TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በቡራዩ ነዋሪዎች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግድያ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ሰዎች ላይ የፀጥታ ሐይል የፈጸመው #ግድያ እንዲመረመር ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል አሳስቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ክፍል 1-ኃላፊነት የጎደለው የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የሚያስከፍለው ዋጋ!

ሐሳብን በነፃነት መግለጽ የዴሞክራሲ ማዕከላዊ መርህ ነው፡፡ ይህ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ #መብት ደግሞ በይበልጥ እንዲተገበርና እንዲከበር ካደረጉ የታሪክ ክስተቶች፣ የቅርብ ጊዜውና ትልቁ ተጠቃሽ የማኅበራዊ ሚዲያ ነው፡፡ ማኅበራዊ ሚዲያ በባህርይው በማዕከላዊነት የሚደረግ የይዘት ቁጥጥር ባለመኖሩ፣ ተጠቃሚዎች የሚፈልጉትን ጉዳይ ያለማንም ገምጋሚነትና አርታኢነት በመቶ ሺሕዎች ለሚቆጠሩ ተጠቃሚ ተከታዮቻቸው በአነስተኛ ወጪ ያስተላልፋሉ፡፡ ይህም ሳንሱር እንዲጠፋ የሚደረገው ትግልና ክርክር እርባን አልባ እንዲሆን በማድረግ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ እሳቤ፣ ይህን ያህል ይሄዳል ተብሎ ያልተጠበቀበት ደረጃ አድርሶታል፡፡

በዚህም ምክንያት የማኅበራዊ ሚዲያው ለዴሞክራሲ ልምምድ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሚና እንደሚጫወት ዕሙን ነው፡፡ ዛሬ አንድ ግለሰብ በስልኩ የሚያደርገው ግንኙነት እ.ኤ.አ. በ1980ዎቹ ሮናልድ ሬገን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሳሉ ያደርጉት ከነበረው እንደሚልቅ፣ ከ20 ዓመታት በፊት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ቢል ክሊንተን ያገኙት ከነበረው መረጃ የበለጠ አንድ የ13 ዓመት ታዳጊ በስልኩ እንደሚያገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ መረጃ ኃይል ነውና በዚህ ዘመን በቀላሉ የሚገኝ መረጃ ለዴሞክራሲ ልምምድ ብሎም በመረጃ ላይ የተመረኮዘ ውሳኔ ለመስጠት ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡ ከመሪዎቹ የሚገዳደር መረጃ እጁ ጫፍ ላይ የያዘ ዜጋ የመንግሥትት ተጠያቂነት እንዲኖር ለማድረግ ይችላልና፡፡ ከአንድ የዓለም ጫፍ የተከሰተን ጉዳይ  ማግኘትና መተንተን፣ ከዚያም ለውሳኔ መዘጋጀት ከኢንተርኔት ዘመን አስቀድሞ የደኅንነት ተቋማት ተግባር ነበር፡፡ አሁን ግን ከደኅንነት ተቋማት በማይተናነስ ደረጃ ማንኛውም ዜጋ መረጃ አለው፡፡ ይህም መንግሥት የሚወስዳቸውን ዕርምጃዎች እየተከታተሉ ለምን? እንዴት? ለማን ተወሰኑ? በሚሉ ጥያቄዎች ማረምና ተጠያቂነትን ማምጣት ይቻላል፡፡

ይሁንና በ1980ዎቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ሬገንና ከ20 ዓመታት በፊት በተመሳሳይ ሥልጣን ላይ የነበሩት ክሊንተን ያገኟቸው የነበሩ መረጃዎች፣ አሁን ላይ ማንም ከሚያገኛቸው መረጃዎች የሚለዩበት አንድ ነጥብ አለ፣ ተዓማኒነት፡፡ ፕሬዚዳንቶቹ ለሚያስተላልፏዋቸው ውሳኔዎች እንዲረዷቸው መረጃዎቹን ከታማኝ ምንጮች ያገኛሉ፡፡ ለመተንተን ይረዳቸውም ዘንድ ከባለሙያዎች ጋር ይነጋገራሉ፡፡ ነገር ግን አሁን ላይ ከስልኮቻችን፣ በተለይም ከማኅበራዊ ሚዲያ የምናገኛቸው መረጃዎች ተዓማኒነታቸው አናሳ በመሆኑ የሚተላለፉ ውሳኔዎች አደገኛ እንዲሆኑ ያደርጋሉ፡፡

ለዚህ የቅርብ ጊዜ ማሳያ የሚሆነው በማይናማር (በርማ) በሮሂንጂያ የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የተፈጸመው #ግድያ ነው፡፡ በዚህች የደቡብ ምሥራቅ እስያ አገር የሚኖሩና እንደ አገሪቱ ዜጎች የማይቆጠሩት የሮሂንጊያ ማኅበረሰብ እ.ኤ.አ. በ2016 በአገሪቱ ወታደሮች በተፈጸመባቸው ጥቃት ከአሥር ሺሕ በላይ ሰዎች ሲሞቱባቸው፣ ከ700 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ለመሰደድ በቅተዋል፡፡ በዚህች አብዛኛው ማኅበረሰብ #ዜናም ሆነ ተያያዥ መረጃዎችን ከማኅበራዊ ገጾች በተለይም #ከፌስቡክ እንደሚያገኝ በሚገለጽባት አገር፣ በሮሂንጂያ ማኅበረሰብ ላይ የተፈጸመው በደል ‹በዓለማችን እጅግ በጣም የተጨፈጨፉ ሰዎች› በመባል እንዲታወቅ ያደረገ ጥፋት እንዲፈጸም ያደረገው #በፊስቡክ የሚለቀቅ መረጃ ነበር፡፡

በማይናማር የቡድሂስት መነኩሴ የሆኑት #አሺን_ዊራቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የፌስቡክ ተከታይ ያላቸው ሲሆኑ፣ ይኼንን የተከታዮቻቸውን መብዛት ለበጎ ሳይሆን የውሸት መረጃዎችን በማሠራጨት ለበርካቶች #ሞት መንስዔ ሆነዋል፡፡ እኚህ የማይናማር ቢን ላዲን በመባል የተሰየሙት መነኩሴ ለተከታዮቻቸው ሙስሊም የሆነ አንድ ባለድርጅት አሠሪ፣ የቡድሂስት እምነት ተከታይ የሆነችን ሴት ደፍሯል የሚሉ የሐሰት ማስረጃ ቢያስራጩም ተጠያቂ አልሆኑም ነበር፡፡ ፌስቡክም በተደጋጋሚ ሪፖርት ቢደረግለትም እ.ኤ.አ. እስከ 2018 ድረስ ዕርምጃ ባለመውሰዱ ከፍተኛ ጥፋት እንዲፈጸም ምክንያት ሆኗል፡፡

በዚህ የማኅበራዊ ሚዲያዎች በተንሰራፉበት ዓለም እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በማደግ ላይ ያሉና አብዛኛው ኅብረተሰብ ያልተማረ በሆነባቸው አገሮች፣ የማይናማር ዕጣ ፈንታ ሊደገምባቸው እንደማይችል ማረጋገጫ እንደሌለ ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ፡፡ ይህ በተለይ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ፈር ካልተበጀለት #አጥፊነቱ ሊከፋ ይችላልም ይላሉ፡፡
.
.
ክፍል ሁለት 6:00 ላይ🔄

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጀማል አስክሬን እንዲሟሟ ተደርጓል‼️

ጋዜጠኛ #ጀማል_ካሾጊ ከተገደለ በኋላ አስከሬኑ ተቆራርጦ #እንዲሟሟ ተደርጓል አሉ የፕሬዚዳንት #ኤርዶሃን ኣማካሪ።

የአሁኑ የአማካሪው መግለጫ “የጋዜጠኛው አስከሬን በአሲድ እንዲጠፋ ተደርጓል መባሉን ለማጣራት ምርመራ እየተካሄደ ነው” በማለት
አንድ ከፍተኛ የቱርክ ባለስልጣን ለዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ የሰጡትን መረጃ እውነትነት #ያረጋግጣል ተብሏል።

አማካሪው ያሲን አክታይ ቱርክ ውስጥ ለሚታተመው ሁርየት የተባለ ጋዜጣ እንደተናገሩት የካሾጊ አስከሬን ተቆራርጦ ብቻ ሳይሆን ሟሙቶ እንዲወገድ መደረጉን ነው ማወቅ የቻልነው ብለዋል።

እጃችን ላይ እንደደረሰው መረጃ ከሆነ ገዳዮቹ አስከሬኑን የቆራረጡት በቀላሉ ለማሟሟት እንዲመቻቸው ነው ብለዋል አማካሪው።

የቱርክ ዋና ዐቃቢ ህግ ባለፈው ረቡዕ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት መግለጫ ካሾጊ ኢስታንቡል ወደሚገኘው የሳዑዲ ቆንስላ እንደገባ በተደራጀ ሁኔታ #ግድያ ተፈጽሞበት አስከሬኑም ተቆራርጦ እንዲወገድ መደረጉን አረጋግጠዋል።

“አንድም የሰውነቱ አካል እንዳይገኝ አልመው ያደረጉት ነገር ነው። ንጹህ ሰው መግደል አንድ ወንጀል ሆኖ ሳለ አስከሬኑ እንዲጠፋ የተደረገበት መንገድ ደግሞ ሌላ አስከፊ ወንጀል ነው ብለዋል ያሲን አክታይ።

ምንጭ፦ ARTS TV WORLD
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሼክ አላሙዲን ነገር⁉️

"ቢቢሲ ዛሬ በለቀቀው ዘጋቢ ፊልም እነ ሼክ አላሙዲንን ከሳዑዲ ልዑላውያን ጋር ደምሮ ያሳረዉ የሳዑዲ መንግስት በታሳሪዎቹ ላይ የከፋ #ድብደባ እና #ማሰቃየት እንዲሁም #ግድያ እየፈፀመ ነዉ ሲል ዘጋቢ ፊልም ሰርቷል። ከሟቾች ዉስጥ ጄኔራል አሊ አልካታኒ አንዱ ናቸዉ። ሞሐመድ ቢን ሰልማን የሚባለዉ እና ፖለቲካዊ አመለካከቱ ሊበራል ነዉ ተብሎ ሲወደስ የነበረዉ በቅጽል ስሙ ኤም ቢ ኤስ የተባለዉ የሳዑዲ አልጋወራሽ በእርሱ ትዕዛዝ የታሰሩ ባለሀብቶችና ንጉሣውያን ቤተሰቦች በድብደባ ምክንያት የደረሰባቸውን ጉዳት በሌላ ሆስፒታል እንዳይታከሙ በሪትዝ ሆቴል ተንቀሳቃሽ ሆስፒታል ከፍቷል። ይህ ዘገባ የተሰራዉ በቅርቡ ቱርክ በሚገኘዉ በሳዑዲ አረቢያ ቆንስላ
በጋዜጠኛ #ጀማል_ካሾጊ ላይ የተፈፀመዉን ግድያ ጋር ተንተርሶ ነዉ። አላሙዲን ምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? የኢትዮጵያ መንግስት ያለዉ መረጃ
ምንድነዉ? ከአላሙዲን ጋር ሲበሉ ሲጠጡ ሲያተርፉ ሲነግዱ ያዙን ልቀቁን ሲሉ የነበሩ የት አሉ ? አላሙዲ ታሰረ አልታሰረ ጉዳያቸዉ አይደለም። ነገር ግን በእርሳቸዉ እርዳታ ህክምና ላገኙ እርዳታ ለተደረገላቸው ጥቂት ኢትዮጵያውያን ቤት ተሰርቶ ለተሰጣቸዉ ድሆች ስንል የመሐመድ ቢን ሰልማን ሰለባ እንዲሆኑ አንሻም። በሙስና የሚጠየቁ ከሆነም በፍርድ ቤት በአግባቡ መሆን አለበት ከጥላሁን ገሠሠ እስከ ካሚላት ላደረጉት በጎ ምግባር እናመሰግናለን።"

©Hailemelekot Agizew
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ኦነግ በሬ እያረደ በተቀበለው ህዝብ ላይ ዘረፋና #ግድያ ፈጽሟል” ጄኔራል #ብርሃኑ_ጁላ

• ሠራዊቱ ከትግራይ እንዳይወጣ የሞከሩት ህዝቡና የክልሉ መንግሥት አይደሉም

• መከላከያን ከኃላፊነቱ ውጪ የክልሎችና የፖለቲካ ሥራን የማሠራት ፍላጎት አለ

• በሠራዊቱ ላይ ጥላቻ በመንዛት አገርን ለማፍረስ የሚሠሩ አሉ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና የኢትዮጵያ መንግሥት #በሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ ተከታታይ #ግድያ የመፈጸም #ዕቅድ እንደነበር አስታውቋል።

🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ለባለስልጣናቱ #ግድያ አዴፓ ራሱን ተጠያቂ እንዲያደርግ ህወሐት ጠየቀ። ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የህወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬ ተጠናቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/TPLF-07-10

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የ32 ዓመቷ ወጣት በፖሊስ ጥይት ከጀርባዋ ተመታ ህይወቷ ያለፈ ሲሆን ፖሊስ የድርጊቱ ፈፃሚ በቁጥጥር ስር ይገኛል ብሏል። በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ነዋሪ የሆነች የ32 አመት ወጣት ከፖሊስ አባል በተተኮሰ ጥይት ተመታ ህይወቷ አልፏል። በፖሊስ አባል ጥቃት የደረሰባት ኢየሩሳሌም አስራት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ስትሆን ጥቃቱ ካጋጠማት በኋላ በጥቁር አንበሳ…
#AddisAbaba

#ሕዳር

* ባለፈው ሕዳር 13/2016 በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ነዋሪ የሆነች የ32 አመት ወጣት እየሩሳሌም አስራት ከፖሊስ አባል በተተኮሰ ጥይት ከጀርባዋ ተመታ ህይወቷ ማለፉ መነገሩ አይዘነጋም። ይህች ወጣት በፖሊስ አባል ጥቃት ካጋጠማት በኋላ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና እና ሕክምና ክትትል ሲደረግላት የነበረ ቢሆንም ህይወቷ ሊተርፍ ግን አልቻለም።

* አሁን ደግሞ ዶ/ር እስራኤል ጥላሁን የተባለ የጤና ባለሞያ የፖሊስ አባል ነው በተባለ ግለሰብ ሕዳር 28 ቀን 2016 በተተኮሰ ጥይት ህይወቱን እንዳጣ ተሰምቷል። ይህ ወጣት የጤና ባለሞያ " ስፖኪዮ ገጭቶ አመለጠ " በሚል አንድ የፖሊስ አባል " ጎማውን መትቼ ለማስቆም " ነው ብሎ በታጠቀው መሳሪያ ዶክተሩ ላይ በመተኮስ #ግድያ እንደፈፀመ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ተናግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ታህሳስ 7 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት አዲስ አበባ ቦሌ ኤድና ሞል አካባቢ አንድ ሰው በጥይት ተመቶ ተገድሏል። ድርጊቱ የተፈፀመው ቦሌ ከኤድናሞል ወረድ ብሎ በሚገኝ አንድ የመዝናኛ ስፍራ አካባቢ ነው። ምሽት አራት ሰዓት ገደማ ሟች #አባተ_አበበ በአንድ #መሳሪያ_በታጠቀ ግለሰብ በጥይት ተመቶ መገደሉ ታውቋል። አባተ አበበ ተወልዶ ባደገበት ፣ በሚኖርበት  አካባቢ እንዲሁም ደግሞ በስራ…
#ግድያ #የፖሊስ_ምላሽ

" ፖሊስ ሥራውን እየሰራ ነው። ግልጽ ማድረግ በሚገባን ሰዓት ላይ ግልጽ እናደርጋለን " - ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ

አቶ አባተ አበበ የተባሉ ግለሰብ ታህሳስ 7 ቀን 2016 ዓ/ም አዲስ አበባ ቦሌ ኤድናሞል አካባቢ ዝቅ ብሎ በሚገኝ መዝናኛ 'በጥይት ተመትቶ ተገደለ' መባሉን በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጠይቋል።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " ፖሊስ ሥራ እየሰራ ነው። ግልጽ ማድረግ በሚገባን ሰዓት ላይ ግልጽ እናደርጋለን " ብለዋል።

ኮማንደሩ በሰጡት ማብራሪያ፣ " ሰው ወዲያው እንደሞተ ወደ ሚዲያ መውጣት አለበት ? " ሲሉ ጠይቀው፣ " በጣም አሁን እኮ አንዳንድ ፀሐፊዎች እንዳውም ፎቶ ግራፉን ሁሉ ' ተጠርጣሪ ይሄ ነው ' እያሉ እየለጠፉ ነው። ይሄ ኢቲካል እኮ አይደለም " ብለዋል።

አክለውም፣ " ይሄን ሰውየ እኮ ፍርድ ቤት ነው 'ጥፋተኛ ነህ' ብሎ ጥፋተኛ መሆኑን የሚገልጽለት እንጂ ግለሰብ እየተነሳ 'ጥፋተኛ ነው' ብሎ ፎቶ እየለጠፉ ትክክል እኮ አይደለም " ብለዋል።

ምክትል ኮማንደር ማርቆስ የጉዳዩን አሳሳቢነት ሲያስረዱም ፦

- " ፍርድ ቤት እኮ ጥፋተኛ እስከሚለው እኮ ነፃ ሆኖ የመቆጠር መብት አለው። "

- " ከሕግ አንጻር እኮ ማዬት መቻል አለብን። ይሄ ነገር #የሚያስከትለውን ነገር ማየት መቻል አለበት። "

- " ቤተሰቦቹን ማሰብ መቻል አለበት። አሁን እነዚህ ሰዎች #ጎረቤታሞች ቢሆኑ እኮ የዛ ቤተሰብ መጥቶ እዚህ ልጅ ላይ እርምጃ ሊወስድ ነው። እንዴት እንደዚህ አይታሰብም ? ብቻ በአጠቃላይ በጣም ቀውሷል ሚዲያው ፤ ከባድ ቀውስ ላይ ነው ያለነው " ሲሉ አስረድተዋል።

የሟቹን ጉዳይ በተመለከተ ፖሊስ ያገኘው መረጃ እና የጀመረው ምርመራ እንዳለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው ኮማንደር ማርቆስ፣ " ፖሊስ ሥራ እየሰራ ነው። ግልጽ ማድረግ በሚገባን ሰዓት ላይ ግልጽ እናደርጋለን። አሁን ሥራ እየተሰራ ነው " ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

የአባተ አበበን ጉዳይ በተመለከተ እየተከታተልን የምናቀርብ ይሆናል።

ይህን መረጃ አዘጋጅቶ የላከው የአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

" ... አሁንም ቢሆን ለያዥ እና ገናዥ አስቸጋሪ የሆነው የመንግስት አቋም ነው " - መረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር)

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ( #ኦፌኮ ) ሊቀመንበር መረራ ጉዲና (ፕ/ር) በሀገራችን ጉዳይ ላይ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

Q. በተለያዩ ቦታዎች ያለውን የጸጥታው ችግር እንዴት ትገመግሙታላቹ ? መፍትሄውስ ምንድን ነው ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" ብሔራዊ እርቅ እና ብሔራዊ መግባባት የሚባለውን እኮ ከኢህአዴግ መጀመሪያ ዓመት ጀምሮ እስከ 30 ዓመታት ስንጠይቅ ቆይተናል።

አሁንም ቢሆን መልክ አልይዝ እያለ ያስቸገረው / ለያዥና ለገናዥ አስቸጋሪ የሆነው የመንግስት አቋም ነው።

ስልጣንን በMonopoly መያዝ ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ እንደ ባህል ተይዟል። አሁንም ቀጥሏል። የኢትዮጵያ መሪዎች ከዛ አልወጣ አሉ። ውጤቱ ደግሞ የታወቀ ነው። 

ደርግ ወጣቶችን ጨፍልቆ ነው የሄደው ፤ ኢህአዴግ ለ27 ዓመታት አገሪቱን ቀላል ያልሆነ ቀውስ ውስጥ ከቷት ነው ጡረታ የወጣው ፤ ብልጽግናም በባሰ መንገድ ይህንኑ ሁኔታ እየተከተለ ነው።

የኢትዮጵያ ጸጥታ ሁኔታ ' ከድጡ ወደ ማጡ ' ተብሎ የሚገለጽበት ደረጃ ላይ ነው።  መፍትሄው ቁጭ ብሎ መወያዬት ነው።

ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን #ከመገዳደል ፓለቲካ ወደ #መደራደር ፓለቲካ ማምጣት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። "

Q. በየጊዜው የንጹሐን ሕይወት በግፍ እየተቀጠፈ ነው። ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ መስራትም የሞት ጊዜን እንደማፋጠን ሆኖ ይስተዋላል።  መፍትሄ እንዲመጣ ምን እየሰራችሁ ነው ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና፦

" ለ30 ይሁን ለ6ቱ ዓመታት በዴሞክራሲ የሚደረገው ለውጥ በተለይ ዴሞክራሲያዊ ምህዳርን እንዲያሰፉ ደጋግመን ስንጠይቅ ነበር።

አሁንም ያን መጠየቅ ቀጥለናል። ሜዳው / ምህዳሩ ግን በተቃራኒው እየጠበበ፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎች በአገሪቷ ላይ እየተንሰራፉ የመጡበት ሁኔታ ነው ያለው።

ምህዳሩ ካልሰፋ፣ ለዴሞክራሲ የሚደረገው ትግል መልክ ካልያዘ፣ ወጣቱንም ወደ ጫካ እየተገፋ የትም አያደርሰንም። "

Q. ከመንግስት የሚደርስባችሁ ጫና ምንድን ነው ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" ከኦነግ ቀጥሎ ከፍተኛ ጫና ያለበት የእኛ ፓርቲ ነው።

ለምሳሌ የዛሬ 4 ዓመት ከ200 በላይ ቢሮዎች ነበሩን፤ አሁን ያሉን 3 ብቻ ናቸው። አባሎቻችን #ግድያ እና #እስራት ይፈጸምባቸዋል። 

ለምሳሌ ፦ የምሥራቅ ወለጋ የቢሮ ኃላፊ ከተወሰደ የት እንደገባ አላወቅንም 2 ዓመታት ሊሆነው ነው።

የምሥራቅ ሸዋ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላችን ለዚያውም የዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ታስሯል።

አምቦ 4 ወጣቶች ታስረው 2 ሳምንታት ሆኗቸዋል። "

Q. #ብልሹ_አሰራርና #ሙስናን በተመለከተ ኢትዮጵያ በምን ደረጃ ትገኛለች ? መፍትሄውስ ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" በኢትዮጵያ ታሪክ የተለዬ/የከፋ የሙስና ደረጃ ነው ያለው።

መንግስትና ተቋማቱ የአንድ ቡድን ጉዳይ አስፈጻሚ ሆነው ሲዋቀሩ እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ይፈጠራሉ።

አሁንም መንግስት ተጠያቂነት ባለው መንገድ እንደገና ካልተዋቀረ በስተቀር፣ ከዚህ በሽታ የምንወጣበት መንገድ ያለ አይመስለኝም።

Q. የኑሮ ውድነቱ ሕዝቡን በእጅጉ አማሮታል። ፓርቲያችሁ ለመንግስት ያላችሁ ግምገማን ቢያጋሩ ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" ዜጎች እጅግ አስቸጋሪ ፣ ፈታኝ ሁኔታ ላይ ደርሰዋል።

መንግስት አስፈላጊ እርምጃ እንዲወስድ በተደጋጋሚ ተይቀናል።

መንግስት ግን ጆሮ ያለው አይመስልም። ችግሩ ግን እጅግ በጣም ፈታኝ ነው። "

Q. በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ተመራጭ ሆኖ ለመቅረብ ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" የፓለቲካ ምህዳር ለማግኘት የመገዳደል ፓለቲካው እንዲቆም እየጠየቅን ነው። ምርጫ ከዚያ በኋላ የሚመጣ ነው።

ለነፃና ፍትሃዊ ምርጫ አስቻይ የሆነ ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም።

ትልልቆቹ አማራና ኦሮሚያ ክልሎች ጦርነት ውስጥ ናቸው። በዚህ ሁኔታ ምን አይነት ምርጫ እንደሚካሄ የምናየው ነው። መደራጀቱን ቀጥለናል። "

#TikvahEthiopiaFamilyAA

#ቲክቫህኢትዮጵያ
#የፖለቲካ_ፓርቲዎች_ምን_ይላሉ?

@tikvahethiopia