TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AntonioGuterres #Tigray

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ በርካታ የኢትዮጵያ ትግራይ ክልል አካባቢዎች ረሃብ አፋፍ ላይ መሆናቸው ተናገሩ፡፡

ዋና ጸሃፊው የትግራይ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ እጅግ አስከፊ ወደ ሆነ ደረጃ መሸጋገሩ አይቀሬ ነው ሲሉ አሳስበዋል፡፡

 የተጋረጠውን የረሃብ አደጋ ለመግታት ሰብአዊ እርዳታ ማዳረስ እንዲሁም በቂ ፈንድ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ዋና ጸሃፊው በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልእክት አስታውቋል፡፡

"አሁን የሚከናወኑ ተግባራት ለበርካታ ሰዎች የመኖርና አለመኖር ጉዳይ መሆናቸውን መረዳት ተገቢ ነው"ም ነው ያሉት የተ.መ.ድ ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ፡፡

የጉተሬዝ ትግራይን የተመለከተ መግለጫ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በትግራይ ያሉ የግጭቱ ተዋናዮች ተኩስ እንዲያቆሙና ያልተገደበ የስብአዊ እርዳታ ተደራሽነት እንዲኖር ጥሪ እያደረገ ባለበት ወቅት መሆኑን አል ኣይን በድረገፁ አስነብቧል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ/ኦቻ/ እየተካሄደ ባለው ግጭት ሳቢያ በትግራይ ያለው የሰብዓዊ ቀውስ አሳሳቢ መሆኑን እና በኢትዮጵያ ከ1970ዎቹ ወዲህ ከፍተኛ የረሀብ አደጋ እንዳንዣበበ ባለፈው ሳምንት አሳትውቋል።

#AlAIN

@tikvahethiopia
#Tigray

ምክትል ጠ/ሚና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዛሬ በቪድዮ መልዕክት አሰራጭተዋል።

በመልዕክታቸውም በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በመጠቀም የተለያዩ አካላት በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር የሚያደርጉት ጥረት ኢትዮጵያን አሳዝኗል ብለዋል።

ኢትዮጵያ አሁን ላይ የሚያስፈልጋት ጠንክራ ድጋፍ መሆኑን በመግለፅ፥ የኢትዮጵያን ህዝቦችና የግዛት አንድነት አንዲሁም ትስስርን በሰብዓዊነት ሽፋን ዝቅ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ተቀባይነት የለውም ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍን ከፍ ለማድረግ፣ ማህበራዊ ትስስርን መልሶ ለመገንባት እና መሰረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ከሁሉም አጋሮቿ ጋር ለመስራት ዝግጁ ናት ሲሉም ተደምጠዋል።

በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ወገኖች በሰብዓዊነት ሽፋን የኢትዮጵያን ህዝቦች እና የግዛት አንድነት እና ትስስር ለማዳከም ተልእኮ ይዘው ሲሰሩ ማየት 'የሚያሳዝን ተግባር ነው' እነዚህ ግለሰቦች እና አጋሮቻቸው ከዚህ ተግራቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል።

አቶ ደመቀ፥ "ኢትዮጵያ በራሷ ዜጎች ላይ ረሃብን እንደ ጦር መሣሪያነት እየተጠቀመች ነው" በሚል በሀገሪቱ ላይ የተለጠፉ ክሶች መሰረተ ቢስ ናቸው ብለዋል፤ እንደዚህ አይነት ክሶች በምንምን ስሌት ሰላምንና መረጋጋትን ለመፍጠር አይረዱም።

የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪ አካላት በትግራይ ውስጥ በነጻነት እንዲሰሩ የሚያስችሉ አሰራሮች መዘርጋቱን ገልፀው፥ “አንዳንድ ተዋንያን ግን በሰብዓዊ ዕርዳታ ሽፋን የሽብርተኞችን ቡድን ለማስታጠቅ መሣሪያዎችን በድብቅ ለማስገባት መሞከራቸውን የሚያመለክቱ ተዓማኒ #ማስረጃዎች እንዳሉ ተናግረዋል፤ይህ አይነቱ ድርጊትት ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

#AlAIN
@tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅትን እንዲመሩ በድጋሚ እጩ ሆነው ቀረቡ፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ በራሱ በዓለም ጤና ድርጅት ቦርድ ነው በድጋሚ እጩ ሆነው የቀረቡት፡፡

ይህም በመጪው ወርሃ ግንቦት 2022 ለሚካሄደው የዋና ዳይሬከተርነት ምርጫ በብቸኛነት የቀረቡ እጩ ያደርጋቸዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ምርጫውን አሸንፈው ድርጅቱን በድጋሚ በዋና ዳይሬክተርነት የመምራታቸው እድል ሰፊ ስለመሆኑ ይነገራል፡፡

#AlAIN

@tikvahethiopia
የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፦

" ከዓለም ህዝብ ሩብ ያህሉ (2 ቢሊዮን ህዝብ) በጦርነት ቀጠና ውስጥ እየኖረ ነው።

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ሁከትን የፈጠሩ ከፍተኛ ግጭቶች አሁን ላይ ተስተውለዋል።

በየመን፣ በሶሪያ፣ በሚያንማር፣ በሱዳን፣ ሄይቲና ሳህል ቀጠና ያሉ ጦርነቶች እንዲሁም የቅርብ ጊዜው የዩክሬኑ ጦርነት ዓለም የተገነባበትን ስርዓት የሚሸረሽሩ ናቸው።

እነዚህ ጦርነቶች #በምግብ#በነዳጅ እና #በማዳበሪያ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ እንዲኖር ምክንያት ሆነዋል።

ባለፈው ዓመት ብቻ 84 ሚሊየን ሰዎች ጦርነት በፈጠረው ሁከትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት ቤታቸውን ለቀው ተሰደዋል።

በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል የተደረገው ጦርነትም 4 ሚሊዮን ዜጎችን ከዩክሬን ሲያስወጣ በሀገሪቱ ውስጥ ደግሞ 6 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚሆኑት እንዲፈናቀሉ አድርጓል።

በዚህ ዓመት ብቻ 274 ሚሊየን ሰዎች ሰብዓዊ ድጋፍ የሚፈልጉ ሲሆን ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ 17 በመቶ ጨምሯል "

#AlAIN

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ አማራ ባንክ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ሥራውን በይፋ ጀምሯል። የባንኩ የምረቃ እና ስራ ማስጀመሪያ ሰነ ስርዓት ለገሃር በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ነው የተካሄደው። በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ፦ - የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ፣ - የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ፣ - የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት…
#AmharaBank

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ዛሬ በዛሬው የአማራ ባንክ ይፋዊ ምረቃና ስራ ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ የተናገሩት ፦

" አማራ ባንክ ወደ ገጠሩ ማህበረሰብ በመድረስና ከፍተኛ የአክስዮን ድርሻን በመሸጥ እንዲሁም ከፍተኛ የተከፈለ ካፒታል ይዞ የባንክ ኢንዱስትሪውን በመቀላቀል ቀዳሚው ነው።

በቴክኖሎጂ እና በአገልግሎት አሰጣጥም ተወዳዳሪ በመሆን ቀዳሚ መሆን እንዲችል ራሱን ሊያዘጋጅ ይገባል።

ይህ ከሃገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ከሚታሰቡ የውጭ ባንኮች ጋር ጭምር ለመወዳደር ያስችላል።

ወደ ሀገር እንደሚገቡ ከሚጠበቁት የውጭ ባንኮች ጋር ለመወዳደር ትልቅ ዝግጅት ይጠብቀናል። ለዚህም አማራ ባንክን ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ ባንኮች ራሳቸውን ሊያዘጋጁ ይገባል።

አማራ ባንክ ይህን የሚያደርግና የቁጠባ ገንዘብ አቅሙን ለማሳደግ የሚችል ከሆነ በአጭር አመታት ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ሊደርስ ይችላል።

... 60 ሚሊዮን ገደማ ኢትዮጵያውያን የተንቀሳቃሽ ስልክ (ሞባይል) ተጠቃሚ ናቸው ፤ አማራ ባንክ የተፋጠነ የሞባይል አገልግሎትን በየደረጃው ለመስጠት መስራት አለበት።

የሞባይል አገልግሎት የሚሰጡ የውጭ ተቋማት በቅርብ ጊዜ የአገልግሎት ፈቃድ ሊያገኙ ይችላሉ፤ በአሁኑ ወቅት ቴሌ ብር ብቻ ነው አገልግሎቱን እየሰጠ የሚገኘው በመሆኑም አማራ ባንክ ቅርንጫፎችን ከመክፈት በዘለለ በቴክኖሎጂ ላይ ኢንቨስት ማድረግ ወደ ከፍታ ሊወስደው እንደሚችል አስባለሁ "

#ALAIN

@tikvahethiopia
#China

ኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ እና ሱዳን ስለ ቻይና-ታይዋን ጉዳይ ምን አሉ ?

#ኢትዮጵያ

ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰሞኑን የቻይና-ታይዋን ጉዳይ የተከሰተውን ውጥረት በትኩረት እየተከታተለች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ለኢዜአ ተናግረዋል።

አምባሳደር መለስ ፤ ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት ስታራምድ የቆየችውን የአንድ ቻይና ፖሊሲ አቋሟን እንዳጸናች መሆኑን ተናግረዋል።

" የኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ አቋም ዛሬ የተጀመረ አይደለም ያሉት " አምባሳደር መለስ፤ " ከቻይና ጋር በነበረን ግንኙነት ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስታት አፅንተው የያዙት አቋም ነው " ብለዋል።

አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያ ለ #አንድ_ቻይና ፖሊሲ ፅኑ አቋም አላት ያሉ ሲሆን ፖሊሲውን ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸው የተመድና የአፍሪካ ህብረት የሚያራምዱት አቋም መሆኑን ገልፀዋል።

#ሱዳን

ሱዳን ለአንድ ቻይና መርህ ድጋፏን እንደምትሰጥ አሳውቃለች። ታይዋንም የቻይና ግዛት አካል መሆኗን ገልጻለች።

ሱዳን ፤ ቻይና ሉዓላዊነቷን እና የግዛት አንድነትዋን በመጠበቅ ረገድ የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንደምትደግፍም አስታውቃለች።

#ኤርትራ

ኤርትራ የአሜሪካ አፈጉባዔ ወደ ታይዋን ያደረጉት ጉዞ ከዓለም አቀፍ ህግና መርህ ያፈነገጠ ነው ብላለች።

የአፈጉባኤዋ ድርጊት የቻይና መንግስት ሉዓላዊነት ደንቦችን እና ድንጋጌዎች እንዲሁም " የአንድ-ቻይና " ፖሊሲ የሚጻረር እና የቻይናውያን ውህደት ሂደትን የሚያደናቅፍ ነው ስትል ገልፃለች።

ኤርትራ፤ አሜሪካ ቻይናን ለመቆጣጠርና ለመያዝ ጥረት እያደረገች ነው ብላ ድርጊቱ አጸያፊ ነው ብላለች።

#CGTN #ENA #AlAIN #Shabait

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦ " ሀገሪቱ ካሏት 47 ሽህ ገደማ ትምህርት ቤቶች 99 በመቶዎቹ አመቺ አይደሉም። በተሰራው ምዘና አራት ትምህርት ቤቶች ብቻ ከፍተኛውን ደረጃ አሟልተዋል። 86 በመቶ የአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም 71 በመቶ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ፍፁም ከደረጃ በተታች ናቸው። በትምህርት ምዘናና ጥናት ውጤት ከ4ተኛ ክፍል 20 በመቶዎቹ…
የትምህርት ማስረጃ ማጣራት . . .

የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለህ/ተ/ም/ቤት የተናገሩት ፦

" በሁሉም #የፌደራል_ተቋማት የሰራተኞችን ማህደር መመርመር ጀምረናል። ምን ያህሉ እውነተኛ የትምህርት ማስረጃ ይዞ ነው ? ምን ያህሉ አይደለም የሚል ምርመራ እያካሄድን ነው፤ ከራሳችን ጀምረን።

ማህበረሰቡ ልክ እንደፈተናው [የ12ተኛ ክፍል ፈተና] እንዲያውቅልን የምንፈልገው ከአሁን በኋላ በተጭበረበረ ድግሪ፤ በተጭበረበረ ዲፕሎማ የሚሰራ ስራ አይኖርም የሚለውን ለማሳወቅ ነዉ። በዚህ ዓመት እሱን እንጨርሳለን ብለን እናስባለን። "

Credit : #AlAIN

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ሙሴቬኒ ምን አሉ ?

የዓለም ባንክ ፤ ኡጋንዳን ለምን የ " ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን የሚከለክል ሕግ ተግባራዊ አደርግሽ ፤ ይህ ሕግ መሰረታዊ ከሆኑ እሴቶቼ ጋር ይቃረናል " በማለት አዲስ ብድር እንደማይሰጣት አሳውቋል።

ይህ ውሳኔ በተመለከተ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዮሪ ሙሴቪኒ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ፕሬዜዳንት ሙሴቬኒ ምን አሉ ?

" ኡጋንዳ ያለ ዓለም ባንክ ብድር ማደግ ትችላለች።

የዓለም ባንክ እምነታችንን ፣ ሉዓላዊነታችንን እና ባህላችንን በገንዘብ እንድንቀይር እያስገደደን ነው።

ምዕራባዊያን አፍሪካን ዝቅ አድርገው መመልከት እና ጫና ማሳደር ይፈልጋሉ ፣ እኛ ችግራችንን እንዴት መፍታት እንዳለብን እናውቃለን፣ እነሱም የእኛ ችግሮቻችን ናቸው።

ኡጋንዳ ከዓለም ባንክ ጋር ያለባትን ችግር ለመፍታት የሚቻል ከሆነ ውይይት ለማድረግ ትቀጥላለች። " #ALAIN

ኡጋንዳ ባፀደቀችውና ተግባራዊ ባደረገችው የፀረ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ሕግ እድሜ ልክ በእስር ቤት መማቀቅን ጨምሮ ሞት ሊያስፈርድ ይችላል።

ይህን ሕግ አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን ሀገራት እና ተቋማት የተቃወሙ ሲሆን የዓለም ባንክ ደግሞ አዲስ ብድር አልሰጥሽም ብሏል።

@tikvahethiopia
በመላው ዓለም ኢንተርኔት ሊቋረጥ ይችላል ?

የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም ወይም በምህጻረ ቃሉ ናሳ ከሰሞኑ አንድ ማስጠንቀቂያ አውጥቷል።

የተቋሙ ማስጠንቀቂያም በሚቀጥለው ሳምንት በተለይም በፈረንጆቹ ጥቅምት 10 እና 11 ባሉት ቀናት ውስጥ ከባድ የጸሀይ መብረቅ ወይም ሞገድ ሊከሰት ይችላል ብሏል።

ይህን የናሳን ማስጠንቀቂያ መሰረት በማድረግ በመላው ዓለም ኢንተርኔት ሊቋረጥ ይችላል የሚሉ ዜናዎች በዓለም ላይ በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ።

ይህ ዜና በስፋት መሰራጨቱ ያሳሰበው ናሳም ኢንተርኔት በመላው ዓለም ይቋረጣል በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን አስታውቋል።

ድርጅቱ አክሎም በሚቀጥለው ሳምንት በጸሀይ ሀይል ምክንያት ይፈጠራል በተባለው መብረቅ የኢንተርኔት አገልግሎት ሊቋረጥ የሚችልበት ምንም አይነት ግልጽ ስጋት የለም ብሏል።

የአሜሪካ መንግሥት ንብረት የሆነው ናሳ ስለ ጠፈር ሳይንስ የተለያዩ ጥናቶችን እና ግኝቶችን ለመላው ዓለም በማቅረብ ይታወቃል።

Credit - #AlAin_Amharic

@tikvahethiopia
#TOYOTA

ቶዮታ / Toyota ዓለም አቀፍ የመኪና አምራች ኩባንያ በዓለም ገበያ በዋነኝነት #በአሜሪካ የተሸጡ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎቹን  ከገበያ ላይ እንዲሰበሰቡ አዟል።

ቶዮታ እንዲሰብሰቡ ያዘዘው ከ2020 እስከ 2022 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የተመረቱ ተሽከርካሪዎችን ሲሆን ተሽከርካሪዎቹ የ " ኤርባግ " ደህንነት ችግር አለባቸው ተብሏል።

ከ2020 እስከ 2022 ወደ ገበያ የቀረቡ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎች (በዋነኝነት #አሜሪካ) ከ " ኤርባግ " ጋር በተያያዘ ችግር እንዳለባቸው ተደርሶበታል።

ችግሩ በፊት ለፊት ተሳፋሪ መቀመጫ በኩል በስህተት ከተሰራ የ " ኤርባግ ሴንሰር " ጋር የሚያያዝ ሲሆን ምናልባትም በአደጋ ጊዜ " ኤርባጉ " አገልግሎት ላይሰጥ ይችላል። ይህ አደጋ በሚፈጠር ጊዜ ኩዳቱ እንዲጨምር ያደርጋል።

ቶዮታ የትኞቹ ሞዴሎች ይሰብሰቡ አለ ?

#ቶዮታ

ኮሮላ (2020 - 2021)
ራቭ4 ፣ ራቭ4 ሃይብሪድ (2020 - 2021)
ሃይላንደር፣ ሃይላንደር ሃብሪድ (2020 - 2021)
አቫሎን ፣  አቫሎን ሃይብሪድ (2020 - 2021)
ካምሪ፣ ካምሪ ሃብሪድ (2020 - 2021)
ሴና ሀይብሪድ (2021)

#ሌክሰስ

ES250 (2021)
ES300H (2020-2022)
ES350 (2020-2021)
RX350 (2020-2021)
RX450H (2020-2021) የተሰኙ ከ2020 እስከ 2022 ላይ የተመረቱት የ " ኤርባግ " ችግር ስላለባቸው ይሰብሰቡ ብሏል።

ከላይ የተጠቀሱት ተሽከርካሪዎች ያላቸው ሰዎች ኤርባጋቸውን #እንዲያረጋግጡ እና ችግር ካጋጠማቸው እስከ ቀጣዩ የካቲት ወር ድረስ እንዲመልሱለት ቶዮታ ጥሪ አቅርቧል።

የቶዮታ ተሽከርካሪዎች ችግር እንዳለባቸው የታወቀው የጃፓን ትራንስፖርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ ተሽከርካሪ እምራች ኩባንያዎች ላይ ባደረገው #ምርመራ ላይ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህን ተከትሎ የቶዮታ ኩባንያ አክስዮን ዋጋ ቅናሽ አሳይቷል።

ምርመራው ከቶዮታ ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ ዳይሀትሱ በተሰኘው ኩባንያ ላይም ተመሳሳይ ችግር መታየቱን ገልጿል።

ከ87 ዓመት በፊት ኪቺሮ ቶዮታ በተባለ ግለሰብ የተመሰረተው ቶዮታ የተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ አሁን ላይ በዓመት 10 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎችን በማምረት ላይ ይገኛል።

ከ360 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያሉት ቶዮታ ኩባንያ 300 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት እንዳለው የኩባንያው ዓመታዊ ሪፖርት ያስረዳል።

#ጥቆማ ፦ ከደህንነት ጋር በተያይዘ በተለይም በአሜሪካ እንዲሰበሰቡ የታዘዙ ተሽከርካሪዎችን ቼክ ለማድረግ https://www.nhtsa.gov/recalls በዚህ አድራሻ መጠቀም ይቻላል። የመኪናውን መለያ ቁጥር (VIN) በማስገባት ማወቅ ይቻላል።

Credit - #AlAiN / #Reuters / #Toyota_News_Room

@tikvahethiopia