TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እንኳን ደስ አላችሁ!

#TIKVAH_ETH በሁለት ዓመት ከአንድ ወር ከሃያ አንድ ቀን ከመላው ሀገሪቱ እንዲሁም ከተለያዩ የውጭ ሀገራት ከ400,000 በላይ የቤተሰብ አባላት ማፍራት ችሏል።
_______________________________________

ሰው በሰውነቱ ብቻ የሚከበርባት ሀገር እንድትኖረን እንመኛለን፤ መመኘት ብቻ አይደለም ለዚህ እውን መሆን ያለእረፍት እንሰራለን፡፡

TIKVAH-ETHIOPIA❤️ተስፋ ኢትዮጵያ

አንዱ የአንዱን ባህል፣ ቋንቋና ሃይማኖት ማክበር ከቻለ፤ ከጥላቻ እና ከቂም በቀል ነጻ የሆነ አስተሳሰብ መፍጠር ከተቻለ፤ ልዩነቶችን በውይይት መፍታት ከተቻለ፤ ለመልካም ነገር ለመተባበር ደግሞ ልዩነታችን መሰናክል ካልሆነ #ተስፋ_አለን የኛ ኢትዮጲያ ለሁላችንም የምትመች ሀገር ትሆናለች፡፡ TIKVAH-ETH ውስጥ የተሰባሰብነው እርስ በእርሳችን በመከባበር እና በመዋደድ የተሻለች ሀገር ገንብተን ለመጭው ትውልድ ለማስረከብ ነው።

ሁላችሁንም እናከብራችኃለን!

ረጅም ርቀት አብረን እንጓዛለን!
ሰላም፤ ፍቅር፤ ተስፋ!
TIKVAH-ETH
እንኳን ደስ አለን፤ እንኳን ደስ አላችሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሆሳዕና⬆️

"በሆሳዕና አቢዮ ኤርሳሞ ስታድየም ከለሊቱ 12 ሰኣት ጀምሮ ነበር ህዝቡ ዶ/ር አቢይን ለመቀበል የገባው!" #TIKVAH_ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡ ሠልፉ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በምዕመኗቹ ላይ የሚፈፀመው ግፍ እንዲቆም የሚጠይቅ ነው፡፡ በሰልፉ ላይ ‹‹በቤተ ክርስቲያንና በምዕመኖቿ ላይ የሚፈጸመው ግፍና መከራ ይቁም፡፡ በቤተ ክርስቲያንና ምዕመኖቿ ላይ ግፍ የፈጸሙት በሕግ ይጠየቁ፡፡›› የሚሉ መልዕክቶች ተላልፈዋል።

ሰልፍ ከተካሄደባቸውን ከተሞችና አካባቢዎች መካከል ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ይገስኙበታል፦

•ራያ ቆቦ
•ኮን
•ዳንግላ
•ሞጣ
•ዳባት
•ጫጫ
•መሐል ሜዳ
•ውጫሌ
•ደላንታ ወረዳ
•ደብረ ብርሃን
•ደብረ ማርቆስ
•ወልዲያ
•ባህር ዳር
•ላልይበላ
•ደባርቅ
•ቡሬ
•ቢቸና
•ፍኖተ ሰላም
•ወረኢሉ
•ኢንጂባራ
•መርዓዊ
•አረሪቲ

በበርካታ ቦታዎች የተካሄዱት ሰልፎችም በሰላም መጠናቀቃቸውን የቤተሰቦቻችን አባላት ገልፀዋል።

#TIKVAH_ETH

ፎቶ: ከማህበራዊ ሚዲያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም ለሰራተኞቹ የ23 በመቶ የደሞዝ ጭማሪ አድርጓል። #ETHIO_TELECOM #TIKVAH_ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህብረተሰባችን ስለምርጫም ሆነ ስለ ምርጫ ቦርድ ያለው አመለካከት የተዛባ ነው እንዴት ይስተካከል?

በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ ምርጫ ዋናው ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡ ሀገራችንም በዘንድሮው አመት 6ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ እየተዘጋጀች ሲሆን ይህንን የማስፈጸም ስልጣን የተሰጠው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት በርካታ ሪፎርሞችን በማድረግ ገለልተኛና ብቁ ተቋም በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡ ይህም ሆኖ ግን ዜጎች ከዚህ በፊት በነበሩት ምርጫዎች ምክንያት ስለ ምርጫና ምርጫቦርድ ያላቸው አመለካከት የተዛባ መሆኑ እንደሚያሳስባቸው የጠቀሱት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አባል የሆኑት ዶክተር አበራ ይህንንም ችግር ለመፍታት የመራጮች ትምህርት ለመስጠት ዕቅድ መያዛቸውን ጠቁመዋል፡፡ ለዚህም አዲስ የመራጮች ማኑዋል ተዘጋጅቶ ለቦርድ ቀርቦ ከጸደቀ በኀላ በሥራ ላይ እንዲውል ይደረጋል ብለዋል፡፡ እንደ ዶ/ር አበራ ገለጻ ይህ የስልጠና ማኑዋል በቦርዱ ከጸደቀ በኃላ በተለያዪ ቋንቋዎች እንደሚተረጎምና አካል ጉዳተኞችን ባካተተ መልኩ እንደሚቀርብ ጠቅሰዋል፡፡

#TIKVAH_ETH

ተጨማሪ ያንብቡ👉 https://telegra.ph/ምርጫ-10-08

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🕌 እጅግ የምናከብራችሁና የምንወዳችሁ ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሆናችሁ ቤተሰቦቻችን እንኳን 1 ሺህ 494ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ በዓሉ የሰላም፣ የመረዳዳት የመደጋገፍ በዓል እንዲሆንልን እንመኛለን መልካም በዓል🕌

#TIKVAH_ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE

በደሴ ከተማ አስተዳደር ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ክፍሎች የተወጣጡ የእምነቱ ተከታዮች በሞጣ ከተማ በእምነት ተቋማት ላይ ደረሰው ጥቃት አሳፋሪ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የእምነቱ ተከታዮች በደሴ ከተማ በሚገኘው ዐረብ ገንዳ መስጂድ ባደረጉት ውይይት አጥፊዎቹ በሕግ ሊጠየቁ እንደሚገባም ጠይቀዋል፡፡ ጥቃቱ ከመድረሱ በፊትም ሆነ ከደረሰ በኋላ መንግሥት እያሳዬ ያለው ለዘብተኛ አቋም መታረም እንደሚገባውም አሳስበዋል፡፡

የክልሉ መንግሥት በመስጂዶች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንደሚደርስ መረጃዎች እንደነበሩት በማንሳትም ቅድመ መከላከል አልሠራም በሚል ወቅሰዋል፡፡ ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላም በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ተጠርጣሪዎች ቁጥር አነስተኛ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

መንግሥት የተቃጠሉ ቤተ እምነቶችን እንዲሠራና የተዘረፉ ንብረቶችን እንዲመለሱ ማድረግ እንደለበትም ተናግረዋል፡፡ችግሩ እንዲባባስም ሆነ የቤተ እምነቶች እንዲቃጠሉ የሚዲያ አካላት ድርሻ ከፍተኛ እንደሆነም ነው ተወያዮቹ ያነሱት፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ሚዲያ አውታሮች በተለይ በመስጂዶች ላይ ጥቃት ሲደርስ የሚሰጡት ሽፋን ሚዛናዊ እንዳልሆና መታረም እንደሚገባውም መክረዋል፡፡ መንግሥት የተቃጠሉ ቤተ እምነቶችን እንዲሠራና የተዘረፉ ንብረቶችን እንዲያስመልስም አሳስበዋል።
#AMMA

#TIKVAH_ETH

በሞጣ ከተማ በእምነት ተቋማት ላይ የተፈፀመው ድርጊት የሚያወግዙ ሰልፎች በተለያዩ ከተሞች እና አካባቢዎች እንደተደረጉ መረጃዎች ደርሰውናል። በባሌ ደሎ መና በተካሄደ ሰልፍ የሙስሊሙ እና ክርስትያኑ ማህበረሰብ አባላት ድርጊቱን አደባባይ በመውጣት በጋራ አውግዘዋል። በተለያዩ ከተሞች እና አካባቢዎች የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎችን ማስፈንጠሪያውን በመጫን መመልከት ትችላላችሁ https://telegra.ph/TIKVAH-12-22

@tikvahethiopiaBot
ይነበብ!

#TIKVAH_ETH የፌስቡክ፣ የትዊተር፣ የኢንስታግራም ገፅ የለውም። በቤተሰባችን ስም የሚለጠፉ መረጃዎች እና መልዕክቶች በሙሉ እኛን የሚወክሉ አይደሉም!

ውድ ቤተሰቦቻችን ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን፣ ከቤተሰባችን አባላት፣ መረጃዎችን #እያሰባሰብን የምናስቀምጠው፦

ሚዛናዊ፣ ሁሉን በእኩል የሚያይ ስለ ነገ የሀገሪቱ ሁኔታ የሚያስብ፤ የሚጨነቅ፣ በምክንያት የሚያምን፣ ቅሬታውን በማስረጃ የሚያሳምን፣ በማህበራዊ ሚዲያ ያልተጨበጡ ወሬዎች የማይደናገር፣ የተረጋጋ፣ ሀገሪቷን ችግር ላይ ከሚጥል ወገንተኛ አካሄድ የነፃ አመለካከት፣ ነባራዊውን የሀገሪቱን ሁኔታ የሚረዳ፣ ቤተሰብ ለመፍጠር በማሰብ ነው።

በተጨማሪም የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆናችሁ ሰራተኞች በስራችሁ ላይ፣ ተማሪዎችም በትምህርታችሁ ላይ አትኩሮታችሁን አድርጋችሁ በቀን በተወሰነ ሰዓት ክፍተት የተፈጠሩ አዳዲስ ጉዳዮችን፣ የቤተሰባችን አባላት ያጋሩትን፣ በሚዲያዎች ሽፋን የተሰጣቸውን ጉዳዮችን እጅግ በአጭሩ ሳትሰለቹ እንድታነቡ ለማድረግ ነው።

እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መረጃ ለማግኘት የምትገሉትን ረጅም ሰዓት፣ እግረ መንገድም የምትመለከቷቸውን የጥላቻ ንግግሮችን ለማስቀረትም ያለመ ነው። በተጨማሪም ከአፀያፊ፣ የሰዎችን ክብር ከሚነኩ አስተያየቶች፣ ለግጭት ከሚያነሳሱ፣ አእምሯቹን ከሚረብሹ መልእክቶች እንድትርቁ ለማድረግ ነው።

ለቲክቫህ ቤተሰቦች መረጃዎች አይደበቁም፤ እንደወረዱም አይቀርቡም፤ እጅግ ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ ከመገናኛ ብዙሃን የምንሰማውን፣ የምናነበውን፣ ከቤተሰባችን አባላትም የሚላኩትን መረጃዎች በጥንቃቄ እናጋራለን።

እጅግ አደገኛ ጊዜ ላይ እንደምንገኝ ሁላችሁም የምታውቁት ነው። ማህበራዊ ሚዲያው ሀገር እያተራመሰ ነው፤ ለዚህም በቂ ማስረጃ ማቅረብ እንችላለን። እኛ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ስለምን እንደዚህ ያለ ነገር ውስጥ፤ ነገ ሊፀፅተን በሚችል ጉዳይ ላይ እንሳተፋለን? በፍፁም አናደርገውም! መረጃዎች ስናጋራ፣ ለፀጥታ እና ደህንነት፣ ለመንግስትም ችግር ሲኖር በገፃችን ጥቆማ ስንሠጥ የምንጠነቀቀውም ያለ ምክንያት አይደለም።

ለምሳሌ፦

ከዚህ ቀደም (ከሁለት ዓመት በፊት) ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሚታወቀው ቀጥታ የቤተሰቡን አባላት መልዕክቶችን እንደዋረደ እያጣራ በማጋራት ነው፤ በተለይ ዩኒቨርሲቲዎች እና ወጣቶች ላይ በማተኮር ያላቸውን ጥያቄዎች፣ ዜጎች በመንግስት ላይ ያላቸው ተቃውሞዎች፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ በዜጎች ላይ የሚደርሱ በደሎች፣ ፍትሃዊ ያልሆኑ ድርጊቶችን፣ በየተቋማት ውሥጥ በሰራተኞች ላይ የሚፈፀሙ በደሎችን ወዘተ...

በዛን ሠዓት እንኳን በድፍረት፣ ያለምንም ፍራቻ፣ ለማንም ሳንወግን ስናቀርብ፣ የናተንም መልዕክቶች ስናጋራ ነበር። ዛሬም አንደ አንድ የሀገሪቱ ዜጋ የትኛውም አካል መንግስት ላይ ቅሬታ ሲኖረው፣ ተበድያለሁ ካለ፣ የትኛውም ወገን ተቃውሞ ሲኖረው በቀጥታ እናቀርባለን። እኛ ከሚቀያየረው ፓርቲ ወይም መንግስት አልያም ሀገር አስተዳዳሪ ጋር ሳይሆን ከህዝቡ ጋር ነን!

ነገር ግን ጊዜ ወዲህ ነገሮች በሙሉ መልካቸውን ቀይረዋል (ለአብነት ዘንድሮ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የተፈጠረውን መመልከት በቂ ነው)፣ እያንዳንዱ ጉዳይ ወደ ብሄር ይቀየራል፣ ወደ ሃይማኖት ይዞራል። ይህ ነው ፈታኙ ሰዓት! አንድ ቦታ በሚሰጥ እና በሚነገር መረጃ ሌላ ቦታ ከፍተኛ እልቂት ሲፈፀም በተደጋጋሚ አይተናል።

በሀሰተኛ መረጃ ሰዎች ሲገደሉ፣ አለመረጋጋት ሲፈጠር፣ ሰዎች ሲፈናቀሉ፣ የእርስ በእርስ ግጭት ሲቀሰቀስ ሰምተናል። ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ በርካታ ጉዳዮች እየተመዘዙ እንደሆነ እየተመለከትን ነው እያንዳንዱን ነገር እንደ ከዚህ ቀደሙ እንደወረደ ይቅረብ ከተባለ ችግር አባባሽ እንጂ ችግር ፈቺ ቤተሰብ ልንሆን አንችልም።

ይህንን ያልተረዱ፤ አንዳንዶች ሆን ብለው፣ ምናልባትም ከሰላም ይልቅ እልቂት የሚፈልጉ፣ ሀገራችን እንድትፈርስ የሚፈልጉ፣ ሰላም ውለን ሰላም ስናድር የሚያማቸው፤ እንቅልፍ የሚነሳቸው ግለሰቦች እያንዳንዱን ብሄር ከየአቅጣጫው እየጠራን ነገሮች እንድናጋጋል ይፈልጋሉ፤ በፍፁም የሌለብንን፣ ወደፊትም የማይኖርብንን የሀይማኖት፣ የብሄር ወገንተኝነት ሊለጥፉብን ይፈልጋሉ እኛ እንዲህ ባለማድረጋችን፣ ለነሱ አጀንዳ ባለመመቸታችን ስድብ ያከናንቡናል፤ የጥላቻ ንግግሮችን ያዘንብቡናል።

እነሱ የሚሉት ካልሆነ ሌላው ጠላታቸው፣ የነሱ መረጃ ካልሆነ ዘረኝነት እና ወገንተኛ እንደሆነ አድርገው ይነግሩናል፤ የቤተባችንን ስም ለማጥፋት ይደክማሉ። ልፉ ሲላቸው 😊 ነገር ግን የቲክቫህ ባለቤቶች የሆኑ አባላት ( 508,500 በላይ ) ሁሉም ወጥቶ አልቆ አንድ ሰው ቢቀር እንኳን ሀገራችንን ወገናችንን አደጋ ላይ ለሚጥል ጉዳይ በፍፁም አንገዛም። ውድ ቤተሰቦቻችን ያለምንም ግፊት እና ማስታወቂያ ከ1 ተነስተን ግማሽ ሚሊዮን መድረሳችንን አትዘንጉት። ብቻችን ብንቀር እንኳን ሀገራችንን ሊያሳጣን፣ ህዝብን ከህዝብ ሊያፋጅብን ይችላል ከምንላቸው ጉዳዮች በሙሉ እንደራቅን እንቀጥላለን።

እኛ ሀገር በማተራመስ ውስጥ እጃችንን አናስገባም! ግጭት በማጋጋል ውስጥ አንሳተፍም! ብሄር ከብሄር፤ ሃይማኖት ከሃይማኖት በሚያጋጭ አፀያፊ ድርጊት እጃችን አይገባም ይህን በማድርጋችን ቅር የሚሰኝ ካለ የቤተሰባችን አባል መሆን አይገባውም። በኃላፊነት ቲክቫህ የኔ ነው ለሚሉ የቤተሰባችን አባላት መረጃዎችን በከፍተኛ ጥንቃቄ እናቀርባለን። በድጋሚ መልስ ብላችሁ ከሁለት ዓመት የነበረውን የሀገሪቱን የፖለቲካ ትኩሳት እና አሁን ያለውን ተመልከቱና ፍርዱን ስጡ!

ከ2 ዓመት በፊት እንደምናደርገው መረጃ እንደደረሰን፣ ከሚዲያዎች እንዳነበብን፣ እንደወረደ አናጋራም፤ ከናተ የተሻለ የሀገሪቱን ፈተና እና ከፊት ያለውን አደጋ የተረዳ አካል ያለ አይመስለንም። በመሆኑም እጅግ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ የቤተሰባችን አባላት #ብቻ ሚዛናዊ፣ ሁሉን አቀፍ፣ እውነተኛ፣ ገለልተኛ መረጃዎች እያሰባሰብን እንድታነቡ እንሰራለን።

እኛ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በየጊዜው የሃይማኖት ካርድ እየተመዘዘ፣ የብሄር ካርድ እየተመዘዘ እልቂት ውስጥ እንድንገባ፤ ሀገራችን ፈርሳ ሀገር አልባ ሊያደርገን በሚችል የማህበራዊ ሚዲያ አጀንዳ በፍፁም ተጠልፈን አንወድቅም!

508,500+☺️የቲክቫህ ቤተሰቦች፣ 508,500+☺️የቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለቤቶች!

Addis Abeba,Ethiopia
[email protected]
0919743630
@tsegabtikvah
@tsegabwolde
@tikvahethiopia

@tikvahethiopiaBot 👈 የቤተሰባችን ሀሳብ መቀበያ!
የቲክቫህ ቤተሰቦች ጥቆማ ስጡ...

የህጻናት መጫወቻ በትምህርት ቤቶች ውስጥ መኖር ለህጻናት ትልቅ ደስታ ሲሆን የትምህርቱንም አሰጣጥ ቀላልና ውጤታማ ያደርገዋል፡፡

አሁን ላይ የግል ት/ቤቶች ዘመናዊና ጽዱ የመጫወቻ ስፍራ ሲኖራቸው አብዛኛው የመንግስት ትምህርት ቤቶች ደግሞ ለዚህ ብዙም አልታደሉም፡፡

ይህ ደግሞ የመጫወቻ ስፍራዎች በራሳቸው የሀብትን ደረጃ መለኪያ እየሆኑ መምጣታቸው የህጻናቱ አዕምሮ ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ ቀላል የሚባል አይሆንም፡፡

ልዩነቱን ማጥፋት ባይቻል እንኳን ለማጥበብና ህጻናትን ደስተኛ ሆነው እንዲማሩ ለማስቻል ' ኩኩሉ ' በሚል መጠሪያ የተለያዩ የመንግሥት ትምህርት ቤቶችን የህጻናት መጫወቻዎችን በራሳቸው ወጪና ጉልበት በመስራትና በማስዋብ ህጻናት ትምህርት ቤታቸውን እንዲወዱና በቀላሉ ተዝናንተው ለትምህርት የተዘጋጀ አዕምሮ እንዲኖራቸው ለማስቻል እየሰሩ የሚገኙ ወጣቶች ብቅ ብለዋል፡፡

የማህበሩ አባለት እስካሁን አራት ት/ቤቶችን የመጫወቻ ሥፍራዎችን በመስራትና በማደስ ትልቅ አበርክቶ አድርገዋል አሁንም ይህንን ሥራቸውን በስፋት ለመስራት ቢያስቡም የተሻለ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ት/ቤቶች መለየት ፈታኝ እንደሆነባቸው ይናገራሉ፡፡

ለዚህም በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙና የመማሪያ ክፍል ጥገና፣ የወንበር ጥገና፣ የመጫወቻ ስፍራ የሌላቸው ድጋፉ ያስፈልጋቸዋል የሚባሉ ትምህርት ቤቶችን የቲክቫህ ቤተሰቦች በአከባቢያቸው ተመልክተው ቢጠቁሙን እኛ ለመስራት ዝግጁ ነን የሚል ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ጥቆማ መስጠት የምትፈልጉ፦ +251913185145 / +251 91 155 2494

#TIKVAH_ETH
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

ባደጉት ሀገራት ሳይቀር የጤና ባለሞያዎች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመዋጋት እጅግ በጣም ከፍተኛ ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ። በርካታ ዶክተሮች ህይወታቸው አልፏል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ናቸው።

ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ቁጥር ምናልባትም የመመርመር አቅማችን እንዲሁም ከቫይረሱ ተጠቂዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች አፈላልጎ የማግኘቱ ስራ ከተጠናከረ በእጅጉ ከፍ ሊል ይችላል።

ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት ኮሮና ቫይረስን በመዋጋት ከፊት መስመር ለሚሰለፉት የጤና ባለሞያዎች ግብዓቶችን ከማማላት አንፃር ልዩ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል። በመከላከያ ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ብዙ ዋጋ እንዳንከፍልም እንሰጋለን።

በሌሎቻችን ዘንድ ግን ይህ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] አሁንም 'መድሃኒት ያልተገኘለት' ፣ በየዕለቱም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት የሚቀጥፍ ፣ ብዙ ሺዎችን ሆስፒታል እያስተኛ የሚገኝ አደገኛ በሽታ መሆኑን አውቀን ሳንዘናጋ እራሳችንን ልንጠብቅ ይገባል። የጤና ባለሞያዎችን ምክር መስማትም ይበጃል!

#TIKVAH_ETH

መልካም ምሽት!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia