TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" አባት፣ እናት እና ልጆች ያሉበትን የቤተሰብ ተቋም ማጠናከር እንፈልጋለን " - ቀዳማዊት እመቤት ሬቸል ሩቶ

ጎረቤት ሀገር ኬንያ በትምህር ቤቶች ውስጥ ተንሰራፍቷል ያለችውን " የተመሳሳይ ጾታ " አጀንዳ ላይ ዘመቻ መጀመሯ ታውቋል።

የኬንያ የትምህርት ሚንስትር ኢዚኬል ማቾጉ ፥ " በኬንያ ትምህር ቤቶች ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች አጀንዳ ሰርጎ ገብቷል " ሲሉ ለአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተናግረዋል።

ሚንስትሩ በት/ ቤቶች ውስጥ " የተመሳሳይ ጾታ አጀንዳን " ለማስቀረት በኬንያ አንጀሊካን ቤተ-ክርስቲያን የሚመሩ ጉዳዩን የሚከታተሉ ሰዎች ይሾማሉ ብለዋል።

በኬንያ ትምህር ቤቶች ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የተመለከቱ ጉዳዮችን የሚከታተል ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን ኮሚቴው #መማሪያ እና #አጋዥ_መጽሐፍትን መከለሰን ሊያካትት እንደሚችል ትምህር ሚንስትሩ ገልጸዋል።

ይህ የኬንያ ትምህርት ሚንስቴር እቅድ የተሰማው ቀዳማዊት እመቤት ሬቸል ሩቶ " የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አደጋ ፈጥሯል " በማለት በመላው ኬንያ #ጸሎት_እንዲደረግ ካወጁ በኋላ ነው።

የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ባለቤት የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት " ቤተሰብ በሚባለው ተቋም ላይ አደጋ ደቅኗል " ብለዋል።

ቀዳማዊት እመቤቷ ፤ " አባት፣ እናት እና ልጆች ያሉበትን የቤተሰብ ተቋም ማጠናከር እንፈልጋለን። የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በአፍሪካውያን ዘንድ ተቀባይነት የለውም። የቤተሰብ እሴቶችን እንጠብቅ " ብለዋል።

የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ኬንያ ውስጥ #ሕጋዊ_አይደለም

የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚቃወሙ አመለካከቶች ባለፉት ቀናት ጠንከር ብለው መታየታቸውን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል (ቀዳማዊት እመቤት ሬቸል ሩቶ)

@tikvahethiopia
ማሕበር ሕውነት ደቂ ሰብ ፤ በማሳደጊያው ውስጥ ያሉትን ከ60 በላይ ህፃናት እና ከድርጅቱ ውጪ የሚኖሩ በቀጥታ ድርጅቱ ድጋፍ ያደርግላችው የነበሩ ጧሪ የሌላቸውን ኣረጋውያን በሚገባቸው ልክ ሊደረስላቸው ስላልቻለ የእኛ የልጆቻቸውን ድጋፍ ጠይቋል።

ማሕበር ሕውነት ደቂ ሰብ ጥያቄውን ያቀረበው ለመላው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦችና ለቀድሞ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ባስተለለፈው መልዕክት ነው።

የቀድሞ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመቐለ ቆይታቸው በማሕበር ሕውነት ደቂ ሰብ (Human Beings Assocations of Brothers Hood) በመመላለስ የተለያዩ ማህበራዊ ግልጋሎቶችን በመስጠት ከድርጅቱ ጎን በመቆም በብዙ ቤተሰባዊ ፍቅር መልካም ጊዜያትን ከድርጅቱ ጋር አሳልፈዋል።

አሁን ላይ ድርጅቱ በወቅታዊው ሀገራዊ ሁኔታ ምክንያት በድርጅቱ ማሳደጊያ ውስጥ ያሉ ከ60 በላይ ህፃናት እና ከድርጅቱ ውጪ የሚኖሩ በቀጥታ ድርጅቱ ድጋፍ ያደርግላችው የነበሩ ጧሪ የሌላቸውን ኣረጋውያን በሚገባቸው ልክ መደገፍ ስላልቻለ የቲክቫህ ቤተሰቦች እንዲሁም የቀድሞ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድጋፍ እንዲደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

ድጋፉ የገንዘብ እና የኣይነት መሆን ይችላል።

የገንዘብ ድጋፉን " #ሕጋዊ በሆነው " በድርጅቱ የንግድ ባንክ ኣካውንት (Human Beings Assocation of Brothers Hood 👉1000016160664 በኩል ማድረግ ይቻላል።

የኣይነት ድጋፉን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ማድረስ ይቻላል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ከዓመታት በፊት በፀረ ጥላቻ ንግግር ዘመቻ የሰላም ጉዞ ወቅት ማሕበር ሕውነት ደቂ ሰብን ጎብኝተው ድርጅቱ ከሚያሳድጋቸው ልጆችም ጋር ጊዜ አሳልፈው ነበር።

ይህ መልዕክት የሚደርሳችሁ የቀድሞ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መልዕክቱን ለሌሎች እንድታጋሩና በምትችሉት አቅም ድጋፋችሁን እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
CBE Name.pdf
#CBE

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቀሪ ገንዘብ ያልመለሱ ገንዘቡን እንዲመልሱ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።

ቀሪ ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ስም ዝርዝርም ይፋ አድርጓል።

ባንኩ ችግር ገጥሞት በነበረበት ወቅት በህገወጥ መንገድ ገንዘብ የወሰዱ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ተመላሽ እንዲያደርጉ አሳስቦ ነበር።

በዚህ መሰረት 9281 የሚሆኑ ግለሰቦች በተሰጠው ጊዜ ገደብ ተጠቅመው የወሰዱትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ መልሰዋል ብሏል።

5166 ግለሰቦች ባንኩ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ በከፊል ተመላሽ ያደረጉ ቢሆንም እስከ ዛሬ ድረስ ቀሪውን ገንዘብ አልመለሱም ሲል ገልጿል።

ባንኩ ወደ ቀጣዩ #ሕጋዊ እርምጃ ከማለፉ በፊት ቀሪውን ገንዘብ እንዲመልሱ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

ገንዘቡን የማይመልሱ ከሆነ በባንኩ በኩል ቀጣይ ሕጋዊ እርምጃ እንደማይኖር አረጋግጧል።

እስከተጠቀሰው ቀን ገንዘቡን #የማይመልሱ ካሉ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘዴዎችን በመጠቀም ፦
- ሙሉ ስማቸው
- ፎቷቸው
- በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ በመውሰድ ወንጀል መጠርጠራቸውን በመግለፅ ለሚመለከታቸው የሕግ አካላትና ተቋማት ይገለጻል ለሕዝብም ይፋ ይደረጋል ብሏል።

ከሕግ አካላት እና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር ቀጣይ #የወንጀል፣ የፍትሐ ብሔር እና የአስተዳደር ሕጋዊ እርምጃዎችም እንደሚወሰዱ በጥብቅ አስጠንቅቋል።

ስም ዝርዝሩን በዚህ መልከቱ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/86375

@tikvahethiopia