TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#FerweyniMebrhatu #CNN

"ፍሬወይኒ መብራሃቱ በአውሮፓውያን አቆጣጠር የ2019 የሲ.ኤን.ኤን የዓመቱ ጀግና ተብላ በመጠራቷ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል። ሴት ልጆች በትምህርት ቤት እንዲቆዩ ያላት ቆራጥነት፣ እንዲሁም ማኅበረሰቧን የተሻለ ለማድረግ ያላት አቋም የሚደነቅ ነው። ኢትዮጵያ በፍሬወይኒ ኮርታለች።" ዶ/ር ዐብይ አህመድ (የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚኒስትር)
.
.
"የእኛው ፍሬወይኒ CNN የ2019 ጀግና ሆነች!! እንኳን ደስ አለሽ! በተፈጥሯው ጉዳይ ለሚሸማቀቁ: ከትምህርታቸው ለሚስተጏጎሉ: ለሚያቋርጡ:ከሌላው በታች የሆኑ ለሚመስላቸው..የአገራችን ሴቶች ትልቅ ቀን ነው!ተባብረን ዘላቂ መፍትሄ እናምጣ!" ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ (የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት)

@tikvahethiopiaBot @tikavhethiopia
#CNNHero2019 #FerweyniMebrhatu

«አሸናፊ መሆኔ የሚገርም ነገር ነዉ። ብቻ እንደ ግለሰብ በጣም ያኮራል። ትልቁ ግን ግን ሃገርን ማስጠራት ማለት ኩራት ነዉ። ለአፍሪቃም ኩራት ነዉ። ስለዚህ ይህን ጉዳይ ጉዳያችን ብለን ለዓለም ሕዝብ ፤ ለመጀመርያ ጊዜ ለመላዉ ዓለም ያሳወቅንበት ነዉ። ጥሩ ስራ ተሰርቶአል እስካሁን ድረስ ፤ ግን ብዙ ስራ እንደሚጠብቀን ነዉ የሚያሳየን። ሆኖም ግን ብቻችንን የምንሰራዉ ስራ ስላልሆነ፤ የዓለም ሕዝብ በሙሉ ድምፅ ሰጥቶ እዚህ ደረጃ ላይ አድርሶናል። ዘንድሮ ለዉድድር ከኔጋ የቀረቡት አስሩም ጀግኖች በጣም ጥሩ ስራን ሰርተዉ ነዉ የቀረቡት። ሆኖም ግን የኛ በለጥ ብሎ የታየበት ምክንያት፤ ሁሉንም ማኅበረሰብና ዜጋ የሚነካ ጉዳይ በመሆኑ ነዉ። የሴቶች ጉዳይ ደግሞ ለዘመናት የቆየ ጮክ ብለን የማንናገርለት ችግራችን ነበር። አሁን ግን እዚህ ላይ የደረስነዉ የችግሩን መፍቺያና የግንዛቢ ማስጨበጫ በመስራታችን ነዉ። እናም ለሃገር በተለይ ጥሩ ጥሩ መፍትሄ ነዉ የሚሆነዉ። እንደ አፍሪቃዉያንም በጣም ትልቅ ኩራት ነዉ። አንድ የ «CNN» ጀግና ከአፍሪቃ ሲገኝ ይህ ለመጀመርያ ጊዜ ነዉ። ለ «CNN» ኖች ስለሸለሙኝ ምስጋናዬን ገልጬላቸዉ ነበር። ነገር ግን « ድምፅ የሰጠሽን ህዝብሽን አመስግኝ» ነዉ ያሉኝ መላዉ ኢትዮጵያዉያንን አመሰግናለሁ!» - ፍሬወይኒ መብርሃቱ

#DW

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot