TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለገጣፎ ለገዳዲ‼️

(አቶ አዲሱ አረጋ)

ሰሞኑን በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ ህግን ለማስከበር በተደረገ እንቅስቃሴ በመንግስት ይዞታ ስር ባሉ በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ፣ በአረንጓዴ ቦታዎች፣ በወንዝ ዳር እና የመሰረተ ልማት መገንቢያ ቦታዎች ላይ የተገነቡ እና ከከተማዉ የመሬት አጠቃቃም ፕላን ጋር የሚቃረኑ 347 ቤቶች እና በአጥር የተከለሉ ቦታዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ይታወቃል። የተወሰደዉን እርምጃ ተከትሎ ሰፊ #ቅሬታ በመቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

ህገ ወጥነት መከላከል #ለድርድር የማይቀርብ ጉዳይ ባይሆንም በአፈጻጸሙ ሂደት የተፈጠሩ #ግድፈቶች እና #ስህተቶች ካሉ ለይቶ ማረም አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን ጉዳይ የሚያጣራ አንድ ግብረ ሀይል ተደራጅቶ ወደ አካባቢዉ እንዲሰማራ ክቡር ፕረዚዳንት #ለማ_መገርሳ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡ በዚህም መሰረት ግብረሃይሉ በጥቂት ቀናት ዉስጥ ወደማጣራት ስራ የሚገባ ይሆናል፡፡ ግብረሃይሉ አጣርቶ በሚያቀርበዉ ሪፖርት መሰረትህገወጥ ግንባታን በማፍረስ ሂደት የተፈጸሙ ስህተቶች ካሉ ህግን ተከትለዉ የሚታረሙ ይሆናል።

ህገ ወጥ ግንባታ የፈረሰባቸዉ የደሃ ደሃ የሆኑ ወገኖቻችን ያለ #መጠለያ እንዳይቀሩ ግብረሃይሉ አጣርቶ በሚያቀርበዉ መሰረት ህግና ስርኣትን በተከተለ መንገድ በአጭር ጊዜ ዉስጥ መፍትሄ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡

የተወሰደዉ ዕርምጃ #አንድ_ብሄር ላይ ያተኮረ ጥቃት አስመስሎ በማህበራዊ ሚዲያ እና በሌሎች ሚዲያዎች እየቀረበ ያለዉ ዘገባ #ሀሰት መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

#Addisu_Arega_Kitessa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🏷«ለተማሪዎች ምዝገባ ክፍያ መጠየቃችን #ቅሬታ ፈጥሮብናል» ልጆቻቸውን በመንግሥት ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ ወላጆች

🏷«ክፍያ በሚጠይቁ ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ ይወሰዳል» አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
__________________________________

በአንዳንድ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች መመዝገቢያ እየተባለ የሚጠየቀው ክፍያ ቅር እንዳሰኛቸው ወላጆች ገለጹ። የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በበኩሉ የከተማ አስተዳደሩ ለመንግሥት ትምህርት ቤቶች እና ለተማሪዎች ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልኩ ልዩ ድጋፍ እያደረገ ባለበት ወቅት ለምዝገባ በሚል ገንዘብ የሚሰበስቡ ትምህርት ቤቶች #ሕገወጥ መሆናቸውን አስታውቋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአፕቲትዩድ ውጤታችሁን ከዛሬ ምሽት ጀምሮ መመልከት ትችላላችሁ!

የሃገር አቀፍ ፈተናና ምዘና ኤጀንሲ ተማሪዎች #ቅሬታ ሲቀርብበት የነበረውን የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና የስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ውጤትን ከዛሬ ምሽት ጀምሮ መመልከት እንደሚችሉ አስታወቀ። ኤጀንሲው ከፈተናው የመልስ ቁልፍ ጋር ተያይዞ የነበረው እርማት ተጠናቆ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ በድረ ገጹ እና በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መመልከት ይችላሉ ብሏል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓርዓያ ገብረእግዚአብሄር ከFBC ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ የፈተናው ኮድ 21 እና 22 ችግር እንደነበረባቸው ጠቅሰዋል። ዳይሬክተሩ ቀደም ሲል በአጭር የፅሁፍ መልዕክት እና በድረ ገጽ መለቀቁን ጠቅሰው፥ የተለቀቀው ውጤት ያልተስተካከለው እንደነበር ገልጸዋል።

ለዚህም ቀደም ሲል በአጭር የፅሁፍ መልዕክት የተለቀቀውን መረጃ ማጥፋት የሌላ አካል ሃላፊነት መሆኑንም አንስተዋል፡፡ ከፈተናው ጋር ተያይዞ ለኤጀንሲው 10 ሺህ ያህል ቅሬታዎች መቅረባቸውን ያነሱት ዳይሬክተሩ፥ አሁን ላይም ጉዳዩን የሚከታተል ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ይሁን እንጅ እስካሁን በሌሎች የትምህርት በአይነቶች ችግሮች ያለመገኘታቸውን አስረድተዋል። የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እርማት ሃምሌ 20 ቀን 2011 መጠናቀቁን የተናገሩት ዳይሬክተሩ ፈተናው ይፋ እስከሚደረግ ድረስ ባሉት ጊዜያትም መሰል ችግሮች እንዳይከሰቱ የማጣራት ስራ ሲሰራ እንደነበረም አስታውሰዋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba : የላዳ ታክሲዎችን በአዲስ የመተካት ስራ በታያዘው ዓመት አጋማሽ ድረስ ለማጠናቀቅ እንደታሰበ የአ/አ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል። ረጅም አመታት በከተማው አገልግሎት የሰጡ ላዳ ታክሲዎች አሁን ላይ እርጅና ተጫጭኗቸው በገበያው ውስጥ ከመጡ ሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎቶች ጋር መወዳደር እየተሳናቸው ነው። ባለንብረቶቹ ችግሩን ለከተማው አስተዳደር በማሳወቅ የመፍትሄ ሃሳቦች ሲቀርቡ መቆየቱንም…
#ቅሬታ

በአዲስ አበባ ከተማ ፤ የላዳ ታክሲዎቻቸው በአዲስ እንደሚቀየርላቸው ቃል የተገባላቸው አሽከርካሪዎች እስከ አሁን ምላሽ አላገኙም።

መንግሥት ከኤል አውቶ መኪና አስመጭ ድርጅት ጋር በመነጋገር የላዳ ታክሲዎች በአዲስ እንደሚቀየርላቸው ተነግሯቸው የነበረ ቢሆንም፣ ምላሽ ማግኘት እንዳልቻሉ የላዳ ታክሲ አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች ቅሬታ አሰምተዋል።

የላዳ አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች 30 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ ከባንክ ጋር በማገናኘት ክፍያውን ከፈጸሙ በኋላ አዲስ ታክሲ እንደሚሰጣቸው እና 70 በመቶውን በየወሩ እየሠሩ ከሚያገኙት ገቢ ላይ እንደሚከፍሉ ተነግሯቸው ነበር። ሆኖም የታዘዙትን ክፍያ ከመፈፀም ባለፈ ተግባራዊ የተደረገላቸው ነገር የለም።

አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኤል አውቶ መኪና አስመጪ ድርጅት ሰራተኛ፤ ድርጅቱ ለመቀየር የተስማማቸውን መኪኖች ለማስመጣት ሥራ የጀመረ ቢሆንም፣ ሥራ ከጀመረ በኋላ አዲስ መመሪያ እና ለውጥ በመውጣቱ በመንግሥት በኩል ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ የተፈቀዱ መኪኖች ታግደው ከወደብ ማውጣት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

ችግሩን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር እፀገነት አበበ በበከላቸው ቢሮው የላዳ ታክሲ አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች እና ታክሲ የሚያቀርቡ ድርጅቶችን የሚስማሙበትን ሂደት የመፍጠር ኃላፊነት ተወጥቷል ብለዋል።

ይህም አሽከርካሪዎች 30 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ እንዲፈፅሙ እና 70 በመቶ እየሠሩ የሚከፍሉበትን ሂደት ተነጋግረው እንዲስማሙ የሚያስችል እድል እንደፈጠረ እና መስማማት ላይ መድረሳቸውን ኃላፊዋ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ (https://addismaleda.com/archives/29249)

@tikvahethiopia
#Update

የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ዶክተር ይልቃል ከፋለ ፤ የአማራ ልዩ ኃይልን በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን የተወሰነ ውሳኔ የለም አሉ።

ይህን ያሉት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው።

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ምን አሉ ?

- በሀገር ደረጃ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ ልዩ ኃይሎችን በፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ለማደራጀት ተወስኖ ወደ ትግበራ ተገብቷል።

- ውሳኔው በፌዴራል መንግሥት እና በክልል መንግሥታት ስምምነት የተወሰነ ሲሆን በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ ይደረጋል።

- በአማራ ክልል ውሳኔውን ለመተግበር እየተሠራ ነው። ይህንን በተመለከተ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር ተወይይተናል።

- በአፈጻጸም ላይ በታየ ክፍተት እና በተነዛው ፕሮፖጋንዳ ችግሮች ተከስተዋል። ችግር እንኳን ቢኖር ተወያይቶ መፍታት ይቻላል።

- አብዛኛው የልዩ ኃይል አባል ውይይቱን አጠናቆ ውሳኔውን በካምፕ ሆኖ እየተጠባበቀ ነው።

- ልዩ ኃይሉ ትጥቅ የሚፈታና የሚበተን አይደለም ፤ በላቀ አደረጃጃት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የሚያስችል ነው።

- ልዩ ኃይሉ ዓላማውን ተገንዝቦ ለበለጠ ተልእኮ ሊዘጋጅ ይገባል።

- የአማራ ሕዝብ በሁኔታው #ቅሬታ ውስጥ ገብቷል።ቅሬታው የመነጨው በተሟላ መንገድ ለሕዝቡ መረጃ ባለመድረሱ ነው።

- አደረጃጀቱ የሚደገፍ፣ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው የሀገርን አንድነት የሚያረጋግጥ ነው።

- አደረጃጀቱ የአማራን ክልል በተለየ መንገድ የሚጎዳ አይደለም።

- የአማራ ክልልን ልዩ ኃይል በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን የታለመ ዓላማ የለም።

- በተፈጠረ የመረጃ ክፍተት በአንዳንድ ከተሞች የሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴ፣ የአድማ ጥሪ እና የሰዎች እና የተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴን የመገደብ አዝማሚያዎች እያታዩ ናቸው። አላስፈላጊ አካሄዶች አውዳሚ እና አክሳሪ እንጂ አትራፊ አይደሉም።

- የአማራ ክልል በጦርነት የከረመ ክልል ነው ፤ በጦርነቱ ምክንያት ሕዝቡ ተጎሳቁሏል፣ በጦርነቱ ምክንያት የተጎዳው ኅብረተሰብ እና መሠረተ ልማት ገና ማገገም አልቻለም ፤ ከአንደኛው ችግር ሳናገግም ወደ ሌላ ችግር መሸጋገር ሕዝቡን መጉዳት ነው።

- በመወያየት አላስፈላጊ ጉዳዮችን ማስቆም ይቻላል ፤ ሁሉም አውዳሚ የሆነውን ጉዳይ መከላከል ይገባዋል።

- ግጭት እንዳይፈጠር ወጣቶች እና የሃይማኖት አባቶች የሚመሰገን ሥራ እየሠሩ ናቸው።

- የአማራ ክልል ሕዝብ ጉዳዩን በውል በማጤን፣ በመመካከር እና ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት አስቀድሞ በማሰብ ማስከን ይገባል።

- የአማራ ልዩ ኃይል በተለየ መንገድ የሚጎዳ ውሳኔ አልተወሰነም፣ ወጥና ሀገራዊ ውሳኔ ነው የተደረገው፣ በሁሉም ክልል የሚፈጸም ነው፣ ውሳኔው ለሀገር ግንባታ ታላቅ አስተዋጽዖ አለው።

- ከወቅታዊ ጉዳይ አንጻር የሚነሳው ጥያቄ ትክክል ቢሆንም አፈጻጸሙ ለሀገር የሚጠቅም መሆኑን መገንዘብ ይገባል።

- ከካምፕ የወጡ የልዩ ኃይል አባላት እንዲመለሱ ማድረግ ይገባል።

- የአማራ ሕዝብ ጉዳዩን በሰከነ መንገድ ማየት አለበት ፤ ችግሩ ዳር ወጥቶ ግጭት እንዳይከሰት እያደረጉ ላሉ አካላት ምስጋና ይገባል።

- የልዩ ኃይል አባላት ትጥቅ አትፈቱም፣ የምትበተኑበት ነገር የለም፣ ወደ ላቀ ተልእኮ ነው የምትሸጋገሩት።

- በመደማመጥ ችግሮቻችን እንፈታለን፣ የአማራን ጥያቄዎች እናስመልሳለን።

#AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የመውጫ ፈተና ውጤት እየታየ ይገኛል።

በ2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተመራቂ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከእሁድ ረፋድ ጀምሮ እየተመለከቱ ይገኛሉ።

ውጤቱ መታየት ከጀመረበት ሰዓት አንስቶ ለረጅም ሰዓታት በመንግስት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች ብቻ ውጤታቸውን ማየት የቻሉ ሲሆን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ደግሞ #ከምሽት አንስቶ ውጤታቸውን ማየት ጀምረዋል።

ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹ " ውጤት መመልከቻው ድረገፅ ላይ ገብተው username ሲያስገቡ የሚያገኙት ምላሽ የተቋማቸው " የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ አልተደረገም " የሚል እንዲሁም የአንዳንዶቹ " ያስገቡት ስም የማይሰራ " መሆኑን የሚገልፅ ነው።

ውጤታቸውን የተመለከቱ በርካታ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ደግሞ 50 እና ከዚያ በላይ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ቢሆንም " fail / ወድቀዋል " የሚል ምላሽ እያገኙ መሆኑን በመግላፅ ትምህርት ሚኒስቴር በሲስተሙ ላይ ያለውን ችግር #እንዲያስተካክል ጠይቀዋል።

ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ፤ የመውጫ ፈተና የተቀመጡት 72,203 ተማሪዎች ሲሆኑ 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተው ያለፉት 12,422 ተማሪዎች ወይም 17.2 በመቶ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

በሌላ በኩል ፤ በመውጫ ፈተና አመርቂ ውጤት ካልተመዘገበባቸው / እጅግ በርካታ ተማሪዎች ከወደቁባቸው የትምህርት ክፍሎች አንዱ የ " Accounting and Finance " ሲሆን በፈተናው ላይ  ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች የፈተናው ምዘና ድጋሚ እንዲፈተሽ ጠይቀዋል።

በተመሳሳይ የ " Information Technology " ተማሪዎችም መሰል አቤቱታ እንዳላቸው ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ የተሰጠው ፈተናው ከነበረው ዝግጅት ጋር የሚራራቅ እንዲሁም ደግሞ ከ ተሰጣቸው ' ብሉለሪንት ' ጋር የማይቀራረብ በመሆኑ ሚኒስቴሩ እንዲያይላቸው አቤቱታ አቅርበዋል።

ከዚህ ቀደም የ ' መካኒካል ምህንድስና ' ተመራቂ ተማሪዎች ከፈተናው ጋር በተያያዘ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ ማቅረባቸው የሚዘነጋ አይደለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ወይም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ተማሪዎችን #ቅሬታ የሚያስተናግዱበት መንገድ ካለ ጠይቆ የሚያሳውቅ ይሆናል።

#ማስታወሻ ፦ የመውጫ ፈተና ውጤት የሚታየው በ result.ethernet.edu.et ላይ Username በማስገባት ነው።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የተሽከርካሪዎች_ጨረታ_ጉምሩክ_ኮሚሽን_አዳማ_.pdf
ውዝግብ የፈጠረው የበርካታ ተሽከርካሪዎች ጨረታ !

" ' የጉምሩክ ኮሚሽን ' የገንዘብ ሚኒስቴርን ውሳኔ በመጣስ 237 መኪኖችን ለሐራጅ አወጣብን " - ከሰደት ተመላሾችና 10 የሚደርሱ የአገር ውስጥ አስመጪዎች

" በግልፅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች ህጋዊ ስርዓቱን በአግባቡ በተከተለ መልኩ ነው። ' ህጋዊ ስርዓቱን አልተከተለም ' በሚል የሚሰራጩት መረጃዎች ሀሰተኛ ናቸው ፤ #ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን በህግ አግባብ እንጠይቃለን " - ጉምሩክ ኮሚሽን

ከሰሞኑን የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ፅ/ቤት ያወጣው የበርካታ ተሽከርካሪዎች ጨረታ ውዝግብ የፈጠረ ሆኗል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ቅሬታ አለን ያሉ ከሰደት ተመላሾችና የአገር ውስጥ አስመጪዎች ፤ " ጉምሩክ ኮሚሽን የገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔን በመጣስ 237 ተሽከርካሪዎች ለሐራጅ አወጣብን " በሚል ከሰዋል።

ጉምሩክ ኮሚሽን በበኩሉ ፤ " ምንም አይነት የህግ ጥሰት አልፈተፈፀም ህጉን እና አሰራሩን በተከተለ መልኩ ነው ተሽከርካሪዎቹ ለጨረታ የቀረቡት " ሲል አሳውቋል።

ያንብቡ 👇 https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-11-24

@tikvahethiopia
#ቅሬታ #ምላሽ

“ ... ባለ 3 መኝታ ቤት ዕድለኞች ተብለው የወጡት ተመዝጋቢዎች አብዛኛዎቹ የባለ 2 መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች ናቸው ” - የኪ ሃውሲንግ የቤት ዕጣ ቆጠቢ

“ ... ጥቂት ቁጥሮች ባለ 2 ብለን እኛ ሲስተም ላይ ጽፈናቸው ‘አይ እኔ የተመዘገብኩት ባለ 3 ነው’ ሊሉ ይችላሉ” - አቶ ቸርነት መንግስቱ (ከድርጅቱ)

ከሰሞኑን " Key Housing Finance Solution " የተሰኘ ተቋም የቤት ባለቤት ለመሆን ሲቆጥቡ ለነበሩ ሰዎች ዕጣ አውጥቶ ነበር።

ከተለያዩ ሴክተሮች በሚገኙ ልምድ ባላቸው አካላት ተዋቅሯል የተባለው " Key Housing Finance Solution " ከ15,000 በላይ ለሆኑ የቤት ቆጣቢ ተመዝጋቢዎች መካከል ለ60 ቆጣቢዎች / የቤት ዕድለኞች የመጀመሪያ ዙር ዕጣ አውጥቶላቸዋል።

ድርጅቱ በ77,280 ብር ቅድመ ቁጠባ ሰዎች የቤት ባለቤት የሚሆኑበት ሞዴል ፕሮጀክት እንዳለው በገለጸው እና በተለያዩ መንገዶች ባስተዋወቀው መሰረት ነው ከ15,000 በላይ ቤት ፈላጊ ቆጣቢዎች ውስጥ #ለ60_ቆጣቢዎች / #ባለዕድለኞች ዕጣ ያወጣላቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከ “Key housing Finanance Solution” የቤት ዕጣ ቆጣቢ፣ “ኪ ሃውሲንግን በተመለከተ እጣ አወጣጡ ላይ ስህተቶች የተሰሩ በመሆኑ ማብራሪያና እርማት ብንጠይቅም በሶሻል ሚድያም ሆነ በሌላ ምላሽ ልናገኝ አልቻልንም” የሚል ቅሬታ ደርሶታል።

ከተመዝጋቢዎቹ መካከል አንዷ በሰጡን ቃል፣ “ ባለ 3 መኝታ ቤት ዕድለኛ ተብለው የወጡት ተመዝጋቢዎች አብዛኛዎቹ ባለ 2 ተመዝጋቢዎች ናቸው ” ብለዋል።

አክለውም ፣ “ ለዚሁም ብለን ' አትላስ ' በሚገኘው ዋና ቢሯቸው ማብራሪያ ለማግኘት ከአንዴም ሁለቴ ብንሄድም #በsystem ምክንያት ዕጣ አወጣጡ ላይ ችግር ያለበት መሆኑን ከማመን የዘለለ በቂ ምላሽ አልሰጡንም ” ሲሉ ድርጅቱን ወቅሰዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የቀረቡ ቅሬታዎች በዝርዝር ምን ይላሉ ?

- ዕጣው የደረሳቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ ካደረጉ በኋላ ቼክ በምናደርግበት ጊዜ ልዩነት አለው። 

- ልዩነት የተፈጠረው ባለ 3 ፣ ባለ 2 እና ባለ 1 መኝታ ቤት ነው ያዘጋጁት። ዕጣው ከመውጣቱ በፊት ካለው ዝርዝር ጋር ስናስተያየው ባለ 3 መኝታ ቤት ዕድለኛ ተብለው የወጡት ተመዝጋቢዎች አብኞቹ ባለ 2 መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች ናቸው።

- ከተመዝጋቢዎች ብዛት አንፃር #ባለ_3_መኝታ_ቤት ለ30 ሰዎች (50%)፣ ባለ 2 መኝታ ቤት ለ21 ሰዎች (35%)፣ ባለ 1 መኝታ ቤት ለዘጠኝ ሰዎች (15%) እንደሚወጣ ነበር ዕጣውን ከማውጣታቸው በፊት ሲገልጹ የነበረው።

- ባለ 3 መኝታ #ለ30_ሰዎች ብለው ካሰቡት ውስጥ ለ21 ሰዎች ነው የወጣው። የባለ 2 ደግሞ ለ21 ሰዎች ብለው ከገለጹት ለ29 ሰዎች ነው የወጣው። ባለ 1 መኝታ ቤት ደግሞ ለ9 ሰዎች ብለው ካሰቡት ለ10 ሰዎች ነው የወጣው። ይህ ማለት ይፋ ካደረጉት ፐርሰንቴጂ ጋር ግልፅ የሆነ ልዩነት አለው።

- በተጨማሪም ፤ ዕጣው ከመውጣቱ በፊት የታቀደው ፕላን በፐርሰት 50 በመቶ ባለ 3 መኝታ ቤት ፣ 35 በመቶ ባለ 2 መኝታ ቤት እንዲሁም ፣ 15 በመቶ ለባለ 1 መኝታ ቤት ብለው ነበር ያስቀመጡት። አክቹአል ሲወጣ ግን ወደ 35፣ 48፣ እና 17 ፐርሰቶች ተቀያይሯል።

- ከ15,000 በላይ ተመዝጋቢዎች 60 እደለኞች ብቻ መመረጣቸው ሳያንስ ይኸውም የ60 ሰዎች ዕጣ አወጣጥ ትክክል ያልሆነና ተዓማኒነት የጎደለው ነው።

- ሌላ ያስተዋልው የተመዝጋቢዎች ስም ዝርዝር ተብሎ የተመዘገበው ላይ እስከ አያት ድረስ በተመሳሳይ ደብል የሆኑ ስሞች አሉ” የሚሉ ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ፤ የተነሳውን #ቅሬታ በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ የብሉዞን ማርኬቲንግ ማናጀርና የኪ ሃውሲነሰግ ቦርድ ሜምበር አቶ ቸርነት መንግስቴን አነጋግሯቸዋል።

እሳቸው ምን አሉ ?

ወደ ሲስተም ሲሞላ የታይኘ ኢረር ይኖረዋል። ባለ 2 የተመዘገበን ሰው ባለ 1 ብለህ ልትጽፍ ትችላለህ፣ ባለ 1 የተመዘገበን ባለ 3 ትላለህ። 

ይኼ ከሆነ ምናልባት ደንበኛው ራሱ ደግሞ ዕጣ ውስጥ ' መካተት ፤ አለመካተቱን ' እንዲያረጋግጥ ፣ እንዲህ አይነት የታይፕ ስህተቶች ተፈጥረው ከሆነ ታይቶ እንዲነገረን ፖስት አድርገንላቸዋል። 

በቴሌግራም ላይ ፖስት ካደረግን በኋላ ጥቂት ቁጥሮች ባለ 2 ብለን እኛ ሲስተም ላይ ፅፈናቸው ‘አይ እኔ የተመዘገብኩት ባለ 3 ነው’ ሊሉ ይችላሉ። እሱን ከውሉ ጋር ወዲያው ከሀርድ ኮፒው እናመሳክራለን። ሲስተሙ ላይ ይስተካከልላቸዋል። ምክንያቱም አዲስ ሲስተም ነው። መሞከሪያም ነው መስተካከል አለበት።

ፓስት ያደረግነው ቁጥር ሁሉም ማለት አይደለም የተወሰኑ ሰዎች ‘እንዲህ አስተካክሉልን’ ብለውናል። አስተካክለንላቸዋል። ‘አስተካክሉልን’ ያሉን ሰዎች ከተስተካከለላቸው በኋላ በቀጥታ ሰነዱን ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው ያስረክብነው የተስተካከለውን። 

ቴሌግራም ላይ ፖስት የተደረገው ያልተስተካከለው የመጀመሪያው (አስተያዬት ለመሰብሰብ ፓስት የተደረገው) ነው። ዕጣ ከወጣ በኋላ ሰዎች ሂደው ሲያመሳክሩ ያን ያዩታል። ግን እነዛ ሰዎች እዚጋ እንዲስተካከልላቸው ሆኗል። ራሳቸው ባቀረቡት መሠረት ማለት ነው።

እንዲህ ካደረጋችሁ ፥ በተመዝጋቢዎች በኩል ብዥታ እንዳይፈጠር ለምን የተስተካከለውን በድጋሚ ፖስት አላደረጋችሁላቸውም ? ብሎ ቲክቫህ ጠይቋቸዋል።

ምላሻቸውም ፤ " ካለፈ በኋላ ፓስት ማድረግ እንችል ነበረ " ብለዋል።

ዕጣው ከመውጣቱ በፊት #የተስተካከለውን ሰነድ ፓስት ያላደረጉበትን ምክንያት ሲያስረዱ ፤ " የተጣራው ለአዲስ አበባ የምንሰጠው ሰነድ ነው። የአዲስ አበባን ዩኒቨርሲቲ Soft ware ከሰራበት በኋላ ነው እንጂ ኦዲት የምናደርገው ቀድመን ምን ይደረግ የሚለውን አናውቅም። ዜሮ፣ ዜሮ መሆኑን ብቻ ነው የምናየው " ሲሉ ተናግርዋል።

በተጨማሪ ...

ባለ 3 መኝታ ቤት ዕድለኛ ተብለው ዕጣ የወጣላቸው ተመዝጋቢዎች አብዛኛዎቹ ባለ 2 ተመዝጋቢዎች ናቸው ፤ ተብሎ ለቀረበው ቅሬታ

° " ይህ #እውነት_አይደለም። ምክንያቱም ባለ 2 ተመዝግበው ባለ 3 እንዴት ይደርሳቸዋል ? የደረሰውስ እንዴት ይቀበላል ? የማይሆን ነገር ነው " ሲሉ መልሰዋል።

ዕጣ ከማውጣቱ በፊት ለባለ 3 ፣ ለባለ 2 እንዲሁም ለባለ 1 የቤት ዕድለኞች ያቀዱት ፐርሰንቴጂ ዕጣው ከወጣ በኋላ ተቀያይሯል ተብሎ ለተነሳው ቅሬታ

° “ ቤቱን ገና አላስተላለፍንላቸውም። ገና በ18 ነው ቤቱን የሚረከቡት።

የሚረከቡትም በተባለው መሠረት ባለ 1 መኝታ ቤት ዘጠኝ ሰዎች፣ ባለ 2 መኝታ ቤት 21 ሰዎች፣ ባለ 3 መኝታ ቤት 30 ሰዎች ናቸው። ባልተዘጋጁ ቤቶች ዕጣ አናወጣም። ከየትስ እናመጣዋለን " ከሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ድርጅቱ ማብራሪያ ሊሰጥ ፈቃደኛ አልሆነም ተብሎ ለተነሳው ቅሬታ

° “ ተወካይ ነን ብለው ለመጡ አባላቶች (የምር ተወካይ አይደሉም፤ የተወካይ ህጋዊ ሰነድ የላቸውም) ፤ ግን ነገሩ መልካም ስለሆነ ቢሮ ለእያንዳዱ ሰነድ ጭምር እያሳዬን ማብራሪያ ሰጥተናል ” ሲሉ መልሰዋል።

በተመሳሳይ ስም የተጠቀሱ " ዳብል " ተመዝጋቢዎች መኖራቸው ተከትሎ ለቀረበው ቅሬታ

° " ... እንድ ተመዝጋቢ #ለብዙ_ሰዎች መመዝገብ ይችላል፣ ኮዱም ቢሆን ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል " ሲሉ መልሰዋል።

በአዲስ አበባ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ።

@tikvahethiopia
#ቅሬታ

የፓስፖርት ጉዳይ ...

ከፓስፖርት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ወገኖች አሰፈላጊው ማስተካከያ እንዲደረግ አሳሰቡ።

" የተሰራ ፓስፖርት ለመስጠት ህዝቡ እጅግ በጣም ዘግናኝ በሆነ መልኩ እየተንገላታ ይገኛል። " ያሉት ለቲክቫህ መልዕክታቸውን ያደረሱ ወገኖች ፤ በቀን የሚሰጠው ፓስፖርት ውስን ነው ብለዋል።

" በቀኑ ስለማይሰጥም ባስቀመጡት ቀን ተገልጋዩ እየተመላለሰ መከራ እየበላ ነው። " ሲሉ ሁኔታውን ገልጸውታል።

በተለይ ጎተራ አካባቢ ሌሊት ወረፋ ለመያዝ ብር  የሚጠይቁ እንዳሉ ፤ አንዳንዱ ከፍሎ ወረፋ እንደሚይዝ የሌለው ደግሞ ሌሊት ሂዶ ከገባ በኋላ ሰልፋን ይበትኑና ቀኑን ሙሉ በህዝብ ሲጫወቱ ውለው 10 ሰዓት ላይ በዱላ ደብድበው እንደሚያስወጡ በምሬት ገልጸዋል።

" በቀጣዩ ሳምንትም እንደዛው። " ሲሉ አክለዋል።

" የብዙ ሰው ቪዛ እየተቃጠለበት ለብዙ ወጪ እየተዳረገ " መሆኑን የሚገልፁት እነዚህ ወገኖች " በየወረዳው ቢበትኑ እንዲሁ። በፊደል ተራ በተለቀቀበት ቀን ቢሰጡ/they mix it/  ጥሩ ነው። የህዝብ እንግልት ግድ የሚሰጠው ካለ መፍትሄ ይፈልግ !! " ሲሉ አሳስበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ 1.2 ቢሊዮን የምስኪን ሕዝብን ገንዘብ 4 ዓመታት ሙሉ ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ እየተጠቀመበት ነው። በውላችን መሠረት መኪና አላስረከበንም ” - የቱሪስት ታክሲ ማኀበራት በስራቸው ከ2,800 በላይ አባላት ያሏቸው ከ40 በላይ የሚሆኑ ሕጋዊ የቱሪስት ታክሲ ማኀበራት ከ3 ዓመታት በፊት " ከኦክሎክ ትሬዲንግ/ኃላ/የተ/የግ/ ማኀበር " መኪና እንዲቀርብላቸው ቢዋዋሉም መኪናው ሳይቀርብ የውል ገደቡ እንዳለፈ፣…
#ቅሬታ

“ እኔ 1.5 ሚሊዮን ብር ነው #የተጨመረብኝ። እውነት ድርጅቱ ጨምሮበት ነው ወይስ የድሃ እንባ ፈልጎ ነው ? ”- እያለቀሱ ቅሬታ ያቀረቡ ቆጣቢ እናት

2012 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ በኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር አማካኝነት መኪና ለማስመጣት ገንዘብ ሲቆጥቡ የነበሩ ከ40 በላይ በሆኑ ማኀበራት ሥር የሚገኙ ከ2 ሺህ 800 በላይ ቆጣቢዎች፣ ውል የገባላቸውን መኪና አስመጪ ማኀበሩ በውሉ መሠረት መኪናውን እንዳላቀረበላቸው ገልጸዋል።

ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መካከል አንዱ ቆጣቢ፣ “ እኔ በሥነ ስርዓት መረጃ አለኝ። በእኛ ስም እየመጣ እየተሸጠ ነው። ለዚህ እኔ ምስክር ነኝ ” ሲሉ ኦክሎክ ጀነራል ቲሬዲንግን ኮንነዋል።

ሌሎች ቅሬታ አቅራቢዎች በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

➡️ አንድ ቅሬታ አቅራቢ፣ “ ገንዘባችንን ሰጥተን ለማኝ እየሆንን ነው። ገንዘባቸውን ከፍለው እንደገና የጥበቃ ሰራተኛ ሆነው ተጠግተው መኪና ያገኙ ራሱ አሉ ” ብለዋል።

➡️ ሌላኛው አባት በበኩላቸው፣ “ መኪናውን የሚጠብቁ ሁለት ልጆች አሉኝ። ገናኮ ለየትኛው እንደምሰጥ እያሰብኩ ነው ያለሁት” ሲሉ የነበራቸውን ተስፋ አስረድተው፣ “ ጎዳና ላይ ከምታድር ድሃ መቀነቷን ፈትቶ እንደመውሰድ ነው። ችግር ካለ ስብስቦ ሊጠይቀን ይችል ነበር። ግን በስማችን መነገድ ነው የፈለገው ” ብለዋል።

➡️ ሌላኛዋ ቆጣቢ በበኩላቸው ፦

“ ውላችን ከ3 እስከ 6 ወራት፣ ካልሆነ ደግሞ እስከ 1 ዓመት ነበር፣ 60 ሺሕ ከፍለን የሚለው። 25 በመቶ መኪናው አገር ውስጥ ከገባ በኋላ ገንዘብ እንከፍላለን የሚል ነው ውላችን ላይ የነበረው። 60 ሺሕ ከፍለን እያለ 2013 ዓ/ም ላይ 25 ፐርሰንት ክፈሉ ተብሎ የመኪናውን ዋጋ 25 በመቶ ስንከፍል፣ እኔ ተመዝግቤ የነበረው መኪና 520 ሞዴል ነበር። የመኪናው ዋጋ 520 ሺሕ ብር ነበር። 

በመካከል 25 በመቶ ክፈሉ ‘የቻንሲና የሞተር ቁጥር መጥቷል’ ተብሎ ተከፈለ። ነገር ግን ‘ይህን መኪና ፋብሪካው ማምረት ስላቆመ 690 ሺሕ የሚመረተውን መኪና ቀይሪ’ ተብዬ 690 ሺሕ ብር የመኪናውን 25 ፐርሰንት 2013 ዓ/ም ኀዳር ወር ከፍዬ እየጠበኩ ሁለት ዓመታት ተቆጠሩ።

በ2014 ዓ.ም ከ2,800 በላይ አባላት በተገኙበት ኦሮሚያ የባህል አዳራሽ ተሰብስቦ ‘ከጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የመጣሁ ነኝ መኪናችሁን 1 ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ተውስዳላችሁ። እንባችሁ ታብሷል ” ያላቸው አካል እንደነበር ገልጸው፣ ምንም መፍትሄ ስላልተገኘ፣ መንግሥት ይዳኘን " ሲሉ ጠይቀዋል።

➡️ አንዲት እያለቀሱ ቅሬታቸውን ያቀረቡ እናት በመጀመሪያ የነበረውን ውል መሠረት በማድረግ ተስማምተው እንደገቡ ገልጸው፦ “ ሁለት ወራት ጠበቁና 35፣ ‘45 ፐርሰንት ጨምሩ’ አሉን። ያን አድርገን ሳንጨርስ (ተበድረን ያስገባነውን ጉድ) መልሰው ሦስት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ‘400 ሺሕ ብር ጨምሩ፣ አበዳሪ ተገኝቷል በሁለት ወራት ውስጥ ገጣጥመን እናስገባለን’ አሉ። እኔ 1.5 ሚሊዮን ብር ነው የተጨመረብኝ። እውነት ድርጅቱ ጨምሮበት ነው ወይስ የድሃ እንባፈልጎ ነው?። አልገባኝም። #መንግሥት_ይዬን ። ” ሲሉ እያለቀሱ ቅሬታ አቅርበዋል።

➡️ ሌላኛው ቆጣቢ በበኩላቸው፣ “ ትዳራችንን ልናፈርስ ጫፍ ላይ ደርሰናል። አብዛኞቻችን ደግሞ የተሸወድነው የመንግሥት ባለስልጣንና ባንክ ቁጭ አድርጎ ቃል ሲገባልን ነው ” ነው ያሉት።

#TikvahaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia