ማህበር እና በኢትዮጵያ የኩባ ኤምባሲ ጋር በመተባበር።

#EliasMeseret
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዶክተር ሊያ ታደሰ፦

"የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች [UAE] ውስጥ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሁለት ኢትዮጵያውያን የኤምሬትስ ነዋሪ ሲሆኑ በዛ ሀገር ለአመታት የኖሩ እና በቅርቡም ጉዞ ያላደረጉ መሆኑን አረጋግጠናል"

#EliasMeseret
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ኢትዮጵያዊው የAP ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረትን ጨምሮ 25 የሚሆኑ ከ25 ሀገራት የተውጣጡ ጋዜጠኞች ከነገ ጀምሮ በአሜሪካ 3 ግዛቶች በመገኘት የሀገሪቱን ምርጫን እንዲዘግቡ ፕሮግራም ተይዞ የነበረ ቢሆንም "ለጥንቃቄ" ሲባል ፕሮግራሙ በስድስት ወር እንደተራዘመ ተሰምቷል።

#EliasMeseret
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፓይለቶች ማህበር አባላት የዛሬ አመት በአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ጓደኞቻቸው የማስታወሻ ፕሮግራም አካሂደዋል።

#EliasMeseret #EliasGJ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ኢትዮጵያ፦

- በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው International Community School (ICS) ከነገ ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 11 ትምህርት ቤቱን በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት እንደሚዘጋ አስታውቋል።

- የኮሮና ቫይረስ በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል ትክክለኛውን መረጃ በመጠቀም ረገድ ከመንግስት ተቋማትና ግል ማህበራዊ ሚዲያ አንቀሳቃሾች ጋር ውይይት ተደርጓል።

- የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዛሬው እለት በኮሮና ቫይረስ ቅድመ ጥንቃቄ ዙሪያ ከኢትዮዽያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባል ቤተ እምነቶች ጋር ምክክር አድርጓል።

- የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የጤና ባለሙያዎች ለማሰልጠን፣ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለሟሟላት እና ለህክምና ማዕከላት የሚውል 30 ሚሊዮን ብር አፅድቋል።

- ዛሬ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዓለም የጤና ወረርሽኝ በሆነው የኮሮና ቫይረስ ላይ ምክክር አድርጓል። ዶክተር ሊያ ታደሰ እና ዶክተር ኤባ አባተ በወቅታዊ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ እና ኢትዮጵያ ቫይረሱ እንዳይገባ እያደረገች ባለው ቅድመ ጥንቃቄ ዙሪያ ለምክር ቤቱ አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

#ጤናሚኒስቴር #አዲስፎርቹን #EliasMeseret
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaBOT
ከአሉባልታዎች እና ሀሰተኛ መረጃዎች ተጠበቁ!

ይህ በቀኝ በኩል ያለ ፎቶ ለቀናት "አንድ ቻይናዊ ዱከም ያለው ኢንደስትሪ ዞን ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ይዞት ያሳያል" እየተባለ በብዛት ሼር ሲደረግ ነበር።

ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ከኢንደስትሪ ዞኑ የኮሚኒኬሽን ክፍል መረጃ ተቀብሎ እንዳሰራጨው ከሆነ ግለሰቡ የልብ ህመም አጋጥሞት እንጂ ከቫይረሱ ጋር የተያያዘ አልነበረም። ግለሰቡ አሁን ጤና ተመልሶ በግራ በኩል ያለው ፎቶ ላይ ይታያል።

#EliasMeseret
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር ሀገር አቀፍ መረጃዎች፦

- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሥራ እንዲውል የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለግሰዋል።

- ሼህ ሁሴን አሊ አላሙዲ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝን ለመግታት የ120 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል። በተጨማሪ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ማኔጅመንት፣ አመራር እና ሠራተኞች ከ10 ሚልዮን ብር በላይ ለተመሳሳይ አላማ አበርክተዋል።

- የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ 14, 000 ሰራተኞቹን በጊዚያዊነት ከስራ አሰናብቷል። ሰራተኞቹ ከስራ የተሰናበቱት በአሜሪካና በአውሮፓ ገበያዎች የምርቶቹ ዋነኛ ተቀባይ የነበሩት ድርጅቶች በኮሮና ምክንያት የገበያ ፍላጎታቸው እየተቀዛቀዘ በመምጣቱ ነው።

- መከላከያ ሰራዊት ነገ በአዲስ አበባ የቫይረሱን ስርጭትን ለመግታት የሚያግዙ መልዕክቶችን የያዙ በራሪ ወረቀቶችን በሄሊኮፕተር ይበትናል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ በማርሽ ባንድ የታጀበ የማንቂያ ቅስቀሳ ያደርጋል፡፡

- አልማ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ መመደቡን አስታውቋል።

#DW #etv #EliasMeseret #fbc #ena
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia