TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አማራ🕊ቅማንት!

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው ሰሞኑን ግጭት እየተስተዋለባቸው ባሉ የማዕከላዊ ጎንደር ቀበሌዎች በመገኘት ከአርሶ አደሮች ጋር ዛሬ ተወያይተዋል። ካሳለፍነው እሁድ ሌሊት ጀምሮ በጭልጋ ወረዳ ባሉ ቀበሌዎች በተመሳሳይ ሰዓት በተፈጠረ ጥቃት የሰው ህይወት አልፏል፡፡ በርካታ ቤቶች ላይ ደግሞ ቃጠሎእና ዝርፊያ ተፈጽሟል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ #ላቀ_አያሌው ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎ ንብረታቸውን ጭምር ተዘርፈው ተፈናቅለው በአንድ ቦታ ከተሰበሰቡ
ተፈናቃዮች ጋር ባደረጉት ቆይታ አርሶ አደሮቹ በርካታ ሃሳቦችን አቅርበዋል።

የአማራና ቅማንት ህዝብ ዘመናትን በአብሮነት #በሰላምና #በፍቅር አሳልፎ የተዋለደ አንድ ህዝብ ቢሆንም ሁለቱ ህዝብ እንዲለያይ ተደርጓል። ይሁን እንጅ በተፈጠረው ሴራ አሁንም ድረስ ግጭቶች እንዲፈጠሩ ብሎም ሞትና ስደት እንዲፈጠር መደረጉ አሳዛኝ ነው ያሉት አርሶ አደሮቹ በተለይ የቅማንት ሰዎች ነን የሚሉ ዘመናዊ መሳሪያና የወታደር ልብስ የታጠቁ አካላት በአማራው ላይ ግፍ እየፈፀሙ ናቸው ብለዋል።

ራሳችንን ለመከላከል ጥረት በምናደርግበት ወቅትም የማናውቃቸው ፀጥታ ነን የሚሉ አካላት አማራው ላይ ጫና እያሳደሩ ለሞት ስደት እና ዝርፊያ እንድንዳረግ አድርገዋል ብለዋል።

መንግስት ወንጀል እየፈፀሙ ያሉ ግለሰቦችን ድርጅቶችንና በማንነት ስም የሚነግዱ አካላትን በመለየት እርምጃ መውሰድና ህግን ማስከበር አለበት ብለዋል።

አሁን ተፈናቅለን ያለን አርሶ አደሮች መሰረታዊ ፍላጎቶቻችንን እየጨረስን በመሆኑ መንግስት ሊደርስልን ይገባልም ብለዋል።

ከአንድ ቀበሌ ተሰባስበው የመጡ ተፈናቃዮች ወደ 500 አርሶ አደሮች እንደሚደርሱ የገለፁ ሲሆን በተለይ ህፃናትና ሴቶች እንዲሁም አረጋውያን ለከፋ ግጭት እየተጋለጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የቅማንት ህዝብ የማንነት ጥያቄ በክልሉ ምክር ቤት ራሱን እንዲችል ውሳኔ ከተሰጠ ወዲህ በነባሩ ጭልጋ(የአማራ ወኪል) እና በጭልጋ ቁጥር አንድ (የቅማንት ወኪል) በሚል ለሁለት አስተዳደር የተከፈለችው የጭልጋ ወረዳ አስተዳዳሪዎቿ በሰጡት አስተያየት እየተከሰተ ያለው ግጭት የሁለቱንም ህዝብ ፍላጎት የሚያንፀባረቅ አለመሆኑን ተናግረዋል። በማንነት ስም ሁከትና ትርምስ እየፈጠሩ ባሉ አካላት ላይ የማያድግም እርምጃ በመውሰድ መፍትሄ መስጠት የክልሉና የፌዴራል መንግስት ድርሻ ነው ብለዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ላቀ በበኩላቸው በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ የሚሰሩና የሁለቱንም ህዝቦች የማይወክሉ አካላት መኖራቸውን ገልፀው ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ለዚህም
የሁለቱ ህዝቦች ወንጀለኞችን የማጋለጥ ስራ በማከናወን ከመንግስት ጎን መቆም አለባችሁ ብለዋል።

የክልሉ መንግስት ችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ላቀ በግጭቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ህዝቦች ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

በጭልጋ ወረዳ በተቀሰቀሰው የሰሞኑ ግጭት ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ሞትን ጨምሮ ከ700 ቤቶች በላይ ተቃጥለዋል፤ ንብረት ተዘርፏል። ሰብል ክምር ተቃጥሏል። በአካባቢው ህገ ወጥ ድርጊቶች ተበራክተዋል።

የፌዴራል ወታደርና የክልሉ የፀጥታ ሃይል በአካባቢው ባይመጣ ኖሮ ችግሩ ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን እንደሚችል የአካባቢ ነዋሪዎችና አመራሮች ለአብመድ ተናግረዋል።

የጭልጋ ወረዳ ዋና መቀመጫ አይከል በአሁኑ ሰዓት ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውጭ ሆናለች። ትምህርት ቤቶች ስራቸውን አቁመዋል። የትራንስፓርት እንቅስቃሴም የለም፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ👆

የኦሮሚያ እና የሱማሌ ክልል ህዝቦች #በሰላምና #በፍቅር አብረው ለመኖርና ለመስራት ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚችሉባቸው ሁኔታ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚመክር የህዝብ ለህዝብ መድረክ በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia