TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር ከአጋሮቹ ከዩኒሴፍ እና ከሕፃናት አድን ድርጅት ጋር በመሆን ትምህርታዊ ዝግጅቶችን በኢትዮሳት የቴሌቪዥን መድረክ ማስተላለፍ ጀመሩን #SavetheChildren በላከልን መግለጫ አሳውቋል።

ለትምህርት ማሰራጫነት የታለመው የመጀመሪያው የሳተላይት መድረክ ኢትዮሳት በኮቪድ-19 ምክንያት የተቋረጠውን የትምህርት ቤቶች የትምህርት ተግባር ለማሰቀጠል እንዲቻል ዘጠኝ ትምህርታዊ ቻነሎችን በስርጭቱ ሥርዓት ውስጥ እንዲካተቱ አድርጓል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
#SavetheChildren

የህፃናት አድን ድርጅት (Save the Children) ይፋ ያደረገው መረጃ በዓለማችን መካከለኛና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚኖሩ ቤተሰቦች የተገኙ ወደ 594 ሚሊዮን የሚጠጉ ህፃናት ኮቪድ-19ን ለመቋቋም የሚያፈልጋቸውን የገንዘብ እርዳት ከሃገሮቻቸው መንግስታት እንዳላገኙ ያሳያል።

ከSave the Children የተላከልልን ሙሉ መረጀ ከላይ ይመልከቱት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SavetheChildren

ባለፉት አራት ሳምንታት ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን የገቡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ቁጥር ከ45 ሺህ ማለፉን UNHCR አስታውቋል።

ከነዚህ መካከል 45% ህፃናት እንደሆኑም ገልጿል።

በሱዳን ኡም ራክባ 158 የሚሆኑ ወላጅ እና አሳዳጊ ሳይኖራቸው ብቻቸውን መገኘታቸውን በሱዳን የSave the Children ዳይሬክተር አርሻድ ማሊክ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ ህፃናቱ በአስር (10) ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ መሆናቸውን ገልፀው ካምፕ ውስጥ ባለው መጨናነቅ የተነሳ መሰረታዊ ነገር ለማሟላት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ከላይ የተጠቀሰው አሃዝ በአንድ የስደተኞች ማዕከል በተደረገ የመረጃ ማሰባሰብ ሂደት የተገኘ መሆኑን ገልፀው እንደ ሃምዳይት ባሉ ከ30 ሺህ በላይ ስደተኞች ባሉበት ትልልቅ ካምፖች ብዙ ህፃናት ሊገኙ ይችላሉ ብሏል።

ሁኔታው ህፃናቱን እና ታዳጊዎቹን ለተለያዩ ጥቃቶች እና ብዝበዛ ሊያጋልጣቸው እንደሚችል ገልፀዋል።

Save the Children ከሱዳን መንግስት እና ከተመድ (UNHCR) ጋር በመተባበር መሰረታዊ የሆነ ድጋፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ለቪኦኤ ራድዮ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Tigray

የህፃናት አድን ድርጅት / Save the Children / በትግራይ ክልል ትምህርት ቤቶችን ከስጋት ነፃ ለማድረግ በተሰራ ስራ 1 ሺህ 231 ያልመከኑ ፈንጂዎች መገኘታቸው ገለፀ።

አሀዱ ሬድዮ ፤ የህጻናት አደን ድርጅት በኢትዮጵያ / Save the Children /  የትግራይ ክልል አስተተባባሪ የሆኑትን አቶ አታክልቲ ገብረ ዮሓንስን ዋቢ በማድረግ ባሰራጨው መረጃ ፤ ከሰላም ስምምነቱ በኃላ 1 ሺህ 218 ት/ ቤቶች የተከፈቱ ሲሆን  722ቱ የሚሆኑት በደረሰባቸው ከባድ ጉዳት አገልግሎት አልጀመሩም።

ተማሪዎች 3 ዓመት የትምህርት ገበታቸው ላይ አለመገኘታቸውን ያነሱት አስተባባሪው አሁን ላይ ለ39 ሺህ መምህራን የ3 ወር  ደሞዝ መከፈሉን አሳውቀዋል።

ት/ቤቶችን ከስጋት ነጻ ለማድረግና የተማሪዎቹ ደህንነት እንዲጠበቅ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን እና ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር በተሰራው ስራ በ1 ሺ 544 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 231  #ያልመከኑ ፈንጂዎች መገኘታቸውን  ጠቁመዋል።

ድርጅቱ የተሸከርካሪ እና ሌሎችም ድጋፎችን በማድረግ በጋራ በተሰራው ስራ ትምህርት ቤቶችን ከስጋት ነጻ ማድረግ እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡

ለ40 ሺህ ተማሪዎች በ59 ትምህርት ቤቶች ላይ የህጻናት አደን ድርጅት በኢትዮጵያ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉን አቶ አታክልቲ ገብረ ዮሓንስ ለአሐዱ ገልፀዋል።

#አሐዱ #SavetheChildren

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ከተጎጂዎች መካከል 30,427 ህፃናት ናቸው። የሟቾች ቁጥር ከ40 በላይ ደርሷል ” - ሴቭ ዘ ቺልድረን በሶማሌ ክልል ከተከሰተ የወራት ያለፈው የጎርፍ አደጋ የውሃ መጠኑ እየቀነሰ የመጣ ቢሆንም ትንበያዎች የሚያመለክቱት በመጪው የዝናብ ወቅት ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንዲሚችል ስለሆነ፣ ህብረተሰቡም አሁንም ካለፈው የጎርፍ አደጋ ገና እያገገመ በመሆኑ፣ ትልቅ ፈተናና ስጋት መፍጠሩን በቦታው የሚገኘው…
#SavetheChildren

“ በሚያሳዝን ሁኔታ 70 ሰዎች በኮሌራ ሕይወታቸውን አጥተዋል። 9 ሰዎች በኩፍኝ ሞተዋል ” - የህጻናት አድን ድርጅት

በሶማሌ ክልል በተለይም #የጎርፍ_አደጋ በደረሰባቸው ወረዳዎች በተፈናቀሉ ወገኖች የተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሆነ የክልሉ የህጻናት አድን ድርጅት (Save the children) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የድርጅቱ ምሥራቅ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ አብዲራዛቅ አህመድ ፣ የኮሌራ ወረርሽኙ እንደቀጠለ መሆኑን በሴፕተምበር 2023 ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ በድምሩ 7, 480 ሰዎች እንደተጎዱ ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ በሰጡት ቃል፣ “ በሚያሳዝን ሁኔታ 70 ሰዎች በኮሌራ ሕይወታቸውን አጥተዋል። 9 ሰዎች ደግሞ በኩፍኝ ሞተዋል ” ብለዋል።

በተጨማሪም ከ2024 መጀመሪያ ጀምሮ 533 ሰዎች በኩፍኝ በሽታ እንደተያዙ፣ 9ኙ ሰዎች ለሞት የተዳረጉት በጎዴ ከተማ፣ ጎዴ ወረዳ፣ በራኖ አካባቢዎች መሆኑን አስረድተዋል።

ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ምንድናቸው ?

📣 በጎርፍ ለተጎዳ ማህበረሰብ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚደረግ ምላሽ፣ የአደጋ ጊዜ መጠለያ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ ለማደረግ አቅርቦቶችን ማጎልበት። የኮሌራ ክትባቶች ከፍተኛ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች መስጠት ይገባል።

📣 የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ መሠረታዊ እና አስፈላጊ የጤና አገልግሎቶችን ለማቅረብ ወሳኝ በሆኑ የጤና ተቋማት ላይ ጉዳት እንዳደረሰ በመገንዘብ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የጤና መሠረተ ልማት ግንባታ ላይ መዋዕለ ነዋይ ሊፈስ ይገባል።

📣 #ህፃናት በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሆናቸው ልዩ እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል። 

#ጥሪ

(አቶ አብዲራዛቅ አህመድ)

" ለለጋሽ ማህበረሰቡ አንድ ጥሪ ማቅረብ እፈልጋለሁ። ወረርሽኝ እና ተደጋጋሚ የጎርፍ መጥለቅለቅ የሚያመጣውን ከፍተኛ ጉዳትና ተጽዕኖ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመቀነስ የገንዘብ ድጋፍ ያስፈልጋል። "

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia