TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EthiopianFederalPolice

መነሻቸውን ብራዚል ሳኦፖሎ መዳረሻቸውን ደግሞ ዱባይና ናይጄሪያ በማድረግ በአውሮፕላን ሲጓዙ የነበሩ የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎች በትላንትናው ዕለት በኢትዮጵያ 🇪🇹 ፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎቹ 2 ናይጄሪያዊያንና አንዲት ብራዚላዊት ሲሆኑ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተደረገባቸው ፍተሻ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል።

ግለሰቦቹ አደገኛ ዕፁን በውስጣዊ የሻንጣ አካል በመደበቅና ውጠው በሆዳቸው በመያዝ ለማሳለፍ ሙከራ ቢያደርጉም የፌደራል ፖሊስ አባላት ባደረጉት የተጠናከረ ፍተሻ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት 3 የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎቹ መካከል በብራዚላዊቷ ላይ በተደረገ ፍተሻ ከ13 ኪሎግራም በላይ የሚመዝን 666 ጥቅል ፍሬና በዱቄት መልክ የተዘጋጀ ከ17 ኪሎግራም በላይ የሚመዝን 11 እሽግ ኮኬይን የተሰኘ አደገኛ ዕፅ በሻንጣዋ ይዛ መገኘቷን ተረጋግጧል።

ሁለቱ ናይጄሪያዊያን አደገኛ ዕፁን በሆዳቸው ይዘው ሊያዘዋውሩ እንደሚችሉ በመጠራጠር በፌደራል ፖሊስ ሆስፒታል በተደረገላቸው የኤክስ ሬይ ምርመራ የተገኘባቸው ሲሆን 1,650 ግራም የሚመዝን 83 ፍሬ ኮኬይን ከሆዳቸው እንዲወጣ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በአሁኑ ወቅት ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ተጨማሪ ምርመራ እያካሄደ መሆኑ ታውቋል፡፡

@tikvahethiopia
#EthiopianFederalPolice

ከዚህ ቀደም ወደ ሌላ ሀገራት ተልኮ ይደረግ የነበረው የዘረመል (DNA) ምርመራ ከ1 ወር በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።

በሀገር ውስጥ የዘረ-መል ( DNA ) ምርመራ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚጀመር የገለፀው ፌዴራል ፖሊስ፤ በአስር ዓመቱ ስትራቴጂክ ዕቅዱ ከአፍሪካ ምርጥ 5 የፖሊስ ተቋማት አንዱ ሊሆን አሰራሮቹን በቴክኖሎጂ እያዘመነ መሆኑን አስታውቋል።

ከቴክኖሎጂ ባለፈ ፖሊስ ውጤታማ ስራ ለመስራት ያስችለው ዘንድ አዳዲስ አደረጃጀቶች አዋቅሯል።

አዳዲሶቹ አደረጃጀቶች እያደገ የመጣውን የአየር እና የየብስ ትራንስፖርት ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ናቸው ተብሏል።

በተጨማሪም ኢንዱስትሪዎችንና ዩኒቨርሲቲዎችን ትኩረት አድርገው መዋቀራቸውን ተገልጿል።

አዳዲሶቹ አደረጃጀቶች ፦

👉 የአቪየሽን ፖሊስ፣
👉 የምድር ባቡር ፖሊስ፣
👉 የዩኒቨርሲቲ ደህንነት ፖሊስ እንዲሁም በኢንዱስትሪ እና ቱሪዝም ላይ ትኩረት አድርጎ የሚከታተል የፖሊስ ክፍሎች መሆናቸውን ኤፍ ቢስ ዘግቧል።

 @tikvahethiopia
#EthiopianFederalPolice

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ፤ በኢትዮጵያ ከፍተኛ አደጋዎች ሲያጋጥሙ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ የተደራጀ ቡድን ሊቋቋም እንደሆነ አሳውቋል።

የሚቋቋመው ግብረ ሃይል ከህክምና፣ ፎረንሲክ፣ መረጃና ሌሎች ተቋማት የሚውጣጡ ባለሙያዎችን ያካተተ ነው።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከአለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ጋር በመተባበር ቡድኑን መመስረት የሚያስችሉ አሰራሮችን ለመዘርጋት የሚያስችል ውይይት አካሂዷል።

በኢትዮጵያ የአውሮፕላን አደጋን ጨምሮ በሚከሰቱ ሌሎች ከባድ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ተጎጂዎችን የሚለይ “ዲዛስተር ቪክትም አይደንቲፊካሽን ቲም” እስካሁን አልተቋቋመም።

በዚህም ምክንያት ለአደጋ ፈጥኖ ያለመድረስ፣ ተቀናጅቶ አለመስራት፣ የዘረመል ምርመራ አለማድረግ እና ሌሎችም ችግሮች እንደነበሩ ተገልጿል።

የሚቋቋመው ቡድን በቀጣይ አደጋዎች ሲገጥሙ ፈጣን ምላሽ በመስጠት የነበሩ ችግሮች ይቀርፋል የተባለ ሲሆን ከተለያዩ አገሮች ልምድ ተወስዶ የሚቋቋም በመሆኑም በአደጋ ወቅት ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ ክፍተቶችን እንደሚያስቀር ተገልጿል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግር እና ወከባ ፈጥረዋል ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉት 6 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት የፌዴራል ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን የግዜ ቀጠሮ ፈቅዷል። ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው በጠበቆቻቸው አማካኝነት ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል። የፖሊስን የምርመራ…
#FederalPolice

የፌዴራል ፖሊስ " በሽብር እና በሲቪል አቪየሽን ሕግ ጥሰት ወንጀል ጠርጥሬያቸዋለሁ " ብሎ በቁጥጥር ካዋላቸው መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከ1989 ዓ ም ጀምሮ እሰከ 1999 ዓ ም በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች ተከሶ ዳዊት ድሪባ በዳኔ በሚል ስም 3 ጊዜ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ደጋጋሚ ወንጀለኛ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት  2ኛ ወንጀል ችሎት ታህሳስ 25 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችሎት ፦
- በዘረፋ፣
- በቅሚያ፣
- በሌብነት፣
- በቤት ሰብሮ  ስርቆት እና በደንብ መተላለፍ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበት ነበር።

ተጠርጣሪው ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ ፣ ጀማል ኑሩ እና ዳዊት ድሪባ በዳኔ የሚሉ ስሞችን በመጠቀም ፦

➡️ 11 ጦር መሣሪያ መዝረፍ ወንጀል፣

➡️ 6 ቅምያ ወንጀል፣

➡️ 3 ሌብነት ወንጀሎች፣

➡️ 3 ሰው #መግደል ወንጀል፣

➡️ 2 ስርቆትና ቤት ሰብሮ ስርቆት ወንጀሎች፣

➡️ አንድ ሐሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል፣

➡️ ከእስር ማምለጥ ወንጀል

➡️ አንድ ደንብ መተላለፍ የወንጀል ሪከርድ በአጠቃላይ 28 የወንጀል ሪካርዶች እንዳሉበት ፖሊስ አመልክቷል።

ከዚህ ውስጥ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት መጋቢት 24 ቀን በዋለው ችሎት ስድስት መዝገቦችን ሦስት ጊዜ አጣምሮ  ሦስት ጊዜ በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ ተላልፎበት ነበር።

እንደገና የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ሚያዚያ 30 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችሎት በጦር መሣሪያ የታገዘ የዘረፋ፣ ከአስር ቤት የማምለጥና በሌብነት ወንጀል የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ቅጠት አስተላልፎበት ነበር።

ተጠርጣሪው በውሳኔው መሠረት ማረሚያ ቤት የገባው ይግባኝ ጠይቆ ሞት ፍርዱ ወደ እድሜ ልክ የተቀየረለት ቢሆንም በድጋሚ ይግባኝ በማለቱ ቅጣቱ ወደ 25 ዓመት ተቀንሶለት ለ17 ዓመታት በማረሚያ ቤት ከቆየ በኋላ #በይቅርታ መፈታቱን ከፖሊስ የምርመራ ማህደር ማረጋገጥ እንደተቻለ ተገልጿል።

#EthiopianFederalPolice

@tikvahethiopia